Get Mystery Box with random crypto!

'ለካስ ደስታም ሲያልፍ ህመም ይሆናል።'' ትዝታዬ እሷ ውስጥ ሰጥሟል እሷነቷ ዘመኔን የደበቅኩበት | GRACE_TUBE .♥.

"ለካስ ደስታም ሲያልፍ ህመም ይሆናል።''

ትዝታዬ እሷ ውስጥ ሰጥሟል እሷነቷ ዘመኔን የደበቅኩበት ባህር ነው።ትናንታችን ያለፈ ሳይሆን ገና እንደሚመጣ ተስፋ በልቤ ተሞንጭሯል።በመቅረት ውስጥ መዘውተርን ማሰብና ማለም በጊዜ ካብ ውስጥ ያሰሩኝ የምናብ ቤቴ ናቸው።በነበረችኝ ጊዜ ያለኝ ደስታ የቀረች እለት እንደ በረዶ ሟምቶ በሃዘን ኮሰመነ።ፈገግታዬ ተሰብሮ እንዳረጀ መስታወት በናፍቆት ተኮራምቶ  ደበዘዘ።

ለካስ እንባና ሳቅ ልክ እንደ ነፍስና ስጋ የተቆራኙ ናቸው።ሲያድር አንዱ ለአንዱ ገጹን ይቀይር ኖሯል.......ሀሴት ያደረግኩባቸው ቀናቶች የሚፈጥሩብኝ  ህመም የህይወት አቅጣጫዬን ወደ ገሃነም ወረወሩት።
የሄደች እለት ነበር ራሴን መሆን ያቃተኝና አዲስ በማልወደው ሰው የተተካውት።የሄደች ግን ያለች እንደ ጨረቃ ያለፈ ብርሃኗ የሚታየኝ ግን ለመንካትና፣ለመዳሰስ ደግሞ ያልታደልኳት ተፈጥሮዬ ናት።የኔ አለም ኢሄው ነው እምኖረውም እሷነቷ ውስጥ ያለውን እኔነቴን ስፈልግ ነው.........

Share @JESUSlovingly142