Get Mystery Box with random crypto!

‍ ------------ ------------- ★ለፍቅር ፊዳ★ ------------ -------- | ikhlas Tube

‍ ------------ -------------
★ለፍቅር ፊዳ★
------------ -------------

★ክፍል ሰላሳ አንድ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…ለኔ ሚሆነኝ እሱ ነው ገባህ አለቀ ደና ሁን"ብላኝ ሄደች ሀፍሲ በምን ላስረዳሽ በአላህ ወላሂ ቅስሜን ስብርብሩን ነው ያወጣችልኝ ኡፍፍፍ…"በረጅሙ ተንፍሶ ጭንቅላቱን ይዞ ዝም አለ ሀፍሲ ምን እንደምታረግ ግራ ገብቷት ትከሻውን ይዛ
" ደና ነሀ"
"ደና ነኝ"ድምፁ ግን ሀዘን እንደሞላው ያስታውቃል
"አይዞህ በቃ ተረጋጋ እሺ ከዚ ቡሀላ አትንገረኝ ይበቃኛል"
"ምን,አለቀ እኮ ምን ቀረው ትንሽ ነው የቀረኝ እሱን ልጨርስልሽ እና ደሞ ማያ ጋር ትወስጂኛለሽ"
"ከፈለክ እሺ"
"እሷ ልቤን ሰብራ መሄዷ ለኔ ከነካሊድ መቋረጥ ወደ አላህ መመለስ ሰበብ ሆናኛለች ምንም ቢሆን በዚ አመሰግናታለው ግን ከሷ ስብራት ቡሀላ እንደ ማያ ነበር ሴት የጠላሁት ግን አንቺን ካገኘሁሽ ቡሀላ ሁሉም አንድ እንዳልሆኑ ተረዳው"ሀፍሲም ደስ ብሏት እየተሽኮረመመች አንገቷን ሰበር አርጋ
"እንዴት"አለች
"ማለትማ ሀያእ አለሽ ሰው አክባሪ ነሽ በዚም እንዳንቺም አይነት እንዳሉ አስባለው አላህ ይጨምርልሽ"
"አሚን እና ታሪክህ በዚው አበቃ"
"አው ልጨምርበት"
"ሀሀሀ ይሻላል እ…እህትህ ምን አይነት ሁኔታ ላይ ናት"
"አልሀምዱሊላህ ከባሏ ጋር በሰላም እየኖሩ ነው ለህመሟ ውጭ ሀገር በተሻለ ሁኔታ አሳክሟት ሁለት ልጆችን ወልዳለች ሶስተኛም እርጉዝ ናት አልሀምዱሊላህ አላህ በመጨረሻም ክሶናል"
"ማሻአላህ እና ትምርት ጨርሰሀል"
"አረ በማርኬቲንግ የሶስተኛ አመት ተማሪ ነኝ"
"ወላሂ ታሪክህ በጣምደስ የሚል ነው አስተምሮኛል"
"እና አንቺስ የህይወት መንገድሽን አታካፍይኝም"
"ሀሀሀሀሀሀ በጣም ታስቃለህ የኔ ህይወት እንደማናቹም ችግር ፈተና ፍቅር መሰበር መጣመር አንዱንም አላቃቸው አያቁኝ በቃ የኔ መኖር ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ነው ወላህ ምንም ሚወራ የህይወት ታሪክ የለኝም"
"ወላሂ በጣም ምትአጅቢ ፍጥረት ነሽ"
"አረ ነው"ፈገግ አለች
"እና ማያ ጋር መች ልውሰድህ"
"ዙሁርን ሰግጄ ምሳ በልቼ ልምጣ እና ትወስጂኛለሽ"
"ዛሬ ምሳ እኛ ጋር ነህ የትም መሄድ አይቻልም"
"አረ ዩሚን ዛሬ እንግዳ አመጣልሻለው ብያታለው አንቺ ነሽ ምትመጪው እንጂ"
"አረ ባባ ካልፈቀደልኝስ"
"እኔ ጠይቀዋለው መቼስ እንቢ አይለኝም"
"እሺ ካልክ"
ሰሚር ሰአቱን ካስተዋለ ቡሀላ
"በይ በቃ ዙሁር እየደረሰ ነው መስጊድ ልሂድ ለባብሰሽ ጠብቂኝ ሰግጄ መጣለው በዛው ባባሽን አስፈቅድልሻለው" ብሏት ወጣ በደስታ እየፈነጠዘች ገብታ ለእናቷ እና ወንድሟ ነገረቻቸው ወንድሟ በደስታ አቅፋት
"ራስን ጠብቂ እሺ የኔ ውድ"አላት እናቷ ደሞ
"አይ የኔ ቅልብልብ ለዚም በቃሽልኝ"
"ውይ ማሚ ደሞ ምሳ ጠራኝ እንጂ ሊያገባኝ ነው።አላልኩሽ ሆ"
"አይይይ ነገ መቀየሩ ይቀራል ብለሽ ነው"
"ውይ ኡሚ"እየተሽኮረመመች ኡዱ ልታረግ ወጣች ኡዱእ አርጋ አዛን ወቶ ሳይሰገድ ቀደም ብላ ሰግዳ ወንድሟን ምሳ አብልታ መኝታውን አስተካክላ ሁሉንም አቅርባለት ልብሷን ልትቀይር ወጣች ልብስ እያወጣች እያየች ስጥል ስታነሳ በመጨረሻ እንደ ጨረቃ ሚያፈካትን አንድ ቆንጆ ሰፊ ልብስ ለብሳ ያለወትሮዋ ተውባ ፈክታለች ነገር ግን አንድም የተቀባችው ነገር አልነበረም ልብሱ ነበር ያፈካት ከልብሷ ጋር ሚሄድ ቦርሳ እና ጫማ ለብሳ ውጪ ላይ ቁጭ ብላ ጠበቀችው ብዙም ሳይቆይ በራቸው ተንኳኳ በፍጥነት ሄዳ ከፈተች አባቷ እና ሰሚር ነበሩ ሰሚር አምሮባት ሲያያት ፈገግ ብሎ ከላይ እስከ ታች ካያት ቡሀላ አይኑን ሰበረ አባቷም
"የኔ ሙሽራ ልታገቢ ነው እንዴ እንዲ የተዋብሽው"አሏት ፈገግ ብላ አንገቷን ደፋች
"የኔ አይናፋር በይ አታስቁሚው ውጪ"አሏት የአባቷን ግንባር ስማ ቻው ብላው ወጣች መኪናውን ከፍቶ አስገብቷት ጉዞ ወደ ቤቱ ጀመረ…


★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents