Get Mystery Box with random crypto!

፨፨በጻድቁ አባታችን /አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ/ 500 ዓመት በያዙት መስቀላቸውና መቋሚያቸው እ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨፨በጻድቁ አባታችን /አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ/ 500 ዓመት በያዙት መስቀላቸውና መቋሚያቸው እንዳበሳለን፤ ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ
ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።

፨ አቡነ እጨ ዮሐንስ ዘጠገሮ፨፦ሰው ሆነው ከመዕላክት የተደመሩ የእሳት ክንፍ የተሰጣቸው እስራኤላዊ ጻድቅ ሲሆኑ የድንግል ማርያምን ጡት የጠብ መና ብቻ እየተመገቡ 500ዓመት የኖሩ መንዝንና ይፋትን ሃገሪ ነው የሚሉት ገድላቸው ላይ። ፀሐይን፣ጨረቃንናደመናን በእጃቸው እየያዙ የጸለዩ አባት ናቸው።

ይህ ጠገሮ ጸበላቸው ሲሆን በዚህ ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ድንግል ማርያም ከሁሉም ነገደ መላዕክት ጋር ከሐዋርያት ከነበያት ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር ወርዶ የረገጠው ያረፈበት የባረከው ቦታ ጸበል ነው ይህ ጠገሮ ገዳም.ከዚህ ከማይጎለው ጸበላቸው ባህር ሲሆን ጥልቀቱ የአካባቢው ሰዎች የ15 የሞፈር ርዝመት ማለት 45ሜትር አካባቢ ነው ይላሉ!

ከዚህ ባህር ውስጥ የአባታችን የአቡነ እጨ ዮሐንስ ከሰማይ የወረደላቸው መስቀል፣የእጃቸው መቋሚያ፣ገድላቸው፣ደረቅ አፈር፣የእጃቸው መስቀልና ልብሳቸው ከዚህ ከምታዩት ጸበላቸው ባህር ውስጥ ወጥቶ በዚህ ገዳም ይገኝል/።ገና ወደፊት ግዜው ሲደር ብዙ የሚወጡ ግን የታዩ ታቦቶች፣የወርቅ ከበሮ እና የወርቅ ዙፋንዎችናየተለያዩ ቅርሶች እንደሚወጡ አባቶች ይናገራሉ።ጸበሉም ከምታዩት ባህር ሳይጎል በአሸንዳ ወጥቶ ህዝበ ክርስቲያኑ በገድላቸው፣ ከሰማይ በወረደው መስቀልና የወርቅ መቋሚያቸው እየተዳበስ እንዲጠመቁ ይደረጋል።አቡነ ተክለሃይማኖት ቀጥሎ እጨጌ የሆኑ፤በስማችው ዝናብ፣ብርድንና ውርጭን የሚገዝቱባቸው ትልቅ አባት ናቸው።ህዳር 29ተወልደው፥ሐምሌ 29ያረፉበት
ቀን ነው።በአላቸውም 29 ከባዕለ ወልድ ጋርና ወራዊ በዓላቸውም ነው።በዚህ በጠገሮ ገዳማቸው የእጃቸው መስቀላቸው ከቤተመቅደስ ሲወጣ መስቀሉ ላይ ብቻ ቀስተ ደመና እና ደመና ወርዶ እንደ ዥንጥላ ተዘርግቶ መስቀሉን ይከተልና መስቀሉ ተመልሶ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ የወረደው ደመና ሲበተ የሚታይበት አስደናቂ ገዳም ነው።

አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ]፦ቃልኪዳናቸው*/.........
~ ገዳምህን የረገጠ ንስሃ ሳይገባ አይሞትም
~ላልምረው ደጀንህን ገዳምህን አላስረግጠውም።
~ገዳምህን የረገጠ 10(አስር)ትውልድ ወደፊትም ወደኋላ እምርልህልለሁ።
~መሃን ቢሆንም ፤መሃን ብትሆንም ማህጸኖን እከፍትላታለሁ ልጅ እሰጣታለሁ እሰጠዋለሁ
+++አባታችን ዮሃንስም ጌታችንን እንዲህ አለው ~የገድሌን መጸሐፍ የፃፈ ቃልኪዳኔንም በመታመን ያፃፈውን በደሉ ምንም እንኳን ከሁሉም ቢበዛ ስለ እኔ ብለህ ማርልኝ፤ጌታችንም አባታችን ዮሃንስን እንዲህ አለው እውነት እልሃለሁ ቃልኪዳንህንም በመታመንና በፀሎትህ የገድልህን መፅሐፍ ያፃፈውንና የፃፈውን በስምህም ታቦትን የቀደሰውን የተከለውን እኔም እቀድሰዋለሁ በመንግስተ ሰማያትም ስሙን እፅፈዋለሁ ኤዶም ከተባለች ገነትም በሚመነጭ በህይወት ውሃ አጥበዋለሁ በይቅርታዬ እና በቸርነቴም እንዳልበደለ አደርገዋለሁ።
~ገድሌ የሰማ ያሰማ በመንግሰተ ሰማያት 100እጥፍ አስጉንም እስኪሰጥ ድረስ የክርስትያኑ የምትሆን ገነትንም እሰጠዋለሁ 10ትውልድም እምርልሃለሁ ብሎ መድሐኒዓለም ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል።
~++++፨ "ገድሌን በቤቱ ያስቀመጠ"፦
~የረከሱ መናፍስት አይቀርብትም፣
~ክፉ አጋንትም አይቀርብትም፣
~የቸነፈርና የወባ በሽታም አያገኛውም፣
~በነፍሱም መላዕኢከ ጽልመት አይነኩትም አለም ፍጻሜ ድረስ እጠብቀዋለሁ እምረዋለሁ።
~በገዳምህ ከየትም ቦታ መጥቶ የተቀበረ "መነኮሳት"ከሆኑ በሰማያት ያሉ ክንፎች አበቅልለታለሁ።
~አረማዊም ቢሆን አይሁድም ቢሆን፣ (ያላመነ ያልተጠመቀ) ቢሆንም፣ከሃጥያቱ ያልነጻ
ቢሆንም፣በገዳምህ አርፋ ቢቀበር ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር እልልሃለሁ፤እንዲሁም እንደ መቃብሬ ጎለጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ ብሎ መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ገብቶላችዋል።

፨፨የንግስ ጉዞ የጻድቁ አባታችን/አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ/ እረፍታቸው ሐምሌ ፳፱ 29
++++ የአመቱም የመጨረሻ ጉዞ ነው፤በክረምቱ ምክንያት ጸበሉም ሰለሚሞላ ዝግ ነው እስከ መስከረም 28/1/2015 ድረስ።
ጉዞ

ሐምሌ፳፰|፳፱ 28~29
ለበለጠ መረጃ የገዳሙ ኮሚቴ፦..
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
4/0901002929

በጻድቁ አባታችን 500 ዓመት በያዙት መስቀላቸውና መቋሚያቸው እንዳበሳለን፤ ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ
ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።ቃልኪዳን፤ጣባቂ ያላት ሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም የማትሆነው ቀድሞ የነበራች ከሁሉም የተለየች ሃገራችንን የቃልኪዳኑዋ አስራት ሃገር እምየ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አስታርቃን በሃገራችን ያለውን ርሃብ ታጥፋልን ህዝቦቿን ትጠብቅልን።አሜን!!!

ቦታው፦ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ ባዕለወልድ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም።

የገዳሙ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ!
ለበለጠ መረጃ/# 0911190212/# 0911481388
Fb-(Johnny Aleme)

++ ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ወራዊ በዓል!
++++ ወር በገባ 29
++++ልደታችሁ ህዳር 29
++++እረፍታችሁ ሐምሌ 29
++++ፍልሰት አጽማቸው መጋቢት 18
ሐገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ፍቅር አንድነትን ይሰጡን ።አሜን
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/?utm_medium=copy_