Get Mystery Box with random crypto!

#ሙሳ ዐ.ሰ #ክፍል ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝ | 🍂ISLAMIC TEAM🍂

#ሙሳ ዐ.ሰ
#ክፍል

ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው አልቀው የልጅ ልጆቹ ግን በመተካካት ግብፅን እጅጉን እየሞሏት ነው።
ምንም እንኳን ያኔ በዩሱፍ (ዐ ሰ) ዘመን እነዚህ በኒ ኢስራኢሎች (የያዕቁብ ልጆች) በግብፅ ምድር የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ያለው ንጉስ ግን እጅጉን ይበድላቸው ጀምሯል።
ይሄን ግዜ ነበር እንግዲ አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ነፃ እንዲያወጣ ሙሳን የላከው።
የሙሳ የዘር ሀረግ፦
ሙሳ ኢብን...ዒምራን ኢብን...የስሀር ኢብን...ቃሂስ ኢብን...ላዊ ኢብን...ያዕቁብ ኢብን...ኢስሀቅ ኢብን...ኢብራሂም ኢብን....አዛር......ምናምን እያለ ይቀጥላል።
ሙሳ ከመወለዱ በፊት ፊርዐውን አንድ ቀን በህልሙ የሆነች እሳት ከእየሩሳሌም ወደ ግብፅ መጥታ የግብፃውያንን ቤት እየዞረች ታቃጥል'ና የበኒ ኢስራኢሎችን ቤት ስትተው ተመለከተ።
እና ይህ ህልም እረፍት የነሳው ንጉስ በነጋታው ጠንቋዮችን እና ኮከብ ቆጣሪዎችን ሰብስቦ የህልሙን ፍች ሲጠይቃቸው፦"ከነዚህ የያዕቁብ ልጆች(ከበኒ ኢስራኢሎች) አንድ ንግስናህን የሚሽር ልጅ ሊወለድ ነው" አሉት።
ፊርዐውን ይህን ሲሰማ በጣም በመደንገጥ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆችን እንዳለ እንዲገደሉ አዘዘ...ምንም አይነት ወንድ ልጅም ቢረገዝ እንደሚገድልም ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የፊርዐውን ትዕዛዝ መተግበር ተጀመረ...በጣም ለቁጥር የሚያዳግቱ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆች እንደ ገፍ ተገደሉ። በመጨረሻም ይህ ህግ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት የግብፅ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ፊርዐውንም ዘወትር የሚተገበረውን የግድያ ተግባር አንድ አመት ግድያ እንዲቆም እና አንድ አመት እንዲገደል አደረገ.....
በዚህ ሁኔታ ነበር የማይገደልበት አመት ላይ ሀሩን የተባለው የሙሳ ወንድም ተወልዶ፤ በሚገደልበት አመት ደሞ ሙሳ የተወለደው።
ሙሳ ልክ እንደተወለደ የሙሳ እናት ህፃኗን አይኗ እያየ እንዳይገድሉባት በጣም ተጨነከች።ምታደርገው ጠፍቷት በመዋለል ላይ ሳለች አላህም እናትየውን ከእንጨት የሆነ ሳጥን ሰርታ፤በዚያ ሳጥን ውስጥ ህፃኑን እንድታስገባው'ና ሳጥኑንም ከነ ህፃኑ ወንዝ ላይ እንድትጥለው አዟት፤ ይህንንም ህፃን ነቢይ አድርጎ እንደሚመልስላት ቃል ገባላት።
በዚህ መሰረት የሙሳ እናት ህፃን ልጇን በጨርቅ ጠቅልላ በሳጥን አሽጋ ሆዷ እየባባ በናይል ወንዝ አሻግራ ሸኘችው።
ውሀውም ሳጥኑን ከነ ህፃኑ እያንሳፈፈ የልጆችን ግድያ ትዕዛዝ ወደሰጠው ፊርዐን ግቢ ይዞት ገባ።በሰዐቱ የፊርዐውን የሚስቱ አገልጋዮች እዚያ ወንዝ ዳር እየታጠቡ ነበር'ና ይህን ሳጥን ሲመለከቱ በውስጡ ወርቅ ያለ መስሏቸው ለእመቤታቸው ሳጥኑን ሳይከፍቱ በስጦታ መልክ ወስደው አስረከቧት።
የሙሳ እህት እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር'ና እናቷ የጣለችው ሳጥን በገዳዮች እጅ መግባቱን ስታረጋግጥ ወደ እናቷ ስትከንፍ ሄዳ ነገረቻት።እናትም ልጇን ተመልሳ ሄዳ ሁኔታውን እንድታጣራላት ላከቻት። ልጅቷም ሁኔታውን ለማጣራት ቤተመንግስት ተመልሳ መጣች።
