Get Mystery Box with random crypto!

Jo art gallery

የቴሌግራም ቻናል አርማ jo_art_gallery — Jo art gallery J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jo_art_gallery — Jo art gallery
የሰርጥ አድራሻ: @jo_art_gallery
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 635
የሰርጥ መግለጫ

Jo art gallery

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-29 13:48:56
Jö @rt @yohannesfikru https://t.me/jodrawingart for more
126 viewsJö , 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 19:46:48
የ2021 Website developing አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያዊ።
100 viewsɪ'ᴍ ᴄᴀʀʟᴏꜱ, edited  16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 09:21:47 https://vm.tiktok.com/ZMLwNfnEB/?k=1
113 viewsJö , 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:54
ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሰን፥ አደረሳችሁ!
145 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:54 2,300+ ተከታይ ያለው ቻናል መግዛት የምትፈልጉ እውነተኛ ገዢ ብቻ ያናግረኝ።።


@gech_criminal
@gech_criminal
111 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:53 ኢማን

#በእዉነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ

#ክፍል2

ትልቁ ወንድማችን ቢላል ነው ቢሉ ከእኛ ጋር ብዙም ሰአት አያሳልፍም ስራ ነው ሚዉለው ጠኋት ወቶ ማታ ነው ሚገባው እኛ ራሱ መች በቅጡ እናየዋለን ቢሉ ሁሉ ነገሩ እኛን ነው ሚመስለው ከውጪ ላየው ጉረኛ ከሚባሉት ወንዶች ይመድቡታል የሚያስመስለውም ባህሪው ነው ሲበዛ ኮስታራ ነው እሱ ታድያ ስለሚባለው ነገር ግድ አይሰጠውም በጣም ነው ምወደው እሱም እንደዛው ቤት ውስጥ ከባባ ቀጥሎ እኔ ላይ ተስፋ አለው ሚረዱኝም እነሱ ናቸው ማማንስ ተዋት የምን መረዳት ነው በጣም ሀይለኛ ናት የትኛውንም ስራ በሰጠችው ሰአት እንዲተገበር ምትፈልግ ሴት ናት ለኔ ግን ጀግና ሴት ናት በጣም መቆጣጠሯን ግን አልደገፈውም..መፀዳጃ ቤት ሄጄ ራሱ ደቂቃ ትይዛለች ሃሃሃሃ ይሄን ያህል ማለት ነው አባ ሁል ጊዜ ይህንን ፀባይ እንድትተው ይነግራታል እሷ ግን አሻፈረኝ ነው ምትለው ነግሮ ነግሮ ሲደክመው አሁን አሁንማ ዝም ብሎ ማየትን መርጧል በዚያን ሰአት እኔ የ6ተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ሰሙ 8ተኛ ክፍል ነበረች በትምህርቴ ጎበዝ ተብለው ከሚመደብት ውስጥ አለሁበት...የኛ ቤተሰብ መካከለኛ ገቢ አለው አባ ጫማ ቤት አለው እማም እንደነገርኳቹ የሰፈር ሱቅ አላት ቢላልም በሹፍርና ሰርቶ ከሚያመጣው ገንዘብ ላይ ይሠጣታል አልሀምዱሊላህ ምንም ነገር እንድናጣ የማይፈልግ አባት አለን ከማንም እንዳናንስ አደርጎ ነው ያሳደገን አባ ለኔ አለሜ ነው ወላሂ....እኔን አይቶ እድሜን መገመት ለማንም ከባድ የሆነ ስራ ነበር። እድሜ ትንሽ ቢሆንም ከእድሜ በላይ ነው ማስበው ውሎዬም እኔን ከሚበልጡኝ ልጆች ጋር ነበር እሱም ይመስለኛል ተፅዕኖ ያደረገብኝ ቅዳሜና እሁድ ትምህርት ስለማይኖር እማን አግዛታለው ምሳ ሰአትም ለ አባ ምሳ ላደርስ ወጣለው...... አንድ ቀን ቅዳሜ እለት እንደ ወትሮ ሱቅ እየጠበኩ.........ሱቁ ተንኳኳ አቤት የዛን ቀን ወላሂ መቼም ልረሳው አልችልም ከ ጭንቅላቴ እስከ እግር ጣቴ ሲነዝረኝ ይሰማኛል ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ሲል ይታወቀኛል አይቼው ማላውቀው ሰው ሱቁ በር ላይ ቆሟል "እማ የመጠጥ ውሀ ይኖርሻል"? አለኝ ወዲያው ከቧንቧ ቀድቼ ሰጠሁት አመስግኖኝ ሄደ......ያኔ ነው የፍቅር ህይወቴ ተጀመረ ያልኩት። በጣም ገርሞኛል እንደዚህ አይነት ስሜት ሊሰማኝ በመቻሉ ብዙ ጊዜ ሱቅ ስጠብቅ የሰፈር ወንዶች ይቆማሉ ስላደረጉት ነገር ሴት ላይ እንዴት እንደሚጫወቱ ስሰማ ለወንድ ልጅ ቦታ የሚኖረኝ አይመስለኝም ነበር።



#ክፍል3_.......ይቀጣላል........


   

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ


ይ ላ ሉን @Yegitm_mender
ይ ላ ሉን @yegitm_mender
┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉┄
88 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:53 ​​◈ ━━━⸙ የግጥም መንደር ⸙━━━━ ◈


​​ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ

ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ

ከዚያን ቀን ጀምሮ

ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ

ዘገየሁ

መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው

እኔኮ ሆዴ

አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ፨


SQUAD


   

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ


ይ ላ ሉን @Yegitm_mender
ይ ላ ሉን @yegitm_mender
47 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:53 :)
የስደተኛው ሰው ደብዳቤ

ያለንብት በርሀ ይጨንቃል … ለካስ ሰው የሌለበት ቦታ ምኑም ደስ አይልም …ሙቀቱ የረብሻል የሚያወራም ሆነ የሚስቅ ማንም የለም ሁሉም ለየብቻው ሀገሩን ከእሩቅ እያየ ለብቻው ያወራል፡ ለብቻውም ይዘፍናል…

   

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ


ይ ላ ሉን @Yegitm_mender
ይ ላ ሉን @yegitm_mender
42 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:53 አትጨነቅ!

የመጨረሻ ቀኑ እንሆነ ሰው የሚያስደስትህን አርግ! ዘላለም እንደሚኖር ሰው ወጥረህ ስራ! የሁለቱን ሚዛን እያስጠበክ ኑር እንጂ ሰዎች ስላንተ በሚያስቡት አትጨነቅ!

ስንት አመት ልትኖር ነው የማትቀይረው ነገር የሚያሳስብህ? ወዳጄ ሺ አመት አትኖር ሺ ነገር ለምን ያስጨንቅሀል? ፈጣሪህን አመስግን ከዛ እስከጥግ ስራ እስከጥግ ተደሰት! አለቀ!

የደስታ ረቡዕ ተመኘንላችሁ

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

ይ ላ ሉን @Yegitm_mender
ይ ላ ሉን @yegitm_mender
39 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:18:53 ሊይዘኝ ነው መሰል

ፍቅር አሳስቆ መሰል ነው ሊይዘን ፣
ምንድነው ምክንያቱ አንተን የሚያሰኘኝ።
ከርቀት ሳይህ ልቤ የሚመታው፣
ደረቴን ፈንቅሎ የሚሮጥ ሚመስለው፣
ከአጠገቤ ስትሆን የምርበተበተው፣
በፍቅር ስታየኝ የምደናበረው፣
ያላንተ ሰከንዱ አመት የሚሆነው፣
ካንተ ጋራ ስሆን ጊዜው የሚበረው፣
የዘላለም እድሜ ሰከንድ የሚመስለው።
አሁንም አሁንም አንተን የሚያሰኘኝ፣
ለሰከንድ ብትርቅ የሚያቅበጠብጠኝ፣
የምግብ ፍላጎት ጠፍቶ የሚያሰቃየኝ።

ምንድነው ምክንያቱ... ሊይዘኝ ነው መሰል!
ከሴት ጋራ ሳይህ በቅናት ምቀላው፣
ስምህም ሲጠራ ዞሬ አቤት የምለው፣
ምንድነው ምክንያቱ ምን ብታስነካኝ ነው፣
ምንድነው ሰበቡ ምንስ ሊይዘኝ ነው።
አይኖችህ ከአይኔ ጋር በሚጋጩ ሰዓት፣
የሚነዝረኝ ንዝረት የሚሰማኝ ስሜት፣
የሚወረኝ ሀሴት፣
ሲኦል የሚመስለኝ አንተ የሌለህበት።
ምንድነው ምክንያቱ ምን ልታስይዘኝ ነው፣
ሚስጥሩ ምንድነው ስልጣኑስ ከማን ነው።

ሊይዘኝ ነው መሰል!

ሀኪሞች መርምረው አጣነው ይሉኛል፣
ጠቢቦችም መልሱ ከባድ ነው ይሉኛል።
ጠቢብ አልፈልግም ምክንያቱን ለማወቅ፣
በምታየኝ ጊዜ ለሚመታኝ መብረቅ።
ዶክተር አያሻኝም አልጠይቅ መድኃኒት፣
አልፈልግም መዳን ከሚሰማኝ ስሜት፣
ከሚነዝረኝ ንዝረት ከሚወረኝ ሀሴት።
የምሻው ፍቅርህን ሰላሜ ነው እሱ፣
መድኃኒቴም አይንህ ለህመሜ ፈውሱ፣
ዶክተሬም አንተ ነህ የልቤ ንጉሱ።
ስለዚህ... እባክህን ና እና ልቤን አድምጥልኝ፣
በሽታዬን አውቀህ መድኃኒት ጻፍልኝ፣
ከአጠገቤ አትራቅ ጥብቅ አድርገህ እቀፈኝ።

ሊይዘኝ ነው መሰል!!

ሊይዘኝ ነው መሰል ፍቅር አሳስቆ፣
ሊሰርቀኝ ነው መሰል ልቤን አስጨንቆ፣
የልቤን መረበሽ ምክንያቴን ማን አውቆ።

ሊይዘኝ ነው መሰል!

አገረሸ መሰል ፍቅርህ በድጋሚ፣
ከእግርህ ስር ሊያውለኝ ሊያረገኝ ታማሚ፣
የከፋ በሽታ በሌለበት ሰሚ።
ሰበብ የናፍቆቴ እንዲህ ምብሰለሰል፣
አደገኛው ፍቅርህ ሊይዘኝ ነው መሰል።

ሊይዘኝ ነው መሰል!

Señorita


,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

ይ ላ ሉን @Yegitm_mender
ይ ላ ሉን @yegitm_mender
37 viewssoıɹɐɔ pıʞ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