Get Mystery Box with random crypto!

share share share ምስክርነት! ++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

share share share ምስክርነት!
++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን
"አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
=ሰላም ጆኒ እንደምን አለህ ምስክርነት ለመስጠት ነበር
፥ ስቶቭ ተበላሽቶብን እንዲሰራ ረድተውኛል
፥ የኩላሊት ኢንፌክሽን በጣም ታምሜ ለሶስት ቀን ፀበላቸውን ጠጥቼ ፈውሰውኛል ሌሎችም የጠየኳቸው ነገሮች ነበሩ ፈተውልኛል በሂደት ላይ ያሉ ነገሮችም አሉ በጣም የሚያስጨንቁኝም ነገሮችም አሉ መጨረሻውን አሳምረው ደግሞ ለመመስከር እንደሚያበቁኝ አምናለሁ ምንም ነገር ጠይቄ አሳፍረውኝ አያውቁም እግዚአብሔር ይመስገን ምስጋና ይሁን ለአጋዝዕተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ የአናዥጋው ቅዱስ እግዚአብሔር አብን መድሀኒአለምን አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሀንስን እናታችን ግፋት ማርያምን ሰሚነሽ ኪዳነምህረትን እናታችን ቅድስት አርሴማን ልደታ ማርያምን ቅዱስ ጊዮርጊስን አቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ዮሀንስን ኤረር ባታ ማርያምን ፀበለ ማርያምን ጌቴሴማኒ ማርያምን ቅዱስ ገብርኤልን ቅዱስ ሚካኤልን እና እናታችን ታቦር ማርያምን አመስግኑልኝ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን አንተም ጆኒ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅህ

=Endemin ameshachu ye egziabher beteseboch. Kguwadegnaye gar tinish tekeyayien tezegagten neber ahun tarkenal. Tsadkun amesginuligni. Hulu gize siterachew simatsenachew yemautewugni abate ahunim yegodelwin yimulilugni lemisikirinet yabkugni.

=በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሰላም ነህ ወንድም አብነ እጨጌ ዮሀንስ የሰጠን አምላከ ቅዱሳን መድሀኒያለም ክብር ምስጋና ይግባው እጨጌ የረጉልኝ ነገር ቆጥሬ አንዘልቀውም ሰሞኑን በቀኝ እነበግራ ጎኔ አያያመኝ ተቸግሬ ነበር ማታ በፃዱቁ ስዕል አድኖ ተደባብሼ ተኝቼ በጣም ደህና ነኝ ፃዲቁ ካለብኝ ፈተና ያላቁሽ በሉኝ አባቴ አብነ አጨጌ ዮሐንስና የአዥጋው ቅድስ እግዚአብሔር አብ ይድረሱልኝ አሜን

=በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ምስክርነት ለመስጠት ነበር እጅግ እጅግ እጅግ በጣም በተደጋጋሚ ጊዜ አብነ እጨጌ ዩሐንስን ካወኳቸዉ ጀምሮ የሚደረግልኝ ብዙ ነዉ በጣም ቡዙ ጊዜ ምስክርነት ሰጥቻለሁ ሰሞኑን የአንጋዥ አብነ እግዚአብሔር አብ የንግሳቸዉን ምስሎች በፎቶ እያየሁ ወደ ሥራ እየሄድኩ ነበር እና ራሴን; ጆሮዬን እግሬ እደዉ ስዉነቴን በሙሉ በጠቅላላ ጥሩ ስሜት የለኝም እና ፔሬድም ሊመጣ ትንሽ ምልክት እያየሁ ነበር እና እባኮን አንጋዥ አብነ እግዚአብሔር አብ ዳብሱኝ ድረሱልኝ ፔሬዴም እዲመጣ አልፈልግም እና ያዙልኝ አልኳቸዉ ሞስክርነዎቱን በፍጥነት እሰጣለሁ ማሩኝ አልኳቸዉ እግዚአብሔር ይመሰገን ደህና ነኝ ፔረድም አልወረደም በጣም ደህና ነዉ ራሴንጆሮዬን የተወሰነ ያመኛ ጨርሰዉ እደሚምሩኝ አልጠራጠርም ክብርምስጋናለአንጋዥ አብነእግዚአብሔር ይድረስ ፍቅርተ መድህን አብነ እጨጌም በጤናዬም በሁሉም ነገር ስጠራቸወዉ ይደርሱልኛል ሠሞኑንኮምፒተር አልሠራ ብሎ አደራዎ ይርዱልኝ ብያቸዉ ትንሽ ቆይቶ ቻርጅ አደረ ተመስገን ክብር ምስጋና ይግባቸወዉ ሁሌም አመሠግናቸዋለሀሉ ንግስቲቱ አዛኜ እናቴ እመብርሃን ሁልጊዜ ሁል ጊዜ ከእኔ ጋር ናት አመሰግናታሁ ፈጠራዬ የዓለም ገዢ መድህኔ ክብር ምስጋና ይግባዉ ሁሉም ቅድሳን ሰማዕታት መላዕክት ሠዋሪያትክብር ይግባቸዉ መጨረሻዬን ያሳምሩልኝ ለሥጋዉለደሙ ያብቃን !

