Get Mystery Box with random crypto!

share share [ግፍት ቅድስት ማርያም]፦ እንኳን ግፍት ማርያም ብለን ተማጽነናት ቀርቶ የተዘራ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

share share [ግፍት ቅድስት ማርያም]፦ እንኳን ግፍት ማርያም ብለን ተማጽነናት ቀርቶ የተዘራው ሁሉ የሚበቅልበት ገዳም ነው። ንገሯት ተሳሉ። ለምስክርነት ታብቃችሁ። አሜን!

በገዳሟ አካባቢ የተዘራወ ሁሉ ይበቅላል።

*ጉዞ ንግስ መስከረም20 ወደ ቅድስት ግፍት ማርያም ስንሄድ ዋሻ ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል ገብኝተን ተባርከ ጉዞ ወደ ግፍት ቅድስት ማርያም ይሆናል በ21 አንግሰን ተባርከን መመለስ።
ለበለጠ መረጃ~
~0911190212
~0911481388
~ 0901002929

/መንዝና ተጉለት /ግፍት ቅድስት ማርያም ገዳም"
~እናቴ ገዳሟን ሲረግጡ በሃሴት በደስታ የሚሞሉበት ሰሚ በዐለት ሰለት ሰሚዋ በ11 ክ/ዘመን የተመሰረተችው ስለት ሰሚዋ የሰለቷ መልስ የምንገረምባት ቁጡም ናት ገና ደጅዋን ሲረገጧት ሙሉ በሃሴት በደስታ የሚሞሉበት ዳግማዊ ግሸን የምትባለው ቦታውም ገዳሙ አካባቢውም በተራራው ጫፍ ላይ ያለች መግቢዋ አንድ በር የሆነ ሁሉ ነገሩ የቦታው ነገር ግሼ ማርያም የረገጡ ያሉ ነው የሚመስለው

•••••••••••በንብ የምትጠበቀው
+++ከገነት/ምድረ መዓዛ/ የመጣች ታቦት ናት
~~~~ጥንት ታቦቷ የመጣችበት /ምድረ መዓዛ/ከሚባል ቦታ መጥታ ታቦቷ በድንኳን ሆኖ ቤተልሄሟን ሰርተው ከዚያም በዚህ ቦታ ቤተክርስትያኖ በሳር ቤት ተሰርቶ ቤተክርስቲያኖዋ ተቃጥሎ የቤተክርስቲያኗ ጉልላት እንስራው መሬት ወድቆ ምንም ሳይሰበር የሚገኞበት ገዳም ነው ከዚያም 1977ዓም ጣሪያው በቆርቆሮ ተለወጠ። ቤተልሔም ግን እስከ አሁን ሳርቤት ነው።

~ቤተክርስያና እሳት በድንገት ተነስቶ ንብ ጉልላቷ ላይ፤ በገዳም አጠድ ላይ በዛፏት ላይ፤ በእድሞዕ በርላይ፤ ንብ አለ።

ድንገት እሳት ተነስቶ ቤተክርስቲያኖዋ ልትቃጠል ስትል ንቦቹ ከአሉበት ስነሱ እሳቱ ጠፋ
~ለእርሻ ያቀጠሉት እሳት ድንገት እንደ ሰደድ እሳት ተነስቶ እሳቱ ቤተክርስቲያኑ ግቢ ገባ ቦተዋ እንደ ግሸን ማርያም ናት መውጨዋ መግቢዋ አንድ ነው በአካባቢዋ ሰው ህዝብ የለም እሳቱን በምን ያጥፉት የነበሩትም ያላቸው አንድ እንስራ ውሃ ብቻ ነበር፤ ያን አንድ እንስራ ውሃ እሳቱንለማጥፉት ጉልላቱ ላየ አውጥተው ውሃን ደፍተው እሳቱን ሊያጠፋ ሲሉ እንስራው ከጉልላቱ አምልጣቸው/ከጣራው/መሬት ሲወድቅ እንስራው ሳይሰበር መሬት ወደቀ እሳቱም ጠፋ
~~~ሌቦች ታቦቷን ሊሰርቁ ገብተው ቤተክርስቲያኑ ግርግዳ አጣብቃ አጣማቸው ተገኘተዋል
~~~ገዳሟ ያለችበት ተራራው በማዕድን የተከበበ ነው ሲሆን ቤተክርስትያኖ ገዳሙ ያለበት ተራራ ማዕድኑን ሊቆፍሩ የሚገቡት ሁሉ ማዕድኑ እየተደረመሰ የሚቆፍረው ሁሉ ያልቃል ይደረመስብታል በጣም ቁጡ ሰለት ሰሚ ናት
~ቤተክርስትያኖዋ ገዳሟ የሚያገለግሉ 48ካህናት 8መርጌታ የሚገኝባት አስደናቂ ጥንታዊ ገዳም ስትሆን የወር ደሞዛቸው [80ብር] ነው ስለ ማርያም ደሞዛቸው እናግዝ ገዳሟ የባንክ አካውንት እንደከፈተች የበኩላችን እናድርግ ቤተክርስቲያን ቢፈርስ ቤተክርስቲያን ይሰራል። አገልጋይ የሌለበት ቤተክርስቲያን ግን ይዘጋል እናስብበት።

