Get Mystery Box with random crypto!

+ጻድቁ አቡነ እስትፋሰ ክርስቶስ ገዳም! ያረፉበት እና የጸለዩበት ዋሻ ይህ ገዳም ነው በረከቱ ይደ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

+ጻድቁ አቡነ እስትፋሰ ክርስቶስ ገዳም!
ያረፉበት እና የጸለዩበት ዋሻ ይህ ገዳም ነው በረከቱ ይደርባችሁ!

+++++++ጽድቁ አባታችን እስትንፋስ ክርስቶስ
*ፃድቁ አባታችን እስትንፋስ ክርስቶስ
~<አባታቸው መልአከ ምክሩ>
~< እናታቸው ወለተ ማርያም> ሲባሉ
~<ሀገራቸው ደውንት ደብረ አስጋጅ> ከተባሉት ቦታ ነው።በሕፃንነታቸው ለእናታቸው መልአኩ ስለቅድስናቸው ነገራት ጻድቁ ካደገ በኃላ ወደ ሐይቅ ሄደው ወደ ገዳሙ ለመግባት ባሕሩን የሚያሻግራቸው ቢያጡ ተንበርክከው ሲጸልዩ በመልአኩ እጅ ደንገል(ታንኳ)ቀርቦላቸው በዚያ ተሻግረዋል።ሲጸሉይም አቡነ አረጋዊና ቅድስ ያሬድ ተገልጸውላቸው።

ቅድስ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸሎታቸው እንዲህ ነበር። በመጀመሪያ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ሲጸልዩ ጌታችን መደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸላቸው።ቃልኪዳንም ሰጣቸው።
~በቀን በቀን እልፍ እልፍ ነፍሳት እምርላሃለሁ አላቸው፣
~በሦስቱ በአላቴ በተወከድኩበት በተጠመቅሁበትና በተነሳሁበት ዕለት ሰባት ሰባት እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ።
~አላቸው እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ዝክርህን፣ያዘከረ፣ስምህንየጠራ፣ገድልህን የሰማ፣የነበበ፣የተረጎመ፣ያስተረጎመውን፣የጻፈ፣ያጸፈውንም እምርልሃለሁ አላቸው።

ከዚህ በኃላ አባታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልደትህ ስንት ነው?ብለው ጠየቁት ፣ጌታችንም መለሰላቸው ልደቴ ሁለት ነው።ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ተወለድኩ።ድኀረ ዓለም ያለ አባት ከድንግል ማርያም ያለዘር ተወለድኩ።ከዚህ የተለየ የሚያስተምር ቢኖር በእኔም ሥልጣን በአንተም ሥለጣን የተወገዘ ይሁን።ወልደ አብ ወልደ ማርያም ብለህ አስተምር አላቸው።

ከዚያ በኃላ አባታችን ገዳማትን ሁሉ ዙረው ስለሃይማኖት ይረዱ ዘንድ ከገዳም ወደገዳም ጠይቀው በዓታቸውን አጸኑ።የምንኩስናን. በጀመሩ ጌዜ አልተቀመጡም።ቆመው መጸለይን አጸኑ፣ዋሻም አነፁ ከረዳቸውም ከአባ ልብሰ ክርስቶስ ጋር በጾም በፀሎት ያለ ውሃ ፣ያለ ምግብ፣በመስገድ ና በትጋት በመራቆት በችግር ፈጣሪያቸውን አገለገሉ።ድውይን በመፈወስ ከሲኦል ነፍሳትን በማውጣት በቀን በቀን በዚያ ጸሎት 24 እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ነፍሳትን ያወጡ ነበር።

አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቲስ ወደ በረሃ ሂደው ውኃ አፍልቀው ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አጠጥተዋል።ያም የፈለቀ ውኃ ዛሬ ጸበል ሆኖ የማይ መቅጃ ነው፣ስሙም አጋም ውሃ ይባላል።

~ወራዊ በዓላቸዉ 9
~ታህሳስ 9 ቀን ቅዳሴ ቤታቸው ይከበራል።
~ዕረፍታቸው ሚያዝያ 9 ቀን ነው።አስገራሚው. አራዊት የሚታዘዝላቸው ገዳምም በዳውንት ይገኘል።

የጻድቁ የቃል ኪዳናቸው በረከት ይደርብን።አሜን!!!

"ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፣ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው"መዝ•118/119÷129

"ፃዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት
ይወስዳል።" ማቴ 10፥41

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል።" ማቴ 10፥40

" እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።"
ዮሐ 9፥12
"የአለም ብርሃን ናችሁ!"

"ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን "1ቆሮ6፥2

-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-"ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።" 88(89)፥3

" እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም።" ማቴ 10፥40-42

የጻድቁ አባታችን ፀሎትና አማላጅነት በሁላችን በያለንበት ይኑር ሐገራችንን ኢትዮጵያ ይጠብቁልን!አሜን!!

ጻድቁ አባታችን አቡነ እስትፋሰ ክርስቶስ የጸለዩበት ዋሻ!እዚህ ወሎ ደላንታ ከአ/አ 720ኪሜ የሚገኛው ይህ ገዳማቸው ያረፉበት ገዳም ነው በረከታቸው በያላችሁበት ይደርባችሁ ይድረስባችሁ የጻድቅ መልዕከ ገድላቸው ያነበበ ትልቅ ቃልኪዳን አለው።በረከታቸው ይደርብን!አሜን!

አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like

+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431

+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME

+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5

+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...