Get Mystery Box with random crypto!

+++የኔታ አባ አክሊሉ በረከት እናግኝ share share share ይህ የሚያሰሩት የቅዱስ ራጉኤል | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

+++የኔታ አባ አክሊሉ በረከት እናግኝ share share share
ይህ የሚያሰሩት የቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስትያን በረከታቸው ይደርብን የመላዕኩን የቅዱስ ራጉኤል ቤት እንስራ በምዕመኑ ዕርዳታ እዚህ ደርሷል።ይህንን በማሰራት ላይ እያሉ ግንቦት12/2013 አረፉ።

ይህን የቅዱስ ራጉኤል ቤትን እንስራ?!
¶¶¶¶¶110ዓመት በላይ የሆኑ አባት[ አባ ሊቀ ሊቃውት የኔታ አክሊሉ ]የሚያሰሩት 'የቅዱስ ራጉኤል' ቤተክርስቲያን ነው።ይህን ቤተክርስቲያን በመስራት የአባታችን በረከት እናግኞ እንዲሁም ወደ መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል የምትሄዱ ምዕመን እኝህን አባት ያረፉት ግንቦት12/9/2013 ዘብር ገብርኤል ነው። በረከትም በማግኝት በመርዳትም ቤተክርስቲያኑ እንዲሰራ እናድርግ፤ ብዙ ምስጢር ያለው ቤተክርስቲያን ነው።
በተለይ ቅዱስ ራጉኤል ብዙ ቃልኪዳን ያደረገበት ቦታ መንዝ በገድሉም ይገልጸዋል፤ እንዲሁም የኔታ አባ አክሊሉ ይህ የሚሰራው የቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስተያን በመንዝ ማማ ከሞላሌ ከተማ ወደ ዘብር ገብርኤል ስንሄድ ከሞላሌ ከተማ 1ኪሜ እርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤እንዲሁም አባታችን እግዝአብሔር ከፈቀደልን መንዝ ማማ ፣መንዝ ላሎ፣ መንዝ ግሼ፣እና መንዝ ጌራ ፡አራት ቦታ እንዲተከል ተናግረዋል በመቃኞም ቢሆን ታቦቱን ያስገቡ ደርብ ግን አይሆንም ለመንዝም ለሸዋም ለኢትዮጵያም ጠባቂ ነው አራቱ ሐገር ቦታ ጋር ይተከል ብለዋል።

ሃሳባቸው ከእግዚአብሔር ጋር፤ መንዝ ማማ ሞላሌ የሚሰራው ይህ ቤተክርስቲያን እዚህ ደረጃ ሲደርስ ሌሎቹም የቀሩት 3ቱ ቤተክርስትያን እንዲሰሩ በመንዝ ውስጥ እግዝአብሔር የፈቀደላችው ቤቱን በመቃኞም ቢሆን ቢሰራ ቢተከል ጥሩ ነው ብለዋል።በመንዝ ላሉ የገባም ሲሆን በመንዝ ማማ ይህ የምታዩት ቤተክርስትያን አባ የጀመሩት ሲሆን ታቦቱንም አምጥተው በሞላሌ ቅድስት ስላሴ ይገኞል ተስርቶ እንዳለቀ ወደ ቤቱ ይገባል።

ይህ ቤተክርስቲያን ተሰርቶ እንዲያልቅ የበኩላችንን እንወጣ፤ በዚህ በድካም ግዜያቸው ነበር የሚሰሩት የኔታ አባ አክሊሉ በረከትና ምልጃ እናግኝ እንርዳ፤ ተሰርቶ አልቆ እንዲመረቅ እናብቃ ፤አደራ እላለሁ፤ በረከትም ነው፤ ለመርዳትም እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው፤መርዳት ለእግዚአብሔር ብድር ነው ዋጋ አለው።

ቤተክርስቲያኑን ለመርዳት
የቤተክርስያኑ ሂሳብ ቁጥር/Account

Account no~1000269882372
Account name ቅ/ራጉኤል ቤተክርስትያን ህ/አ/ኮሚቴ
Commercial Bank of Ethiopia /ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/

+++++{አባ ሊቀ ሊቃውት የኔታ አክሊሉ } ትውልዳቸው :-(መንዝ ላሎ ምድር ዘብር ገብርኤል) ሊቀ ሊቃውት የኔታ አባ አክሊሉ በጎንደር;በጎጃም በወሎ ካስተማሩ በኃላ በሀገራቸው/መንዝ ዘብር ለ54 ዓመት እያስተዳደሩ ;እያስተማሩ ከ60,000ሽህ በላይ ተማራ እና ሊቅ ያፈሩ ትልቅ አባት ናቸው ::