ንግስቲቱም አገልጋዮቿ እና ባለቤቷ ባሉበት ቦታ ሳጥኑ እንዲከፈት አዘዘች፤ሳጥኑ ሲከፈትም ልብን የሚያማልል ውብ እና ማራኪ ልጅ በሳጥኑ አገኙ።የፊርዐውን ሚስት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር'ና፦"ልጅ ስለሌለን እባክህ ይሄን ህፃን አትግደለው።ወደ ፊትም ልጃችን አድርገን እንይዘዋለን " አለችው።
እሱ ህፃኑን መግደል ቢፈልግም የሚስቱን ሀሳብ መቃረን አልፈለገም'ና በሀሳቧ ተስማማ።
አሁን አስቸጋሪው ነገር መጣ....ይህን ምግብ ያልጀመረ ህፃን ማን ያጥባው??????
የተለያዩ አጥቢ እናቶች ይህን ህፃን ሊያጠቡ ቢሞክሩም ህፃኑ ግን የማንንም ጡት ከአፉ ሊያስጠጋ ፍቃደኛ አልሆነም።ይልቁኑ አጥቢዎቹ ሲመጡ ይባስ ያለቅስ ነበር።
የፊርዐውንም ሚስት እጅጉን ተጨነቀች አላህ በልቧ የሙሳን ፍቅር ስለከተበባትም በህፃኑ ለቅሶ ጭንቀት ምትገባበት ጠፋት።
ይሁ ሁሉ ሲሆን ሁኔታዎችን ትከታተል የነበረችው የሙሳ እህት ምንም እንደማያውቅ ሆና፦"ይህን ህፃን ለናንተ የሚያሳድግላችሁን ቤተሰብ ለመላክታችሁ!! ታማኝም ናቸው" አለቻት።
የህን ስትሰማ የፊርዐውን ሚስት ደስታዋ ወደር አጣ።የፈለጉትን ክፍያም ለአጥቢዋ እንደሚከፍሉም ቃሉ ገቡላት'ና የሙሳ ትክክለኛዋ እናት እንድትመጣ አደረጉ።
የሙሳ እናት ቤተ መንግስት ገብታ ልክ ልጇን ስትመለከት ልቧ ተንሰፈሰፈ...፣እንባዋ ከአይኗ ሊሾልክ ተቃረበ።እንደምንም ራሷን ተቋቁማ ህፃኑን ልታጠባ ስታቅፈው ህፃኑ ለቅሶውን ትቶ ጡቷን ይሞጥሙጥ ጀመር።ፊርዐውን እና ኣሲያ(የፊርዐውን ሚስት) ይህን ሲመለከቱ በጣም ተደሰቱ።
በዚህ ሁኔታ የሙሳ እናት እየተከፈላት ልጇን ለ2 አመታት ያህል አጠባችው።
ግዜ ግዜን እየተካ ሙሳም ትልቅ ልጅ ሆነ።ምንም እንኳን ሙሳ የፊርዐውን ያብራኩ ክፋይ ባይሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን የፊርዐውን ልጅ በመባል ነው ሚታወቀው።
ከእለታት አንድ ቀን ሙሳ በጠራራ ፀሀይ ከተማ ውስጥ እየተራመደ ሳለ አንድ ግብፃዊ እና አንድ በኒ ኢስራኢላዊ ሲደባደቡ ተመለከተ። በኒ ኢስራኢላዊውም ሙሳን አድነኝ በማለት ተጣራ።
ሙሳም ይህን ግዜ ግብፃዊው ላይ ገራሚ ቦክስ ሰነዘረበት'ና ሳያስበው የግብፃዊው ህይወት በሙሳ እጅ አለፈች።ይሁን እንጂ ማንም አላወቀበትም ነበር።
ይሄን ግዜ ሙሳ በጣም በመፀፀት አላህን ምህረት ለመነው። አላህም ተውበቱን ተቀብሎት፦"ሙሳ ሆይ! በልቅናዬ እምላለሁ ይህች የገደልካት ነፍስ ለቅፅበት እንኳን በኔ ጌትነት ያመነች ብትሆን ከባድ ቅጣትን አቀምስህ ነበር" አለው።
ሙሳም ከዚያ ቀን አንስቶ የግብፃዊው ሟች ወገን መጥተው እንዳይበቀሉት በጣም ስለሰጋ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ ጀመረ።
በማግስቱም ሙሳ ከተማ ላይ ሳለ ይህ ትናንት ሲደባደብ የነበረው (በኒ ኢስራኢላዊው) የሙሳ ዘመድ ዛሬም ከሌላ ግብፃዊ ጋር ሲደባደብ ተመለከተው።
የሙሳ ዘመድ ሙሳን ሲመለከት ዛሬም የእርዳታ ጥሪውን ለሙሳ አሰማ።
ሙሳም ወገኑን(በኒ ኢስራኢሉን) ሲመለከት፦"አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ" አለው።
ወገኑም፦"በትናንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን አትፈልግም" አለው።
በዚያ አካባቢ የነበሩ የግብፅ ነዋሪያንም ወገናቸውን የገደለው ሙሳ መሆኑን ሲያውቁ እሱን ሊገድሉት መመካከር ጀመሩ።
ይህን የሰማ ሂዝቂል የተባለ ግብፃዊ ሙእሚን ለሙሳ፦"ግብፃውያን አንተን ሊገድሉ እየተመካከሩ ስለሆነ የግብፅን ምድር ለቅቀህ እንድትወጣ እመክርሀለሁ" ብሎ መከረው።
ሙሳም የግብፅን ምድር ትቶ በረሀውን እያቆራረጠ እግሩ ወደ መራው ቦታ መጓዝ ጀመረ።ብዙ ተጉዞ ረሀብ፣ጥማት እና ድካም ድንበር አልፈው ካዳከሙት በኋላ መድየን የምትባል ሀገር ደረሰ።
ሙሳ በከተማዋ መግቢያ ላይም ሲደርስ የመድየን ከተማ ነዋሪያን በሙሉ እንስሳዎቻቸውን ውሀ የሚያጠጡበትን አንድ ምንጭ ቦታ ደረሰ።ልክ እዛ ሲደርስ

#part
ይ.............ቀ.....
.................,,.,ጥ....,ላ......ል

@islllllaamic