ፌስቡክ ላይ ሳይጠየቁ መጫወት የሚጀምሩ ቪድዮዎችን እንዴት ማስቆም ይቻላል? በሞባይል ስልካችሁ አልያም በኮምፒዉተራችዉ ላይ የፌስቡክ ፖስቶችን በምትመለከቱበት ወቅት ቪድዮ ላይ ስትደርሱ እንዲጫወት ሳትጠይቁት መጫወት ይጀምራል፡፡ ይህ ቪድዮ የሚያሳየዉ ስለምትፈልጉት መልካም ነገር ከሆነ ክፋት አይኖረዉም፡፡ ሆኖም ግን ቪድዮው ስሜትን የሚረብሽ አልያም ሌላ ልትመለከቱት የማትፈልጉት መጥፎ መረጃ ከሆነ የያዘዉ ምቾት መንሳቱ ብሎም የስሜት መረበሽ ማስተከተሉ አይቀርም፡፡ በተጨማሪም የስልክዎን ዳታ ያላግባብ በማባከን ለተጨማሪ ወጪ ይዳርጋል፡፡ ይህን ሳይጠየቅ የሚጫወት ቪድዮ በስልክም ሆነ በኮምፒዉተራችሁ ላይ የተወሰኑ ማስተካከያዎችን በማድረግ ማስቆም የሚቻል ሲሆን ምን ማድረግ እንደሚገባችዉ ከዚህ በማስከተል አቅርበንላችዋል፡፡ ከኮምፒዉተራችሁ ላይ ለማስቆም፦ 1. በኮምፒዉተራችዉ ብሮውሰር ላይ ፌስቡክ አካዉንቶን ይክፈቱ፡፡ 2. በስተቀኝ በኩል መጨረሻ ላይ የሚገኘዉን፣ የሶስት መዓዘን ምልክት ያለዉ ማዉጫ በመንካት Settings የሚለዉን ይክፈቱ፡፡ 3. በስተግራ በኩል ካሉት ምርጫዎች ዉስጥ ወደ መጨረሻ አካባቢ Videos የሚል አማራጭ ይገኛል፡፡ እሱን ይጫኑት፡፡ 4. ከሚመጡት አማራጮች ዉስጥ Auto-Play Videos የሚል ማስተካከያ ይገኛል፡፡ ለማስቆም Off የሚለዉን ይምረጡ፡፡ ከአንድሮይድ ስልካችዉ ላይ ለማስቆም፦ 1. ፌስቡክ አፕን ይክፈቱ፡፡ 2. ☰ የዚህ አይነት ምልክት ወዳለዉ Settings menu ይሂዱ፡፡ 3. ወደ ታች በመዉረድ Settings & Privacy የሚለዉን ይጫኑ፡፡ 4. ከዛም Settings የሚለዉን ይምረጡ፡፡ 5. Media and Contacts የሚለዉን እስኪያገኙ ወደ ታች ይዉረዱ፣ ከዛም Videos and Photos የሚለዉን ይምረጡ፡፡ 6. በመጨረሻም Autoplay የሚለዉን ሲያገኙ Never Autoplay Videos የሚለዉን በመምረጥ ማስቆም ይችላሉ፡፡ ከአይፎን ስልካችዉ አልያም አይፓዳችዉ ላይ ለማስቆም፦ 1. ፌስቡክ አፕን ይክፈቱ፡፡ 2. በስተቀኝ በኩል ከላይ የሚገኘዉ ማዉጫ ይጫኑ፡፡ 3. ወደ ታች በመዉረድ Settings & Privacy የሚለዉን ይጫኑ፡፡ 4. ከዛም Settings የሚለዉን ይምረጡ፡፡ 5. Media and Contacts የሚለዉን እስኪያገኙ ወደ ታች ይዉረዱ፡፡ 6. በመጨረሻም Autoplay የሚለዉን ሲያገኙ Off የሚለዉን በመምረጥ ማስቆም ይችላሉ፡፡ ▬▬ Share ▬▬▬▬ ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። here it is https://t.me/Information_Science_Technology በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q 2.3K views08:01