መንዝ አዲስ ሆነ ነባር ቤተክርስቲያ ተሰርተው ሲያልቁ በእርሳቸው እጅ ተባርኮ ተመርቆ ነው:ታቦቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ የሚገባው::
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሊቅነታቸው በአቃቃም;በድጋ;በመጸሐፍት;በቅኔ ትምህረት;60,000በላይ ተማሪ ያስተማሩ በእሳቸው እጅ ያልተማረ ከካሀን እስከ ጳጳሳት ብዙ ሊቃውንት ያፈሩ ማንኛውም ካህን አለቃ አክሊሉን ብጠይቁ ስለእርሳቸው ሊቅነት ይመሰክራሉ::

እኝህ አባት ለጵጵስና ተመርጠው መነኩሴ በገጠር በገዳም ነው፤ እንጅ የሚቀመጠው ብለው እንቢ ያሉ እንዲሁም ተማሬዎቼን ለማን ትቼ በማለት እንቢ ብለው ለቤተክርስቲያን የቆሙ ሊቅ ብዙ አገልጋዮቻን ለቤተክርስቲያናችን ያፈሩ አባት ነበሩ::

እድሜያቸው በውል ባይታወቅም እርሳቸው 110 ያልፈኛል ነበር የሚሉት : ከቤተክርስቲያናችን በጣም ሊቅ እና የበቁ ከሚባሉት ሊቀሊቃውንት አንድ ነበሩ::
የትም ቦታ ያለ ሊቅ ወይም ካህን የየኔታ አክሊሉን ስም ዝና የማያቅ የለም::
በጣም የበቁ አባት የሚያሳዝኑ ትሁት እራሳቸው በጣም ዘቅ የሚያረጉ አባት ነበሩ::አንደበታችው ይገርማል;ያነባሉ ፈደል እንኳን ብንሳሳት ያርሙናል ፤በዚህ እድሜያቸው እራሳቸውን ችለው ነበር የሚሄዱት በጣም ነው የሚያስገርሙት ።/በመንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤልን ለ 54አመት ያስተዳደሩ/ትልቅ አባት ናቸው::
+ ላደለው የ እሳቸውን ጸሎት ብራኪ ያገኝ የታደለ ነው::
+ ያስገርማሉ ማንነታችን ፈላጎታችን ሊነግሩን ይችላሉ ላደለው::ለሀገራችን ለህዝባችን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሳታሳየኝ አትግደለኝ ጌታ ነው የሚሉት:: በረከታቸው ጸሎታቸው ይርዳን ይሁንልን ይደረግልን! አሜን!

[የቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስትያን] ቦታው~ሰሜን ሸዋ መንዝ ማማ ሞላሌ ከአ/አ 255ኪሜ ሞላሌ ከተማ እንደደረስን፤ከሞላሌ ከተማ ወደ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መንገድ ላይ ከሞላሌ 1ኪሜ ላይ የሚገኝ በመሰራት ላይ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው።

[የኔታ አባ አክሊሉ ]ግንቦት12/9/2013 አረፉ።

=== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like

+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431

+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME

+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme

+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5

+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
+++Facebook page
አናዥጋ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ገዳም +Johnny akeme/ዮሐንስ አለመ/
https://www.facebook.com/አናዥጋ-ቅዱስ-እግዚአብሔር-አብ-ገዳም-Johnny-alemeዮሐንስ-አለመ-105994748632235/

+++facebook page
ግፍት ቅድስት ማርያም ገዳም +Johnny aleme/ዮሐንስ አለመ/
https://www.facebook.com/pg/%E1%8C%8D%E1%8D%8D%E1%89%B5-%E1%89%85%E1%8B%B5%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D-%E1%8C%88%E1%8B%B3%E1%88%9D-Johnny-Aleme%E1%8B%AE%E1%88%90%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%98-100618749180538/community/

የሄደ ሁሉ በጻድቁ አባታችን መስቀላቸውና መቋሚያቸው ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ!አሜን!!!!
Share በረከት እናግኛ፦ንገሩ አሳውቁ የሰው ልጅ ይዳን Share Share Share!

[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ /መዘዞ ከተማ/ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ 2ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ
እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም ያስኪዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን!