Get Mystery Box with random crypto!

#Update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ168 የስራ መደቦች በ0 ዓ | Job Ethiopian

#Update

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ168 የስራ መደቦች በ0 ዓመት ስራ ፈላጊዎችን በቋሚነት መቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

በዚህም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በጀማሪ ባለሙያ ዜሮ አመት የተመዘገባችሁ የፈተና ቀን መጋቢት 10/7/2014 ዓ.ም ቅዳሜ መሆኑ ተገልጿል።

አመልካቾች የተሰጣቸውን የምዝገባ ማረጋገጫ መለያ ቁጥር መግቢያ የሚለዉ ላይ አስገብተው እንዲሞክሩት የተጠቆመ ሲሆን በሚያስገቡበት ጊዜ ባዶ ሰንጠረዥ ከመጣልዎት አልተመረጡም ማለት እንደሆነ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት አስተዳደር ቢሮ ከአንድ ሥራ መደብ በላይ ያመለከቱ አመልካቾቾ መፈተን የሚችሉት በአንዱ ብቻ መሆኑን ገልጿል።

በፈተና ሠዓት የተሠጥዎትን የምዝገባ መለያ ኮድ፣ የተፈተኑበትን የስራ መደብ መጠሪያ በፈተና አቴንዳንስ ወረቀት ላይ መፃፍ እንዲሁም እራስዎን የሚገልፅ መታወቂያ እንዳይረሱ ተብላችኋል።

ሆኖም መረጃዎን ለማየት የሚያገለግለው https://www.pshrdb.gov.et አሁን ላይ ይህንን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን አመልካቾች ጠቁመዋል።