Get Mystery Box with random crypto!

Imam ahmed

የቴሌግራም ቻናል አርማ imamahmedcom — Imam ahmed I
የቴሌግራም ቻናል አርማ imamahmedcom — Imam ahmed
የሰርጥ አድራሻ: @imamahmedcom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33
የሰርጥ መግለጫ

"አንድን ሙስሊም የሚያከብር በትህትና
የሚያናግር ሀዘኑን የሚያቃልል ሁሌም በአላህ
በረካ ውስጥ ነው"
ረሱል #ﷺ
ለአስተያየተው
@ZIRAE_99

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 08:28:29
አረፋ ቀን ዱአ ተቀባይነት ያለው ቀን ነው እንበራታ ወንድሞች እና እህቶች በዱአችሁ እንዳትረሱን።
51 viewsousman, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:45:40
#አላሁ_አክበር
#አላሁ_አክበር
#አላሁ_አክበር
#ላኢላሀኢለላህ
#አላሁ_አክበር
#አላሁ_አክበር
#ወሊላሂል_ሀምድ

@ImamAhmedcom
91 viewssalim abdela, 03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:35:50
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
84 viewssalim abdela, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:06:04 ነገ የዙልሒጃ 9ኛው ቀን ነው። ነገን ሁላችንም በፆም እናሳልፍ
325 views anu እ'ን'ደ'ማ'ን'ነ'ቴ እኖራለሁ , 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:38:46 ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል

ቤተሠቦቹን በሙሉ ይዞ አሜሪካ ሄዶ መኖር ከጀመረ ሠነባብቶዋል አሜሪካ በሚገኙ መሳጂዶች ሁሉ በመዘዋወር በዳዕዋ ስራ ላይ ተሠማርቶ ዳዕዋ ማድረግ ወደ አሜሪካ የሄደበት ዋነኛዉ አላማ ነበር። አሜሪካዊ ሙስሊም ተርጓሚ አለዉ አብሮት የሠዉ ልጅ የተፈጠረበትን አላማ ጣኦታትን ከመገዛት አላህን ወደ መገዛት ይጣሩ ጀመሩ በዳእዋ ስራቸዉ ዘወተር ለብዙሀኖች የሂዳያ ሠበብ ሆኑ እንደሁሌዉ የዛን ቀን የመግሪብ ሰላት አካባቢ ዳዕዋ ወደሚያደርጉበት መስጂድ ሄዱ ውዱዕ አድርገዉ ወደ መስጂድ እንደገቡ አስተርጓሚዉ ከመሬት ወደቀ የአላህ ቀድር ሆነና ሞታ ዳኢዉ በገዳይነት ተጠረጠረና ታሠረ ያለምንም ጥፋት አንተነህ የገደልከዉ ተብሎ ለ3አመታት በእስር ማቀቀ። ለማስፈታት ብዙ ጥረት ቢደረግም አልተቻለም ጁሙዐ ቀን ጠዋት ከእስር ቤት ለቤተሠቦቹ እንደሞተ ተነግራቸዉ ጀናዛ እንዲወስዱ ተደረገ።
ጀናዛዉን ወደትዉልድ ሀገሩ መመለስ ስላለበት በፍሪጅ ዉስጥ ተደረገ ከሳምንት በኋላ ጀናዛዉ እየመጣ እንደሆነና ጠዋት 4ሠዐት አካባቢ እንደሚደርስ ለማጠብ እንድዘጋጅ ወላጅ አባቱ ነገሩኝ።
ጀናዛዉ መጣ ጀናዛዉ ወዳለበት ክፍል ገባሁ እኔ ከመምጣቴ በፊት ጀናዛዉ አልተከፈተም ነበር ሁሉም ጀናዛዉን ለማየት ሲመጡ ከእናቱ ከአባቱና ከወንድሙ ዉጪ ማንም ሠዉ እንዳይገባ ከለከልኩ ወደ ክፍሉ ከገባን በኋላ በሩን ዘግተን ጀናዛዉን መክፈት ጀመርኩ በአላህ ይሁንብኝ ከሞተ ሳምንት ያለፈዉ ጀናዛ ፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት ነበር ልክ ከሞተ ደቂቃዎች እንኳን ያልሞሉት ይመስላል። የሚያምር ፈገግታ እያሳየ ነበር ይህንን ሁስነል ኻቲማ ሠዎች ያዩት ዘንድ ካሜራዬን አዉጥቼ ፎቶ አነሳሑት መስጂደል ሀረም ከሠገድንበት በኋላ ቀበርነዉ ፡፡

እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ

በእርስዎ ሰበብ አንድ ሰው ቢቶብት ወይም ባለበት ጠንካራ አቋም ላይ ቢፀና ከፍተኛ አጅርን ይጎናፀፋሉ
250 viewsousman, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:58:38 #የውሙ_ዐረፋ

ነገን ማለትም የውሙ ዐረፋን (9ኛውን ቀን ) መፆም የ2 ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል።

የዐረፋን ቀን ፆም ሙሉ አጅር ለማግኘት፣

1. ስምንተኛው ቀን ምሽት ላይ (ዛሬ ሐሙስ ማታ) ጾምን ነይቶ ማደር፣
2. በዕለቱ ከዐረፋ ፆም ውጪ ሌላ (የቀዳና ወዘተ) ፆም አዳብሎ አለመነየት ይገባናል።

ማስታወሻ
ቀዷ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።
ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣

1. ቀኑን መጾም
2. ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3. ዱዓእ ማብዛት

ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ነገን (ጁሙዓ 1/11/2014 ) በልባችን የዐረፋን ፆም በማሰብ(በመነየት) እንጹም!

ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ
ለራሳችን፣ለቤተሰባችን፣ ለሀገርና ለኡመታችን ዱዓእም እናብዛ!

@ImamAhmedcom
282 viewssalim abdela, 13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:51:55
ምድብ :- 2 ዳዉዶ

ጀግናዉ የኢማም አህመድ መረዳጃ እና የት/ት ማህበር
#ለአራተኛዙር የዚያራ ፕሮግራም አካሂዷል

አቅመ ደካሞችን እና የቲሞችን ልብስ ሲያለብስ ዉሏል።
#ደግነት
#ንፁህልብ
#እዝነት
#ሁሉንም_በኢህላስ
333 views anu እ'ን'ደ'ማ'ን'ነ'ቴ እኖራለሁ , 10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:58:45 ስሉ ኡድሕያ ወሳኝ ነጥቦች

....የኡድሕያ መስፈርቶች.....

1ኛ; ከቤት እንስሳ መሆን አለበት
ግመል፣
በግ ወይም ፍየል እና
ከብት (ላም ወይም በሬ)።

2ኛ; እድሜው የደረሰ መሆን አለበት
ከብት፦ 2ዓመት ሞልቶት 3ኛ መቁጠር የጀመረ፤
በግና ፍየል 1ዓመት የሞላው
[ለተቸገረ ሰው በግ 6ወር ሞልቶት 7ኛ መቁጠር የጀመረ]፤
ግመል 5ዓመት ሞልቶት 6ኛ መቁጠር የጀመረ።

3ኛ; ግልፅ ከሆነ ነውር የጠራ መሆን አለበት
ግልፅ ከሆነ በሽታ የጠራ፤
ዓይኑ ያልታወረ፤
ግልፅ የሆነ ማንከስ የማያነክስ
ያልተሰበረ
[ከዚህ የከፋ ነውር (ጉዳት) ያለበት ከሆነም አይቻልም]



ተወዳጅ የሆኑ ነጥቦች፦

ያማረና ውብ የሆነ ኡድሕያ ገዝቶ ማደለብ፣ ማወፈር እና ለዕይታ ግልፅ እንዲሆን መልቀቅ
ዋጋው ውድ የሆነውና ተወዳጅ የሆነው መግዛት
ከቻለ ግመል
ካልሆነ ከብት
ካልሆነም በግ ወይም ፍየል ማረድ

ከሰላት በኋላ በፍጥነት ማረድ
ከእርዱ መቅመስ (መብላት
የኡድሕያ ወጪ ሚያደርገው ሰው በራሱ እጅ ማረድ
የእርዱ ቀን ዒድ እስከ ሚሰገድ ድረስ መፆም


መታወቅ ያለበት ነጥብ፦

ግመል ወይም ከብት ያረደ
ለ7 ሰው ማከፋፈል ይቻላል
በግ ወይም ፍየል ከሆነ ለ1 ሰው ብቻ
296 viewsousman, 09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:12:15 ያጀመዓ ነገ እንዴት መፆም ያቅተናል

ነገ 9ኛውን የዙል ሂጃ ቀን
(አረፋ ላይ የሚቆምበትን ቀን) መፆም ያለፈውን አመትና..የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪውን ያክል ምንዳ ያገኛል ረሱል (ﷺ)
289 viewsousman, 09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:39:26 #ነገ_ሀሙስን ...

"የዓረፋህ ቀን (የወርሃ ዙል ሒጃህ 9ኛው ቀን) ለዕለተ ጁሙዓህ ጋር ከገጠመ መጾሙ እንደት ይታያል"?


መልስ፦ "ብቻውን ራሱ ይጾማል። ምክንያቱም በመጾሙ የሚፈለገው የዓረፋህን ቀን እንጂ ጁሙዓህን አይደለም"።

ዶ/ር አል-ዑሶይሚ


"ዐረፋ ቀን የጁምዓ እለት ከዋለ፤ የምንፆመው የዓረፋ እለት ስለሆነ እንጂ ጁምዓ ቀን ስለሆነ አይደለምና።መፆሙ ችግር የለውም። ይሁንና ለጥንቃቄ ሲባል ከፊቱ ያለውን ሐሙስ እለት መፆሙ ተመራጭ ነው"።

ኢብኑ ባዝ

እና የቻልን ነገ ኸሚስን በፆም እናሳልፍ ለማለት ነው አላህ ይቀበለን!

@ImamAhmedcom
326 viewssalim abdela, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