Get Mystery Box with random crypto!

፨፨ምስክርነት! ++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨፨ምስክርነት!
++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን
"አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
፨እልልልልልልልልል
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። ፃዲቁን ካወኳቸው ጀምሮ ብዙ ተደረገልኝ ተመስገን ።ዛሬ በ6/12/2014 የወር አበባዬ ለ2ወር ሳይመጣ ቀረ እርግዝና እንዳልሆነ አውቃለሁ ሆስፒታል ማህፀኔን ልመረመር ሄድኩኝ እጢ ያሳያል ተባለኩ እና ሌላ ተጨማሪ ብዙ አይነት ምርመራ ታዘዘልኝ ለአቡነ እጨጌ ከምንም በሽታ ነፃ ሆኘ እጢ የተባለውም በመድሀኒት የሚጠፋ ቀላል ይሁንልኝ ብዬ ነገርኳቸው ሰሙኝ ተደረገልኝም ተመስገን። ክብር ለቅዱስ ኡራኤል, ክብር ለአቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ ይሁን። ክብር ለቅዱስ መርቀሪዎስ ይሁን። የአቡነ እጨጌ ዩሐንስ አምላክ ይመስገን። ክብር ለቅዱስ ሚካኤል አምላክ ይሁን። ክብር ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ። ተመስገን።ክብር ለድንግል ማርያም ልጅ ይሁን። እናቴ የኔ በረከቴ ጌጤ... ድንግልዬ እማዬ ተመስገኝልኝ።ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም። አለማትን ሰላም ያድርግልን።

፨Joney endet senbtk?ወ/ማርያም እባላለሁ አንዳንዴ ሁሉም ይገርመኛል መዳህኒያለም ልጆቹን ለማዳን በዙሪያችን የሚይገራርሙ የሚያስደምሙ ብቻ ለኛ ለሰው ልጆች ሳይገባል በረከታቸው እንዲ ሰጠን ይጠብቀናል እናም አቡነ ጨጌ አባቴ ብዙነገር አማክሪዋለሁ አጠገቤ ሁኖ እንደሚሰማኝ አቅፎ አይዞሽ እንደሚለኝ በእምነት ነገሬዋለሁ እናም በተሰጠው ቃልኪዳን ለኔም መልስ ነገሮኛል እና ሌሎችንም ችግሮቸን በጊዜው በስአቱ እንደሚያስወግድለኝ ባለ ሙሉ ተስፍ ነኝ፣ሁሌም እንዲጠብቁኝ ጎዶሎየን እኔ ሳላየው እነሱ ያይሉኛልና እግዚያብሄር ይመስገን ። ዛሬም ነገም በሂወታችን እንዲጠብቁን ዮሃንስ ንገርልኝ ፣እኔ ብዙ ማውራት መዘርዘር አልችልም፣አሞኝ መፍትሄ አግኝቻለሁ፣ተጨንቄ መልስ አግኝቻለሁ ፣ስለጎደኞቸ ቤተሰቦቸ ደርሰውልኛል፣ስራ አጥቸ አግኝቻለሁ እናም ስለተደረገልኝ ነገረም ወደፊት ስለሚሆነውም እግዚያብሄር ይመስገን!!

፨ሰላም jonney እንዴት ነህ 2 እህቶቼ ተጣልተው ተዘጋግተው ነበር እኔም ለእመቤቴ እና ለአባቴ አቡነ እጪጊ ዩሀንስ አልቅሼ ነገርኮቸው እመቤቴ እና አባቴ ፀሎቴን ሰምተው ተታርቀዎል 2, በሰራ ጉዳይ ያሳሰበኝ ነገር ነበር አባቴ ፀሎቴን ሰምተው አንዱን አስተካክለውልኛል ሌላውንም በቸርነታቸው እንደሚያስተካክሉ አምናለው ለእመቤቴ ለአባቴ ክብር ምስጋና ይድረሳቸው እሳቸውን የሰጠን አምላክ ይክበር ይመስገን

፨ፀጋሕ ይብዛ ወንድሜ ለመመሥከር ነበር ትናንት ማታ ሆዴን ቁርጠት አሞኝ ነበርእና ለሠሜነሸ ኪዳነምህረት ለቅዱሥ ሚካኤል ለቅዱሥ ሩፋኤል ለአባቴ አቡነ ጨጌ ዮሐንሥ ነገርኋቸሁ ደነሁኝ ክብርመሥጋና ይድረሣቸወ

፨~በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! ምስክርነት ለመስጠትነው

** አምላከ አቡነ እጨጌ ዬሀንስ ምስጋና ይድረሰው ? ?

1ኛ - የበር ቁልፍ ጠፋብ ቢፈለግ ጠፋ::
አባቴ አቡነ እጨጌ ዬሀንስ ፃዲቁ እርዱኝ አልኳቸው የማይሆን ………ያልነበርኩበት ያላስቀመጥኩት ቦታ አገኸሁት::
አባቴን ፃዲቁን አመስግኑልኝ ደረሱልኝ

