Get Mystery Box with random crypto!

አበጅተው ጭንቀቴን አስወግደውልኛል 10 ፃድቁን የለመንኳቸው ነገሮች ልመናዬን ሰምተውኛል 11 ለረጅ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

አበጅተው ጭንቀቴን አስወግደውልኛል 10 ፃድቁን የለመንኳቸው ነገሮች ልመናዬን ሰምተውኛል 11 ለረጅም ግዜ ከተራራቅን እህቴ ጋር ፃድቁ አገናኝተውኛል የምፈልገውና የምመኘው ሆኖልኛል 12 አንድ የምገዛው ዕቃ ነበረ ፃድቁ ጥሩ አድርገውልኛል ደስ የሚል ሰላማዊ የሆነ ቀንም እንዳሳልፍ አድርገውኛል 13 ሌሊት እያቃዠኝ በጣም ተቸግሬ ፃድቁን በተደጋጋሚ ለምኛቸው አሁን ደህና ሆኛለው ከፈራሁትም ጠብቀውኛል 14 የትምህርት ሰዓት እየረፈደብኝ ሁሌም ቢሆን ፃድቁን እየተማፀንኩ ያሉትንም ችግሮች እያስተካከሉልኝ በሰዓቴ ነው የምደርሰው ልመናዬን ይሰሙኛል 15 ለቀናት በተደጋጋሚ እያሳለኝ መተንፈስ እያቃተኝ እንቅልፍም አልወስድ እያለኝ ነበር የፃድቁን መልክአ ይዤ እየተኛው ሰላም ያለው እንቅልፍ እየተኛው ነበር ፃድቁ ፈውሰውኛል 16 ፃድቁን የጠየቅኳቸው ነገር ነበረ ሊሳካልኝ ጫፍ ደርሷል 17 ምግብ በደንብ አልበላም ነበረ የምግብ ፍላጎት ጭራሽ አልነበረኝም ነበረ ፃድቁን ለምኜ በደንብ እየተመገብኩ ትልቅ ለውጥ ነበረኝ ስዕለቴን ባለማስገባቴና ባለመመስከሬ ትንሽ ፍላጎቴ ቀንሷል ፃድቁ ይቅር ይበሉኝ 18 ፃድቁን ቤት ውስጥ እንዳልቀመጥ የሆነ ነገር እንዳደርግ አርጉኝ ብያቸው ነበረ ልመናዬን ሰምተው ተደውሎ ያቋረጥኩትን ስራ እንድጀምር ተነግሮኛል ሌላም ተጨማሪ ነገር እንዳደርግ ፃድቁ እየረዱኝ ነው 19 ፃድቁን በልቤ የጠየቅኳቸው 3 ነገሮች ነበሩ ልመናዬን ሰምተውኛል 20 ብዙ ዕቃዎች ሰው ጋራ ነበረኝ ፃድቁን ለምኜ በአስቸኳይ ተመልሶልኛል ገንዘብም ጠፍቶኝ ነበረ ፃድቁን ለምኜ አግኝቼዋለው 21 ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ የተሳሳተ ሰፈር ሄጄ ፃድቁን ለምኜ የወሰደኝ ሹፌር ሊመልሰኝ ችሏል መሃል መንገድ ላይም አንገራግሮ ነበረ ፃድቁን አደራ ብዬ ሊያደርሰኝ ችሏል ከተጨማሪ ወጪም ድኛለው ክብር ለፃድቁ ይሁን 22 አንድ ማግኘት የነበረብኝ ሰውና ማስፈፀም የነበረብን ጉዳይ ነበረ ፃድቁን ለምኜ ያን ሰው እንዳገኘውና ጉዳዩንም እንድንጀምር አድርገውኛል 23 ፃድቁ ሁሌም በምለምናቸው በምጠራቸው ሰዓት ፈጥነው ይደርሱልኛል ፃድቁን አመስግኑልኝ እባክህ ወንድሜ መስክርልኝ

~Selam Johnny miskerenet lemestet naw,
Ketwesen geze befet yabune Echege yemelkea tselot metsehafachew teftobegn magegnet alchalkuem neber ena betam azegna neber ena letsadiku tematsegnachew neber ena telatena kesenet gize behwala agegewet. Hulun yarege Yabune Echege Amlak Egizhabher kenenatu ena Tsadiku yemesgenu

