Get Mystery Box with random crypto!

ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ' | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን "አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
=ሠላም ጆኒ እንደምን አለህ አባታችን ያደረጉልንን ለመመስከር ነዉ የእናቴ ጓደኛ ጡቷን አሟት አብጦባት በጣም ነበር የሚያማት የአባታችንን ፀበል ለሶስት ቀን ተቀብታ አየተሻሸች በጣም ለዉጥ አላት እብጠቱም ሆነ ህመሙ ጠፍቶላታል አሁን ለአባታችን ክብር ምስጋና ይግባቸዉ።

=BESEME AB WEWELD WEMENFES KIDUS AHADU AMLAK AMEN selam Joni msekerent lemesetet new, Balefew samnet teneshu lije lay tkus shay tedefetobet tekatlobegne hakim bet hedo sherop tesetot kuslu tolo alden blogn techegere neber gn labat abune Echege negereachew bemeselachewem debabesh tsebelachewenem akemeshew ahun lay kuslo mulu lemulu tefetolet denual keber mesegan lemedahniyalem, endihum leabate abune echege yuhanes Amen!!

=ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ ወለተ ሃና እባላለው ስመስክር ካሁኑጋ ቡዙ ጊዜ ነው የተደረገልኝ ብዙ ስለሆነ ያለውት ውጪ ነው እና ቤተክርስትያን ውስጥ አንድ እህታችን መንፈስ ያስጨንቃታል እና አጋጣሚ ባልዋ ከኔ አጠገብ ቁጭሲል የ አቡነ እጬጌ ዮሃንሰን ምስክርነት ነገርኩት እና ጸበላቸውን እሰጥሃለው አልኩት እሱም ደስ ብሎት ዛሬ መጥቼ ልውሰደው አለኝ ሲመጣ መልካቸውን እና። ስእል አድኖ አቸውን ጨምሬ ሰጠውት የሚገርመው እንደሰጠውት በነጋታው ስትጠጣው ሙሉ ቀን አሙዋት በጣም ከብዶአት ዋለች በነጋታው ልትቆርብ ስትሄድ በጣም ደና ሆና ተሽሎአት ሄደች ከቁርባን በኋላም በጣም ቅልል ብሎአት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቁርባን ብኋል እንዲ ሲቀላት እናም ብዙ ለውጦች አሉአት እባክሽን መስክሪለን ብለውኝ ነው በጣም ነው ደስ ያለኝ እኝን ትልቅ አባት ፈጥነው ሰሚ የሰጠን አምላክ ይምስገን አሜን ጂኒ አንተንም ያገልግሎት ዘመንህ ይባረክ

ሰላም ጆኒ መቸም የሚደረግልኝ ብዙ ነው እና ሁሌም እመሰክራለው የሚያስጨንቀኝ የወረቀት ጉዳይ ነበር በጻድቁ ፈቃድ አግኝቸዋለው አመስግኑልኝ ለኔም ብሆን ለሰውም ጠርቻቸው የማይዘገዩ አባት ስለስጠኝ እግዚአብሄር ይመስገን አንተንም ጆንየ ጸጋውን ያብዛልህ አሜን

=በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!
ሰላም ወንድሜ ዩሐንስ

ፃድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ አባቴ ያደረጉልን ተአምር ይህ ነው።
በምንሊክ ሆስፒታል የጭንቅላት ቲቢ ነው ተብላ የተኛች አንድ እህቴ ነበረች የአባቴን ፀበልና እምነት ወስጄ ሳጠጣት እና ሰውነቷን ስቀባት: ጆሮዋ ላይ ሳፈስላት: ተዘግቶ የነበረ ጆሮዋ ወድያው ተከፈተላት እራስ ምታቱም ጭንቀቱም ለቀቃት እና አሁን ከሆስፒታል ወጥታለች በጥሩም ሁኔታ ላይ ነው ያለችው ። ፃድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ አባቴን አመስግኑልኝ ።

=Selme wendma jony endate nek abte abun ecga yargulgne lemmsekre new wendma besew hage 22 amte yezgnte passport alnbrwem neza meknyat hagru megbat ayclm nebr metca negracw nebre ngrcn ezme yemyalku werktoce nebr cersulgn ahun ye zegntun passport testot enn yesmu abte entnme yesmu layne sega yabkun ledcacew cemr egzabhare amlk yetmsegn yehun amn !

=ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ ምስክርነት ለመስጠት ነው 1 ባለፈው አመት የኔና የባለቤቴ ወረቅት ነበር ለአባታችን ነግርያቸው ወድያው ምልክቱን አሳዩኝና የባለቤቴ መጣ የኔ ሲመጣ አንድላይ እመሰክራለው ብየ ዝም አልኩኝ በየምክንያቱ እስካሁን የኔ አልመጣም ስላልመሰከርኩኝ ነው አሁን ግን ፍንጭ አሳይተውኛል እና ጨርሶ እጄ ውስጥ እንዲገባ ጸልዩልኝ 2 ወረቐት ለመላክ ሄጄ ፕሪንተሩ እንቤ አለን ደሞ የግድ መላክ ነበረብኝ የ አባቴን የአቡነ እጨጌ ዮሃንስን እና የድንግል ማርያምን ስእል ከሞብይሌ ላይ ይዤ ጸለይኩኝ ሁሉም ተስተካክሎ ላኩት በጣም ነው ደስ ያለኝ ስጠራቸው የማያሳፍሩኝ አባት 3 ባለቤቴ መኪና መግዛት ፈልጎ ጥሩ እንድያገኝ ጠይቄያቸው ጥሩ ገዝቶአል ሳልመስክር ብዙ ጊዜ አለፈው እና ዛሬ ድንገት መነሳት እንቢ አለችን እኔም ስእል አድእኖአቸውን አውጥቼ ይቅር ይበሉኝ እመሰክራለው አልኳቸው ወድያው ተስተካከለች 3 ባለቤቴ እያመመው ስራ መስራት አልቻለም ነበር ደጃቸው መቶ ለ ሰባት ቀን ከተጠመቅ በዋላ እግዚአብሄር ይመስገን በጣም ደና ነው በጠየቅኳቸው ጊዜ ለኔ ፈጥነው እንደሚደርሱ ለናንተም ይድረሱ ሳልመሰክር የረሳውት ካለ ይቅር ይበሉኝ በጸሎታቹ አስቡኝ ጆኒየ ላንተም ጸጋውን ያብዛልህ

=Selam Jonny endet neh sele abatachin lememesker nbr enate egruan le bizu gize amuat nbr enam abaten negryachew nbr ahun betam dena nat. Lela degmo betesebachen lay mesmamat alnbrem abaten lemgnachew yehew selamachin beztual. Keber le abatachin lelam lemgnalew endemisakam amnalew

=በስመ አብ ወውልድ ወመንፈስ ቅድስ አሀዱ አምላክ አሜን ።ባለቤቴ ወደ ውጪ አገር ለስራ ጉዞ ነበራት እና ስሞኑን ትንሽ ያስላት ስነበር ኮረና እንዳይሆን ስትለኝ ለአባታችን በፀሎት ለመንኳቸው ኤዳ ስትመረመር ነፃ ተብላለች ክብር ምስጋና ለፃድቁ አባታችን ይሁን

=Selme yena wendme abte yregulgn lmmsekre nebr lewndma serwen kamiy endiyargut teykcwe nbre yekmiy werkte ferme tblo telkoltal enne yesmu entnme yesmchu amlke ecga yohanse yetmsegn yehun amn

=ስላምህ ይብዛ ወንድሜ ጆኒ ዛሬም የአቡነ እጨጌን ምስክርነት ልሰጥ ነው ልጄ የጆሮ ደግፍ በሽታ አሞት ለሊት ህመሙ አላስተኛ ብሎት ተጨንቄ ነበር በፃድቁ በአቡነ እጨጌ ገድል ሙሉ ሰውነቱን አሻሽቼ እንቅልፍ እንዲወስደው አድርጉልኝ ብዬ ለፃድቁ አባቴና ለእናቴ ቃጥላ ማርያምን ተማፅኜ አላሳፈሩኝም ተኝቶ ለሊቱን በሰላም አልፎልናል ክብር ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ክብር ምስጋና ለናቴ ቃጥላማርያም ክብር ምስጋና ለአባቴ ለአቡነ እጨጌ እስከ መጨረሻው እንዲምሩልኝ በፀሎታቹህ አስቡኝ

፨፨፨፨የንግስ ጉዞ የጻድቁ አባታችን/አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ/ እረፍታቸው ሐምሌ ፳፱ 29
++++ የአመቱም የመጨረሻ ጉዞ ነው፤በክረምቱ ምክንያት ጸበሉም ሰለሚሞላ ዝግ ነው እስከ መስከረም 28/1/2015 ድረስ።
ጉዞ

ሐምሌ፳፰|፳፱ 28~29
ለበለጠ መረጃ የገዳሙ ኮሚቴ፦..
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
4/0901002929