Get Mystery Box with random crypto!

++++ይህ ሰሜንሸዋ መንዝና ይፋት መዘዞ ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም የሚገኞው ጻድቁ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

++++ይህ ሰሜንሸዋ መንዝና ይፋት መዘዞ ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም የሚገኞው ጻድቁ ከጸለዩበት ጥልቅ ባህር ውስጥ የወጣው የጻድቁ ግዕዝ ገድላቸው ሲሆን ከባህሩ ውስጥ ሲወጣ ጸበሉ ውሃ ነክቶት ሲወጣ ደረቅ አፈር ይራገፍ ነበር አሁን በዚህ ግዜ በንጽህና ምህመን ከጠበሉ ባህር ውስጥ ደረቅ አፈር በእጅ ይዞ ይወጣል።

በዚህ ገዳም ጻድቁ 500ዓመት የያዙት የእጃቸው መስቀል መቋሚያ ከዚህ ጠበላቸው ባህር ውስጠ ነው የወጣው።

+++++++ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፉት መዘዞ /ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ነው።
+++++ከፀበሉ ውስጥ ደረቅ አፈር የሚወጣበት፤ በቀስተደመና የተከበበ እና ከሰማይ ወደ ምድር ፀበሉ ላይ ብርሃን ተተክሎበት የሚታይበት ገዳም ነው። ቸሩ መድሃኒአለም የባረከው ፀበል እና ለጻድቁ ቃልኪዳን የሰጠበት ገዳም ነው፤ ቸሩ መድሃኒአለም ለጻድቁ ቃልኪዳን ሊሰጣቸው በወረደ ግዜ ይህ ፀበል እንደ እሳት ተፈለቀለቀ መላዕክትን ሲወጡ ሲወርዱ ይታዩ ነበር ይላል። /ገድለ ቅዱስ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ /

¶ +++አባታችን ዮሃንስም ጌታችንን እንዲህ አለው ~
የገድሌን መጸሐፍ የፃፈ ቃልኪዳኔንም በመታመን ያፃፈውን በደሉ ምንም እንኳን ከሁሉም ቢበዛ ስለ እኔ ብለህ ማርልኝ፤ጌታችንም አባታችን ዮሃንስን እንዲህ አለው እውነት እልሃለሁ ቃልኪዳንህንም በመታመንና በፀሎትህ የገድልህን መፅሐፍ ያፃፈውንና የፃፈውን በስምህም ታቦትን የቀደሰውን የተከለውን እኔም እቀድሰዋለሁ በመንግስተ ሰማያትም ስሙን እፅፈዋለሁ ኤዶም ከተባለች ገነትም በሚመነጭ በህይወት ውሃ አጥበዋለሁ በይቅርታዬ እና በቸርነቴም እንዳልበደለ አደርገዋለሁ።

¶~ገድሌ የሰማ ያሰማ በመንግሰተ ሰማያት 100እጥፍ አስጉንም እስኪሰጥ ድረስ የክርስትያኑ የምትሆን ገነትንም እሰጠዋለሁ 10ትውልድም እምርልሃለሁ ብሎ መድሐኒዓለም ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል።

¶~በገዳምህ ከየትም ቦታ መጥቶ የተቀበረ "መነኮሳት"ከሆኑ በሰማያት ያሉ ክንፎች አበቅልለታለሁ።

¶~አረማዊም ቢሆን አይሁድም ቢሆን፣ (ያላመነ ያልተጠመቀ) ቢሆንም፣ከሃጥያቱ ያልነጻ
ቢሆንም፣በገድልህ ታምኖ በገዳምህ አርፋ ቢቀበር ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር እልልሃለሁ፤እንዲሁም እንደ መቃብሬ ጎለጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ ብሎ መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ገብቶላችዋል።

~ገድለ ቅዱስ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ^.........."ገድሌን በቤቱ ያስቀመጠ"፦
¶~የረከሱ መናፍስት አይቀርብትም፣
¶~ክፉ አጋንትም አይቀርብትም፣
¶~የቸነፈርና የወባ በሽታም አያገኛውም፣
¶~በነፍሱም መላዕኢከ ጽልመት አይነኩትም አለም ፍጻሜ ድረስ እጠብቀዋለሁ እምረዋለሁ

እናታችንን መዳኞችን ቅድስት ድንግል ማርያም አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ በመጣዉ ነገር ሁሉ ሐገራችንን ኢትዮጵያዊ ህዝብን ይጠብቁልን፤አንድነትን ይስጡን።አሜን!

ገዳሙ የባንክ ቁጥር

በገዳሙ ሂሳብ ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Acccount no-1000199224054
Account name-ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስትያን(Tegero Abune Echuge Yohannes Church)
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(Commercial Bank of Ethiopia)
Swift code-CBETETAA

ለበለጠ መረጃ የገዳሙ ኮሚቴ፦
ሀ/0911190212
ለ/0911481388
ሐ/0979986969
መ/0901002929

ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፣ስለዚህ ነፍሴ
ፈለገቻቸው"መዝ•118/119÷129

-ዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት ይወስዳል።
ማቴ 10፥41

-እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል። ማቴ 10፥40

- እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።
ዮሐ 9፥12

-"ቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው"
መዝ 15÷3

-"እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ "
መዝ 4÷3

-"የጻድቅ ሰው ስራ ለዘልዓለም ጸንቶ ይኖራል "
መዝ 111÷7

-"እኔ እግዜአብሔር አምላካችሁ ቅድስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ"
ዘሌ•19÷2

-"ከአገርህ ውጣ ከአባትህ ቤት ከዘመዶችህ ተለይተህ እኔ ወደ ማሳይህ ምድር ሂድ " ኦሪት ዘፍ 12

/ቅዱሳን በአፀደ ነፍስ ያማልዳሉ/
-ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኃላ ከዚያ ጊዜ ከስጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ:: ኢዮብ 19÷26

/በዳዊት አማላጅነት ከተማዋ ከመጥፋ ትድናለች::/
-በ ዕድሜህ ላይ 15አመት እጨምራለሁ አንተና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ ስለ እኔም ስለ ባርያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ " 2ነገስት 20÷6

-ከሰማይም ከእንግዲህ ወዲህ በጌታችን የሚሞቱ ሙታን ብፁአን ናቸው::መንፈስ አዎን ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል:: ራዕይ ዮሐ 10÷1

-የአለም ብርሃን ናችሁ!
-ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን 1ቆሮ6፥2

-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19

-ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።
መዝ 88(89)፥3

- እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴ 10፥40-42

የቅድሳን ጸሎት (ምልጃ ) በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በቂ ማስረጃ ነው::

+++++++ሰሜንሸዋ መንዝ መዘዞ(ጸገሮ) ምዕረፈ ቅዱሳን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ]
+++++ገዳሙ ጉዞ ያዘጋጃል

== መስከረም28/29 በወር ፪/2 ግዜ ጉዞ ቅዳሜ እና እሁድ ያዘጋጃል
ጉዞ___
መነሻ፦= መስከረም 28
መመለሻ፦= መስከረም 29 ተባርከን መመለስ

ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388