Get Mystery Box with random crypto!

ሐዋሪያው ቅድስ ጳውሎስ የትዕግስትን ጠቃሚነት 'መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

ሐዋሪያው ቅድስ ጳውሎስ የትዕግስትን ጠቃሚነት "መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንታገሳለን " ብላል::ሮሜ 5÷4 በሀይማኖት መታገስ አለብን:በመከራ መታገስ አለብን::መከራ እንኳን ቢያጋጥመን የምንችለውን እንጂ የማንችለውን እግ/ር እንደማይሰጠንም "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም ነገር ግን ከሚቻለው መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግ/ር የታመነ ነው ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኃል::"ተብላል::1ኛቆሮ•10÷13
የትዕግስት ተቃራኒ ችኩልነት:በቶሎ ተስፋ መቁረጥ:ወላዋይ መሆን:አለማመዛዘን ናቸው::እነዚህ የሰውን ድካም ሁሉ በከንቱ የሚያስቀሩ ናቸው::ስለዚህ እነዚህን ሁሉ በትዕግስት ድል ለመንሳት የእግዚአብሔር አጋዥነት ያስፈልጋል::

"ትዕግስት ያለው ሰው ለረጅም ጊዜ በመከራ ይጸናል:ተስፋ ያደርጋል ምህረትንም ያሳያል::"2ኛቆሮ2÷14

"በእግዚአቤሔርና በሰዎች ዘንድም ትዕግስት ነው::" ያዕ1÷4

"ትዕግስታቸውን ላጡ ሰዎች ወየላቸው?እግዚአብሔር በተመለሰባቸው ጊዜ ምን ያደርጉ ይሆን?በሰው እንጅ ከምንወድቅ በእግ/ር እጅ እንውደቅ " ሲራክ 2÷18

"እግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ:ሁሉንም የሚችል አምላክ እስትንፋስ ያስተምረኝል " ኢዮብ 33÷4

ከታገስን:-"እግ/ር ይቅርታ አድራጊ ነው:ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል::"መዝ 102÷6

"የእግ/ር ትዕዛዝ አስብ:መጻሕፍቱንም ሁልጊዜ አንብብ:እርሱም ልቡናህን ያጸናዋል" ሲራክ 16÷1

"ፈተናን ታግሶ የሚፀና ሰው የተባረከ ነው::ምክንያቱም እግ/ር በቃልኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የህይወት አክሊል ይቀበላል::" ያዕቆብ 1÷12

ስንፈተን "----ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ብሎ ይታገስ :: ፈል•3÷13

"------አምላኬ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለሆነ
ጠብቀኝ "ብለን እንታገስ:: መዝ•16÷1

በትዕግስት ወደኒ ጩሁ ይላል ጌታ
"ወደ እኔ ጮህ እኔም እሠማሀለሁ(እመለከተሀለሁ) አንተም የማታውቀውን ታምርና ታላቅ ሃይለኝ ነገር አደርግልሃለሁ"
ት/ኤር•33÷4

ካልታገስን "በአንድ ቦታ ላይ ፀጋይ ይበቃል ሃይሌ በድካም
ይፈፀማል "2ኛቆሮ 12÷9

ከታገስን "እኔ አለምን አሸንፈዋለሁ( አይዛችሁ)" ፈሊ•4÷6-10

እየታገስን "በቃልም ቢሆን ወይም በስራ የምታደርጎትን ሁሉ በጌታ ኢየሱስ ስም አድርጉት "አንተ ታቃለህ እንበለው::
ቀላስዮስ 3÷17

"ስለዚህ እንደ እግ/ር ፍቃድ መከራ የሚቀበሉ ሰዎች ሁለንተናቸውን ለታማኝ ፈጣሪ አደራ ሰጥተው መልካም ነገርን ከማድረግ አይቆጠብ "1ጴጥሮስ 4÷17-19

"አቤቱ አንተ አትጣላኝ አምላኬ ከእኔ አትራቅ " በለን እንታገስ::መዝ•37÷21

ፈተና ሲገጥመን:-"እግ/ር ይማረን ይባርከንም ፈተናም በላያችን ያብራ እኛም በሕይወት እንኑር "እንበል::
መዝ•66÷1

ከታገስን "እግ/ር እንደ ልብህ ይሰጥህ ፈቃድህንም ሁሉ
ይፈጽምልህ"መዝ•19÷4

"በእውነትህ ምራኝ አስተምራኝም አንተ አምላኬ መደሀኒቴ ነህና ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ " መዝ•24÷5

"ትዕግስት ታላቁን ሀጢያት ያስተሰርያልና የገዥ ቁጣ የተነሳብህ እንደሆነ ስፍራህን አትልቀቅ " መክብብ 11÷10

(ትዕግስትና ልቦና ያጣ ሰው ገንዘብን ያለ ውለታ ይጨርሳል::)

ወዳጄ:---"ትዕግስት አጥተህ"ግዜህ በከንቱ አታሳልፈው ዛሪን እንጅ ነገን አናቅም::ተዘጋጅቶ ለቅሶ የለም::በመልካም ስራ የእርሱን ቃል እናክብር የድንግል ማርያም ልጅ ይቅርባይ ነው::
-ለእኔም ለእናንተም ትግስቱን ይስጠን
-የእርሱን ቃል ለመተግበር ያብቃን:ቃሉ በእኞ ላይ ይደር
"እምነት ከትዕግስት ጋር ሲሆን ሁሉ መልካም ነው:የድንግል ማርያም ልጅ ልብ ይስጠን::)አሜን አሜን አሜን!!!
አሜን አሜን አሜን!!!

ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።ቃልኪዳን፤ጣባቂ ያላት ሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም የማትሆነው ቀድሞ የነበራች ከሁሉም የተለየች ሃገራችንን የቃልኪዳኑዋ አስራት ሃገር እምየ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አስታርቃን በሃገራችን ያለውን ርሃብ ጦርነቱን ታጥፋልን ህዝቦቿን ትጠብቅልን።አሜን!!!

== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...
አሜን!!!