~~~ ገዳሟ ብዙ ቅርስ ይዛ ከአካባቢው ተወላጅ በስተቀር አጋዥ የላትም እናግዛቸው ቤቷን እንስራ የፈቀደችላችሁ ገዳሟ የባንክ አካውንት
ገዳሟ እርዳታ የሚያስፈልጋት
_ለአጥር
_ለአብነት ትምህርት ቤት
~48ካህናት 8መርጌታ ከዲያቆናት ውጭ ደሞዛቸው በአመት 80ብር ነው ደሞዛቸው እንዲስተካከል የበኩላችንን እንወጣ

Account no-1000079766888ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(Commercial Bank of Ethiopia)
Account name-ግፍት ደብረምህረት ቅድስት ማርያም(Gefet Debre mihret kidist mariyam)
SWIFT CODE-CBETETAA

ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፣ስለዚህ ነፍሴ
ፈለገቻቸው"መዝ•118/119÷129
-ዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት ይወስዳል።
ማቴ 10፥41
-እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል። ማቴ 10፥40
- እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።
ዮሐ 9፥12
-"ቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው"
መዝ 15÷3
-"እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ "
መዝ 4÷3
-"የጻድቅ ሰው ስራ ለዘልዓለም ጸንቶ ይኖራል "
መዝ 111÷7
-"እኔ እግዜአብሔር አምላካችሁ ቅድስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ"
ዘሌ•19÷2
-"ከአገርህ ውጣ ከአባትህ ቤት ከዘመዶችህ ተለይተህ እኔ ወደ ማሳይህ ምድር ሂድ " ኦሪት ዘፍ 12
/ቅዱሳን በአፀደ ነፍስ ያማልዳሉ/
-ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኃላ ከዚያ ጊዜ ከስጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ:: ኢዮብ 19÷26
/በዳዊት አማላጅነት ከተማዋ ከመጥፋ ትድናለች::/
-በ ዕድሜህ ላይ 15አመት እጨምራለሁ አንተና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ ስለ እኔም ስለ ባርያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ " 2ነገስት 20÷6
-ከሰማይም ከእንግዲህ ወዲህ በጌታችን የሚሞቱ ሙታን ብፁአን ናቸው::መንፈስ አዎን ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል:: ራዕይ ዮሐ 10÷1
-የአለም ብርሃን ናችሁ!
-ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን 1ቆሮ6፥2
-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።
መዝ 88(89)፥3
- እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴ 10፥40-42
የቅድሳን ጸሎት (ምልጃ ) በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በቂ ማስረጃ ነው::
የምትከብረው/ንግስ ያለው/መስከረም21 ህዳር21 ጥር21 እና ግንቦት 21 ነው