Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ | 🌼JJU ACADEMY🌼📖

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ

የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ነሐሴ 2014 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል፡፡

መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦና ፀድቆ ለትግበራ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ የሚገባቸውን አገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎች፣ የሙያ ሥነ ምግባር ደንቦችና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ ስርዓቶችን አካቷል።

በመመሪያው ዝግጅት ሂደት በሥርዓተ ትምህርትና ፈተና ዝግጅት ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሙያ ማኅበራት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ግብዓት እንደሰጡበት መመሪያው በጸደቀበት ወቅት መገለጹ አይዘነጋም፡፡

ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በበይነ መረብ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩ ይታወቃል።