Get Mystery Box with random crypto!

እባካችሁ ጻድቁን ያላችሁ በጻድቁ ስም!SHARE በማድረግ በማሳወቅ በረከት እናግኛ። +++ቀጣይ ጉ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

እባካችሁ ጻድቁን ያላችሁ በጻድቁ ስም!SHARE በማድረግ በማሳወቅ በረከት እናግኛ።
+++ቀጣይ ጉዞ ገዳሙ የሚያዘጋጀው(ጥቅምት12/13

ይህ በእናንተ ድጋፍ share በማድረጋችሁ በማሳወቃችሁ በመንገራችሁ የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ቤተክርስትያን ሊፈርስ ሲል በመድረሳችሁ እንዲሰራ እና በገዳሙ ዙሪያ ብዙ ስራ እንዲሰራ አድርጋችኋል፤ እየተሰራ ያለ የእናንተንም ደጋፍ የሚፈልግ ብዙ የሚሰሩ ነገሮች አሉ ተዘርዝረዋል። አሁንም እርዳታችሁ አይለየን በጻድቁ ስም እለምናለን.......?

+++[የምንሰራቸው ስራዎች በቀጣይ እርዳታ የሚያስፈልገው]+++

1፦ቤተክርስትያን ውስጡን ሙሉለሙሉ ለማደስ ከ2,900,000 (ሁለትሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሽይ ብር በላይ)ያስፈልጋል የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል

2፦የጻድቁን ገድል በብዛት እንዲታተም እንርዳ
ገድሌን ያሳተመ ያስተረጎመ የረዳ ያነበበ "ገድሌን በቤቱ ያስቀመጠ"እርኩስ መንፈስ አይነካውም፤አጋንት አይቀርብትም፤ቸነፈርና ወባ በሽታ አያገኛውም፤በሂወቱ ውስጥ መላኢከ ጽልመት አይነኩም አያገኙትም እኔ እጠብቀዋለሁ ይላ ገድላቸው ወዳጆቼ እንዲታተም አደረግን ማለት የሰው ልጅ ከመተት ፣ከመጥፎ ነገር ፤ከሰው ሰራች ሰይጣን ያደረባቸውን ሰዎች አዳንን አተረፍናቸው ማለት ነው የሚያምኑትን የድንግል ልጆችን የጻድቁ ልጆችን እኛን የምንኮራበትን እምነታችን ኦርቶድክስ ተዋህዶ አማኛችን ጠብቀው አኖሩልን ማለት ነው

3፦ለጸበል ለመጡ ማረፊያ ተጨማሪ አድራሽ ለመስራት የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል

4፦በገዳሙ አካባቢ ተጨማሪ መጸዳጃ ቤት፤የቤተክርስትያኑን ሙሉ አጥር እና የገዳሙ ሙዚየም(ዕቃ ቤት)ለመስራት የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል

5፦በገዳሙ አካባቢ የሚገኛን ንጹህ የምንጭ ውሃን ለጸበልተኛውና ለገዳሙ ለመስራት የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል

6፦ለቤተክርስትያናቱ የተለያዩ ስዕል አድኖችን ለማሰራት የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል

7፦የእንጨት መንበር ያስፈልጋል

8፦ገዳሙ ምንም መሬት ስለሌለው በዙሪያው ያለው ተገምቶ 4,280,000/አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ሽህ ብር /ክፈሉ ስለተባለ የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋል።

በገዳሙ ሂሳብ ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Acccount no-1000199224054
Account name-ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስትያን(Tegero Abune Echuge Yohannes Church)
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(Commercial Bank of Ethiopia)
Swift code-CBETETAA

ፃዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት
ይወስዳል። ማቴ 10፥41
-እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል። ማቴ 10፥40
- እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።
ዮሐ 9፥12
-የአለም ብርሃን ናችሁ!
-ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን 1ቆሮ6፥2
-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ። 88(89)፥3
- እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴ 10፥40-42

+++ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ጻድቁ 500አመት በያዙት መስቀላቸውንና መቋሚያቸውን የሄደ ሁሉ ይዳበሳል ይባረካል።

ገዳሙ ጉዞ አመቱን በሙሉ በወር 2ግዜ ያዘጋጃል።
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ የገዳሙ ኮሚቴ ጉዞ /ጥቅምት(12/13) /አዘጋጅቷል........ቃልኪዳናቸውን ለአለም ንገሩ አንብቡ እወቁ።ገዳማቸውን ለመርገጥ እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ!አሜን!!!

ትኬቱን ቅድማችሁ ቁረጡ በጉዞው ቀን ትኬት የለም የመኪና ችግር ስላለ።

መነሻ፦ጥቅምት12ቅዳሜ 12:00መስቀል አደባባይ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ፍለፊት መገናኛ ታክሲ መያዥ ጋር

መመለሻ/ጥቅምት13 የጻድቁን ጸበላቸውን ተጠምቀን በመስቀላቸው በመቋሚያቸው ተባርከን በረከት አግኛተን መመለስ። እግዚአብሔር ፈቅዶላችሁ ገዳሙን እረግጣችሁ እንቆቅልሻችሁን ይፍቱላችሁ!አሜን!!!

ለበለጠ መረጃ፦
/0911190212
/0911481388
/0979986969
/0901002929

ቦታው፦ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም ስንመለስ 2:00ሰዓት መንገድ።