Get Mystery Box with random crypto!

ዒድ እና ጁሙዓ ከተገጣጠሙ በነቢዩ ﷺ ዘመን ዒድና ጁሙዓ ተገጣጥመው ዒድን ካሰገዱ በኋላ ወደ ህዝ | ኢስላማዊ እውነታ

ዒድ እና ጁሙዓ ከተገጣጠሙ

በነቢዩ ﷺ ዘመን ዒድና ጁሙዓ ተገጣጥመው ዒድን ካሰገዱ በኋላ ወደ ህዝቡ በመዞር እንዲህ አሏቸው፦

«ሰዎች ሆይ! ዛሬ ሁለት ዒዶች ተገጣጥመዋል። ዒድን የሰገደ ሰው ለጁሙዓ ይበቃዋል። እኛ ግን ጁሙዓን ለመስገድ እየሄድን ነው።»
(አል-ሐኪም/ አቡ-ዳውድ1073)

ከዚህ በመነሳት ኢማም አህመድ፣ ኢብን ተይሚያህ፣ አል-ሸውካኒ እና አብዛኛው ዑለማዎች ተከታዩን አስቀምጠዋል፦

ዒድን የሰገደ ሰው ከጁሙዓ ወይም ከዙሁር አንዱን መርጦ መስገድ ይችላል።

ዒድን ያልሰገደ ሰው ጁሙዓን መስገድ ግዴታው ነው።

ዒድን የሰገደ እስከ ዐሱር ሶላት የለውም የሚለው በአብዛኛው ዑለማዎች ውድቅ የተደረገ ነው።
(አል-ሙግኒ 2/265/ ፈታዋ ኢብን ተይሚያህ 24/211)

ኢማም አቡ-ሐኒፋ፣ ኢማም ማሊክ እና ኢማም አሽ-ሻፊዒይ ደግሞ፦

ሐዲሱ የተነገረው ዒድን ለመስገድ ከሩቅ ቦታ ለመጡት ስለሆነ በከተማ የሚኖሩት ጁሙዓን መስገድ ግዴታ ይሆንባቸዋል። ዒድ ሱንና ነው። ለሱንና ተብሎ ፈርድ ሶላት አይሻርም ብለዋል።
(ሐሺያህ አል-ደሱቂ 1/391)

በጥቅሉ ሁሉም የተስማሙበት ዒድን የሰገደ ጁሙዓን ወይም ዙሁርን መስገድ ግዴታ አለበት። እስከ ዐሱር ሶላት የለም የሚለው ውድቅ ነው።