=ሰላም ጆኒ አለም አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ያደረጉልኝ ታአምር ነው። በምሰራበት መስሪያ ቤት በተፈጠረ ስህተት በራሴ ችግር ምክንያት 47,ዐዐዐ ብር እንድከፍል ተወሰነብኝ። ከዚያ በኋላ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሀንስን ከዚህ ጭንቅ እንዲያወጡኝና ገንዘብ አግኝቼ እዳዬን ላበደሩኝ አንደከፍል ተማፀንኩ። ይሀዉ አሁን ገንዘብ አግኝቼ ዕዳዬን ላበደሩኝ ሰዎች ሁሉ መልሼ እፏይ ብያለሁ(የሰው ገንዘብ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅ ታውቁታላችሁ)። እልልልልልልልል አመስግኑልኝ እናታችንን እና አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሀንስን።
ሌላው ከአዲስ አበባ ወጥቼ ነበር በሰላም ደርሼ እንድመጣና በመንገዴ እንዲጠብቁኝ ተማፀንኳቸው በሰላም ወደ ቤቴ መልሰውኛል።
ሌላም እንግዲ የለመንኳቸው ነገር አለ እንደሚያስተካክሉልኝ እርግጠኛ ነኝ። በድጋሜ ደግሞ ገዳማቸውን ለመርገጥና ለመመስከር ያብቃኝ።
ሌሎቻችሁም በሚገጥማችሁ ችግር ባለመጠራጠር ጠይቆቸው መልሳቸው ፈጣን ነው ፃድቁ አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ እልልልልል

=ሰላም ወንድሜ ዩሐንስ እንደምን አለህ። አባታችን ያደረጉልኝን ለመመስከር ነበር። ዛሬ ፈተና ነበረብኝ አባቴ እረድተውኛል ጥሩ ሰርቻለው።እግዚአብሔር ይመስገን አንድ የጠየኳቸው ነገር ነበር አድርገውልኛል። አባቴ አቡነ እጨጌ ዩሐንስ ይመስገኑ።እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመስገን። አደራ መስክርልኝ

ገዳሙ ጉዞ አዘጋጅቷል ሰሜንሸዋ መንዝ መዘዞ(ጠገሮ)
+++++(መዘዞ)አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ++++ ጉዞ 28\29/1/2015ተዘጋጅቷል።
መነሻ፦መስከረም28
መመለሻ፦መስከረም 29 ተባርከን መመለስ።
ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
የሄደ ሁሉ በጻድቁ አባታችን መስቀላቸውና መቋሚያቸው ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ!አሜን!!!!
Share በረከት እናግኛ፦ንገሩ አሳውቁ የሰው ልጅ ይዳን Share Share Share!
[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ /መዘዞ ከተማ/ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ 2ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ
እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም ያስኪዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን