Get Mystery Box with random crypto!

' በጉብኝቴ እንደታዘብኩት ለአሜሪካ ሕዝብና መንግስት ነጻነት ፣ ክብርና ጥቅም ሲሉ ውድ ነጻነታቸው | Jafer Books 📚

" በጉብኝቴ እንደታዘብኩት ለአሜሪካ ሕዝብና መንግስት ነጻነት ፣ ክብርና ጥቅም ሲሉ ውድ ነጻነታቸውን የከፈሉ በመሆናቸው መታሰቢያዎቻቸው በክብር የተያዙ ናቸው :: መታሰቢያቸው ውብ ሆኖ ለዘላለም ተቀምጧል :: ልጅ ፣ የልጅ ልጅ ፣ ዘመድ ፣ ጓደኛ በመሰዋትነታቸው በአደባባይ እንዲኮራ በሞታቸው እንዳይጸጸት በሚያስችል መልኩ ተሠርቷል ::

አሁን ያለው ትውልድም ለሀገሩ ቢሰለፍ ደሙ ደመ-ከልብ ፣ ታሪኩም ዳዋ ለብሶ የሚቀር እንዳልሆነ መተማመኛ ሆኗል :: የአሜሪካን የጦር ኃይል መቀላቀል በሕይወትም ላሉት በሁሉ ነገር ቅድሚያ የሚያሰጥ ፤ በሞት በመለየትም ትልቅ ባለታሪክ የሚያደርግ ሙያ መሆኑ በገሃድ ይታያል :: እናም አሜሪካ በዓለም ላይ ለምታካሂደው ግዙፍ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ( Operation ) የሚሰለፉላት ወታደሮች አጥታ አታውቅም :: "

ከዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ " ችቦ " ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ


መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት !!