Get Mystery Box with random crypto!

በሰመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ። ሰላም ጆኒ ስሜ መስቀልክብራ (የምስራች) | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

በሰመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ። ሰላም ጆኒ ስሜ መስቀልክብራ (የምስራች) ይባላል እግዚአብሔር ለዚህ ቀን ይህ የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ምለጃ ስለተደረገለት የጓደኛዬ ልጅ 10አመት ነው በጠና ታሞ ኩላሊቱ መታጠብ አለበት ተብሎ ይነገረዋል ከዛ እኔ በትንሽ ያባታችን ጸበል ሰጠኋት ለእናቱ አባቴም አላሳፈሩኝም ልጁ ምንም እደማያስፈልገው ተነገረው እኔም ይህን ተአምር ለመመሰከር ስላበቃኝ በአውነት እግዚአብሔር ሁልጊዜ የተመሰገነ ይሁን። አቡነ እጨጌ ዮሐንስ የለመንኩዋቸው ብዙ አለ ከለመንኳቸው ውሰጥ አንዱ ሆኖልኛል። ለ 7ቀን ጸበላቸውን ጠጥቼ በሚገርም ፍጥነት ድኛለሁ። እግዚአብሔር አምላክ እሳቸውን የሰጠን በውነቱ ይክበር ይመስገን። አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በእውነቱ የተመሰገኑ ይሁኑ ልመናዬን ሰምተው ለመመስከር ስላበቁኝ አመሰግናለሁ። ለደጆትም ለምስጋና እድመጣ አብቁኝ። ሌሎቹ የለመንኮትን አደራ አለ እዳይረሱኝ ፈጥነው ያማልዱኝ። ሀገራችንን ሰላሟን አሰጥሉን አደራ አባታችን።
ጆኒ አንተም እግዚአብሔር ባለህበት ሁልጊዜ ይጠብቅህ። አመሰግናለሁ