Get Mystery Box with random crypto!

ሁለቱ ጓደኛሞች አመታትን አብረው በትምህርት አሳልፈዋል፡፡ የህፃንነትም ሆነ የወጣትነት ዕድሚያቸውን | ikhlas Tube

ሁለቱ ጓደኛሞች አመታትን አብረው በትምህርት አሳልፈዋል፡፡ የህፃንነትም ሆነ የወጣትነት ዕድሚያቸውን ያሳለፉት አንዱ የአንዱ የልብ ጓደኛ በመሆን ነው፡፡

ታዲያ ምንም እንኳን አብሮ አደግ ጓደኛሞች ቢሆኑም ሁለቱም በተለያየ የህይወት መርህ የሚመሩ የሁለት አለም ሰው ናቸው፡፡

ለአንደኛው ህይወት የእለት ተለት ደስታ ናት፤ ነገ ብሎ ቀመር እሱ ጋር አይሰራም፡፡ ዛሬን መብላት፣ መጠጣት፣ መደሰት፤ በቃ ስለነገ ነገ እራሱ ያውቃል ነው፡፡

ሌላኛው በሌላ በኩል ህይወት በህግጋትና በቀመር የምትመራ፤ ዛሬ ተጀምራ ሞት ሲመጣ የምታበቃ፤ በጅምር ላይ ያለች ቤት ናት ብሎ ያስባል፡፡ እያንዳንዱ እርምጃው ነገን ከግምት ያስገባ ነው፡፡ ለዚህ ሰው ህይወት ማለት ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ የእራስን ቤተሰብ መመስረት ነው፡፡

እስቲ የእናንተስ የህይወት መርህ መንድን ነው? የህይወታችሁ ትልቁ አላማስ የቱ ነው?


@ikhlasstudents
@ikhlasstudents