Get Mystery Box with random crypto!

የምንሰጠው ሌላው ስለሚያስፈልገው ነው! አንድ ሰው እንዲህ አለ 'መስጠትን ተምሬያለው ተርፎኝ ሳይ | Inspire Ethiopia

የምንሰጠው ሌላው ስለሚያስፈልገው ነው!

አንድ ሰው እንዲህ አለ "መስጠትን ተምሬያለው ተርፎኝ ሳይሆን ማጣትን ስለማውቀው ነው!" በእርግጠኝነት በአንድም በሌላም አጋጣሚ መራብን የማያውቅ ሰው የለም! የተራበን ሰው የሆነ ምግብ ስትሰጠው ምን ሊሰማው ይችላል? ብርዱ ያሰቃየውን ሰው ልብስ ስትደርብለት እንዴት አድርጎ ይደሰት! ታድያ የዚህ ደስታ ምንጭ ከመሆን በላይ በዚህ ምድር ምን ትልቅ ነገር ይገኛል! የተረፈህ ስለሆንክ ስለሞላህ አይደለም ግን ስለሚያስፈልጋቸው ጥቂቷን ስጥ እና ብዙ ተደሰት ወንድሜ እህቴ አንቺም ካለችሽ አጉርሺ ስለሚመልሱልሽ ሳይሆን ስለሚያስፈልጋቸው ነው!

ደስ የሚል ሰንበት ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