Get Mystery Box with random crypto!

ሼይኽ ሱለይማን አረሂይሊ ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ አንድ ሰው የውጪ ልብሱንና የውስጥ ልብሱን ተ | ጠቃሚ ኢስላማዊ ፅሁፎች

ሼይኽ ሱለይማን አረሂይሊ ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

አንድ ሰው የውጪ ልብሱንና የውስጥ ልብሱን ተቅዋን ከተከናነበ /ከለበሰ/ ራሱን ብሎም ማህበረሰቡን ከመጥፎ ነገሮችና ከፊትና ይጠብቃል ።

ለዚህም ላቅ ያለው ጌታችን እንዲህ ይላል ፦
يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا ۖ وَلِبَاسُ التَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ۚ ذَٰلِكَ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ

የአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡ አል ዐእራፍ :26
{فقة اللباس والزينة :٩}