~Yesadiku abaten teamr zarem lememesker new sebelachewn setche teamr yaltederegelet yelm. Ahunm guadegnaye erguznat leketero hospital hida andit nefsetur set techenka staleks mnhunesh new stlat dem eyefesesegni ena mahsenishilay siga teletatfal tebiye. Ene muslim negni gin ye kidisu mikaelna ye tekliye sebel teiche demo komo neber endegena gi mefses jemere zare docteru cancer sayihonibidhi ayikerim bilogn techenke tilatalech keza guadegnaye ney yabune chrge sebel enisetishalen esachew yadnudhsl bilat yizat metach sebelachewun setenat wrdiyawe demua kome yecancerun mrmeram adrga nesa nesh tebalech mahsen lay yalewm sga yelem ahun esam sindum beselam nachew enam yichi muslim ehitachin kechaliku be hamle guzu kalchilku degmo welje hije emesekiralehu eskezaw gin yenantem selot ayilryegni bilalechi kinir misgana le abatachin

~ጆኒ እንዴት ነህ ወለተ ሐና እባላለሁ አባቴ አቡነ እጨጌ በየእለቱ በየሰዓቱ በጠራኋቸው ጊዜ ሁሉ ፈጥነው ይደርሱልኛል።ክብር ምስጋና ይድረሳቸው። ምስክርነት ለመስጠት ነው እባክህ ጆኒ መስክርልኝ።
ባለፈው ሐምሌ 2/3 በነበረው ጉዞ ተሳታፊ ነበርኩ በወቅቱም አባታችን ያደረጉልኝን ነገር መስክሬ ነበር ነገር ግን የተደረገልኝን ትልቅ ነገር ሳልመሠክር በመቅረቴ ድጋሜ ተከሰተ ይኸውም ቢሮ ያለ ልጅ በፍጹም አይታዘዝም ፣ስራ ያበላሻል ፣ ያናድደኛል እንጣላለን ለአባቴ አቡነ እጨጌ እርሶ አስተካክሉልኝ እንዲታዘዝ አድርጉልኝ በሰላም እንድንሰራ አስታርቁን ብዬ ሰላም ሆኖ ነበር እዛ ደርሼ ሳልመሠክር በመምጣቴ በጣም ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ገባሁ።
በተጨማሪም ደህና የተወኝን ስለመጥፎ ንግግሩ፣ ድርጊቱ ቀኑን ሙሉ እያሰብኩ መጨነቅና ደስታ መራቅ ባለመመስከሬ ተመልሶ መጣብኝ በጣም ተረበሽኩ አባቴ ባለመመስከሬ ነውና ይቅር በሉኝ አሁንም እርሶ ከእመቤቴ ድንግል ማርያም ጋር ኑልኝ እርዱኝ ተቋሙን ምሩት፣ አስተካክሉልኝ አቅም የለኝም አልኳቸው ጉዳዩን ለመፍታት በጠራሁት ስብሰባ ላይ ተገኙ ብዬ መልካቸውን ጡት ማስያዣዬ ውስጥ አድርጌ ስብሰባ ገባሁ ስብሰባው ከአንድ ዓመት በላይ የተቸገርኩበት ነገር እንደምፈልገው ሆነልኝ አሁንም ይቅር ይበሉኝና የቀረውን ሁኔታውን ያስተካክሉልኝ።
2. ደስታ የራቀውንና አዕምሮዬን የሚረብሸኝን የልጁን ሀሳብ እመቤታችንንና አባቴን አቡነ እጨጌን ከአዕምሮዬ አውጡልኝ ፈጽሞ እንዳልጨነቅ አድርጉኝ አልኳቸው ከአዕምሮዬ አስወጥተውልኛል ተመስገን ፣
3.ሌላው ባለፈው ከአንድም ሁለት ቀን ጨጓራዬን በጣም አሞኝ ጸበላቸውን ጠጥቼ ወዲያው ዳንኩኝ።
4. ቤቴ አይጥ በጣም አስቸግሮኝ ነበር ብዛታቸው ራሱ ወደ ክፍለሀገር ስሄድ ለአባቴ አጥፉልኝ ብዬ ጸበል ረጭቼ ሄድኩ ስመለስ የት እንደገቡ አላውቅም አንዲት ብቻ ናት የቀረችው እሷንም እንደሚያጠፉልኝ አምናለሁ አመስግኑልኝ።
እሳቸውን የሰጠን አምላክ ይመስገን። አባቴ አቡነ እጨጌም ምስጋናዬ ይድረሳቸው፣ እመቤታችን፣ ጻድቃንና ሰማዕታት የተመሰገኑ ይሁኑ።አሜን

~ቦታው፦ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ ባዕለወልድ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም።
የገዳሙ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ!
ለበለጠ መረጃ/# 0911190212/# 0911481388