2ኛ - የወንድሜ ልጅ ከእንቅልፉ ከነቃ በኃላ ፈዘዘ ምን ሆነ ብለን ስናገላብጠው አይሰማም አይለማም ፀጥ ፀጥ አለ አይተነፍስም የፃዲቁን ፀበል አደረግንለት::
ሆስፒታል ወሰድነው እየሄድን መንገድ ላይ ነቃ አሁን ኖርማል ሆነ ግን በጣም ለሁላችንንም እንቆቅልሽ ነው የሆነብን ሃኪሞቹም በጣም ገርሟቸዋል ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም ተመስጌን ጌታዬ ተርፎልናል ! አምላከ አቡነ እጨጌ ክብርና ምስጋና ይግባው! አመስግኑልኝ

፨Selam yegezabear beteseboch welete mariyam ebalalew betam tecenekea neber ecegea yohanes abatean deresulegn beyea meselacewen eyayew lemenkuachew ande ken sayader fesemulegn lenea endederesu lenatem yederesulachu

፨እንደምን ከረምክ ጆኒ አባቴ ያደረጉልኝ ለመመስከር ነው አንደኛዋ ልጄ የታይሮይድ መድሀኒት በየቀኑ ትወስዳለች እና ሀኪም ቤት በየሁለት ወሩ ቼክ አፕ ትሄዳለች እና ባለፈ ስትሄድ ለዛሬ የደም ዉጤት እና አልትራሳውንድ ተነስተሽ አምጪ ብሏት ነበር እና እኔም አባቴ የደሟንም የእልትራሳውንዱንም ውጤት ጥሩ አድርገው ይህን በየቀኑ የምትወስደውን መድሀኒት አስቀሩልኝ ብየ አንገታን እምነታቸውን እየተቀባች ለምኛቸው ነበር ይሄው ዛሬ ስንሄድ ለግዜው መድሀኒቱን አቁሚውና የዛሬ ወር ከንደገና እናየዋለን አላት አባቴን እጨጌ ዮሐንስን ቃጥላ ማርይምን መጥምቀ መለኮት ቅድስ ዮሐንስን አመስግኑልኝ እስከመጨረሻው አድነዋት ከመድሀኒት እንዲገላግላት ጸልዩልኝ ስለቱንም በአካውንት አስገባለው መስክርልኝ አደራ ወንድሜ እባታችንን የስጠን አምላክ ይክበር ይመስገን

፨በስመአብ ወወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
እንዴት ነህ ጆኒ አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ያደረጉልኝ ድንቅ ተአምር ለመመስከር ነበር
1 የምኖረው ከኢትዮጲያ ውጪ ነው ወደ ሀገር ቤት ስመጣ የአባታችንን አመታዊ ክብረ በአል ውስጥ ገብቸ ለማክበር በጣም ጏጉቸ ስለነበር ለአባቴ እባኮትን እርዱኝ ብየ አልቅሽ ነገርኳቸው ክብር ምስጋና ይግባቸው የኔን የአጥያተኛዋን ልመና ስምተውኝ በክብር ፀበላቸውን ተጠምቄ በአላቸን
አከበርኩኝ
2 ወንድሜ መጠጥ ይጠጣል አባቴን እባኳት ይህንን ነገር አንሱለት ብየ ፀለይኩኝ እናም ፀበላቸውን ለ7 ቀን ተጠመቀ አሁን ከንግዲህ መጠጥ የሚባል አልጠጣም አለኝ ሳምንት ሆኖታል ጠጥቶ አያውቅም አባቴ እስከመጨረሻው እንዲያስጠሉት ፀልዩልኝ
ሌላም ብዙ የነገርኳቸው ነገር አለ ሁሉንም እንደሚያስተካክሉልኝ እምናለሁ
3 እናቴ ያማታል አባቴን ፀበል ተጠምቃ ለውጥ አላት
እኔን የስሙኝ አባቴ እናንተንም ይስሟችው
አባታችንን የስጠን የድንግል ማርያም ልጅ ይክበር ይመስገ
አሜን አሜን አሜን

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
ሰላም ወንድሜ ዮሀንስ እንዴት ነህ ... እባክህን ይሄን ምስክርነት አድርስልኝ

አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሀንስ በጨነቀኝ ሰአት ሁሉ እንደደረሱልኝ ነው እናም ደጃቸው መጥቼ ሰው ያስፈልገኛልና የኔ የምለው ሰው እንዳገኝ እርዱኝ ብዬ ለመንኳቸው እሳቸውም አላሳፈሩኝም እረድተውኛል እስከመጨረሻው እንዲፀናልኝም አማላጅነታቸው አይለየኝ አሜን!

፨Hi Johnny, tikit negerochen lememesker new.

1. Wendeme aynun amot be abatachen siel aynun ashehulet ena ke sira befitm kebet siweta sielachewen eyetesaleme eyeweta bemigerm fitnet aynu lewt alew.

2. Ye abate mekina tegelbeto shuferun endiadnut ena ye insurance gudayem endialkelet le abate teyekiachew be teamer yan kemesele mekina adega adelem sew Mnem yiterfal bemaybalebet adega wust shuferum ya 1 guday yale kusel enkuan dinual. Ye insurance gudayem tiru eyehede new. Egziabher amlak be tiru endemichereselenem amnalehu.