Get Mystery Box with random crypto!

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት ይህ የሐጅን ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት የሚያብራራ | ኢስላማዊ እውነታ

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

ይህ የሐጅን ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት የሚያብራራ አጭር ጽሁፍ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል–ዑስይሚን ተዘጋጅቶ ወደ አማርኛ ተመልሶ የተሰራጨ ነው።
በአላህ ፍቃድ የየእለቱን የሐጅ ተግባር ከዚህ ቀጥሎ ከፋፍለን እናቀርባለን:–

(ክፍል–1)

የመጀሪያው ቀን ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን የውመ አት–ተርዊያ በመባል የሚታወቀው ነው።
ለሐጅ ኢህራም ወይም ኒያ ማድረግ
በመካ ከተማ እና በዙሪያዎ ያለ ሰው ካለበት ቦታ ታጥቦ፣ (አካሉን) ሽቶ ተቀብቶ፣ የኢህራም ልብሱን ለብሶ እና "ለበይከ ሀጀን፤ ለበይከ አላሁመ ለበይክ፤ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለከ" በማለት ኢህራም(ኒያ) ያደርጋል። ከዚህ ቀን በፊት መካ ያልመጣና ከሚቃት ክልል ውጪ ለሀጅ ወይም ዑምራ የሚመጣ ሰው የሚቃት ክልሉን ያለ ኢህራም(ኒያ) ማለፍ የለበትም።* *ወደ ሚና መጓዝ*
ወደ ሚና ይጓዛል እዚያም የዘጠነኛው ቀን ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ ይቆያል። የስምንተኛውን ቀን የዙሁርን፣ የዓስርን፣ የመግሪብን እና የዒሻን እንዲሁም የዘጠነኛውን ቀን ፈጅር ሰላቶች በየወቅታቸው እና አራት አራት ረከዓ የሆኑትን የዙህር የዓስርና የዒሻእ ሰላቶች ሁለት ሁለት ረከዓ በማድረግ አሳጥሮ ይሰግዳል።

ይቀጥላል…

ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ
አላህ ያግራልን!

ጣሀ አህመድ

https://t.me/tahaahmed9