Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክ ታላቁ አጼ ሰንደቅ አልማ በዓለም ለመጀመ | ወልድ ዋሕድ

ታሪክ

ታላቁ አጼ ሰንደቅ አልማ



በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን አዳቅሎ ያስገኝ፤

የጀነቲክስ አባት፤

በስሙ እጼያ/እስያ/ አሀጉር የሰየመ፤

33 አንበሶችን የገደለ ልዕለ ሰብዕ(super man)፤

የሰውና የአራዊት ንጉሥ፤

ታላቅ ፈላስፋ፤

....

✦ዘመን ከተቆጠረ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ ዓመተ ዓለም ላይ ሱባ ሱባያ በሚባል ከተማ ላይ ግዮን በሚፈስበት ምድር የአምለክ አገልጋይ ካህን የነበረ የንጉሦች ንጉሥ ስመ መንግስቱ እንደ አባቱ መጠሪያ ስም ኢትዮጲስ የተባለ ኤልካኖ የሚባል ነበር።ከሰባቱም ወንዶች ታለቁ ንጉሥ ነገሥትና የኤል (የእግዝአብሔር) አገልጋይ እሴ ወይም አጼ ሰንደቅ አልማ ወለደ።


✦አጼ ከልጅነቱ ጀምሮ አስተዋይና ተመራማሪ ስለነበር ከእለታት አንድ ቀን ዱር ለዱር እየተዘዋወረ የወፍ ጎጆ አሰራሩን ከተመለከተ በኃላ የወፍ ጎጆ አስመስሎ ጠልፎ ቤቱን በዋሻና በዛፍ ላይ መስራት ጀመረ። እንደዚህ ያለ ከሰማይ ወፍና ከምድር አራዊት ጥበብን ሲማር የንብ ማር ቆርጦ ሲበላ ቆይቶ የማሩን ሰፈፍ አሰራር ሲያስተወል ለንቡ አውራ የተሠራውን የሰፈፉን ሁኔታ ወሰዶ ለአባቱ ያሳየው ነበር። አጼም ከምስጥ ተዋጊነትን፤ ከጉንዳን ፈጣንነትን ከእንስሳትና ከዱር አራዊትና ከሰማይ ወፍ ያለወን ሥረዓትና ጥበብን አየተማረ ከአራዊት ጋር አደገ።


✦አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል አድርጓል። ከነዚህም ውስጥ በቅሎ ከአህያና ከፈረስ እንድትወለድ #ለመጀመሪያ ጊዜ የአደረገ አጼ ነው።ብዙ ሺህ የሚሆኑተን እፅዋት አዳቅሏል።ስለቤት ምግብ፣ ስለወጥና ስለወይን ጭማቂ አንዱን ከአንዱ በማዋሐድ፣ በመቀመም ለወገኖቹ ጽፎ አስተምሯል።


✦የሰው ልጆች ከሌላው ፍጥረት የማድረግ የመስራትም እድል ስላላቸው ማንኛውንም ነገር አስተውለው ከአጠኑትና ከአወቁት ተመራምረው ከተረዱት የማይሆን ነገር እንደሌለ ጽፎአል። ብዙ ዘመን፣ ብዙ ዓመታት ከሌሎች ፍጥረት በይበልጥ እንደሚኖሩ ኅልቆ አእባን በሚባለው የድንጋይ ጥበብ መጸሐፍ ጽፎአል።


✦የሰው ልጅ ብዙ አመታትን ለመኖረ ከፈለገ ይላል ሥራቸው በማይነግል እፅዋቶችና ጥራት ካለው ድንጋይ ውስጥ የሚወጣን ውኃ በየጊዜው መጠጣት ያስፈልጋል ብሎ ተናግሯል። አጼም አቻ የሌለው ታላቅ ፈላስፍ ነበር።ለሰራዊቱ ሁሉ የጦርነት ስልትና ዘዴ ያስተምራቸውም ነበር።


✦አጼ ሰንደቅ አላማ ለልጅ ልጆቹ በየአስር አመቱ የንጉሥ ልጅ ሁሉ ሊነግሥ የፈለገ ከንጉሥ ጋር መግጠም አለበት ብሎ ከእንስሳት የተማረውን ህግ ስለመሰረተ በገዛ በአስረኛ ዘመኑ የሚገጥመው ስለጠፍ ከአንበሳ በረት ውስጥ ያሉትን አንበሶች ሁሉ ገጥሞና ጥሉ በቡጢ እየመታ 33 አንበሶችን ገደለ። አጼም የሰውና የአራዊት ንጉሥ እኔ ነኝ ብሎ ለልጁ ለታምሪያ የሳበን መንግሥት ሰጠው።የሚመስለው ጀግና ስለጠፋ ልዕለ ሰብዕ(super man) ተባለ።


✦ከፍብፅ እስከ ሞአብ ያሉትን ሃገሮች ወረረ። አማሌቅንና ፍልስጤምን አስገበረ። ስለዚህ ያስገበረውን ሃገር በስሙ እጼያ/እስያ/ አለው።ትርጓሜውም ታላቋ ሃገር ማለት ነው። እንደሱባውያን #እጼያ ሲሆን እንደ እብራውያን #እስያ ይባላል።


✦በዚህ ጊዜ በሼንና በምፅዋ በሚገኙ ሸለቆች ውስጥ ድንኳኑን አስተክሎ ሳለ የመልከጼዴቅና የኢትኤል አምላክ በራዕይ ተገለጸለት "አባቶችህ ያላዩትን ታያለህ፤ እድሜም በብዙ ትጠግባለህ፤ መንግሥትህም ታስረዝማለህ፤ እጅ መንሻ ጋዳ በዘርህ እና በቃል ኪዳኑ ቀን እንጅ ዛሬ አይሁን፤ ለማየት የወደድከውን ለማድረግ ተፈቅዶልሀል" አለውና በተራራዎች መካከል ሲያልፍ አየ። በዚያም አጼ/እሴ/ ነቢዩን ሳሙኤልን የአምላክ መላዕክ ነግሮት ነበርና ከአጼ ጋር ተገናኘና እጁን ሳመው። ሁለቱም እንደሚተዋወቁ ሰዎች ሆነው በአንድ ላይ አምላካቸውን አመሰገኑ።


✦በነገሠ በ14ኛው ዘመኑ ከኪትም እስከ ሙት ባህር ከትልቁ ባህር እስከ ሬሴን ያሉ ጎሣዎችና የጎሳዎች አለቃ ሁሉ በንጉሡ ጥሪ መሰረት ተሰበሰቡ ሥርዓቱም በግዬን መገናኛ ኢትዮጵ ኢትኤል በስሙ ምድሩን ኢትዮጵያ፤ ወንዙን ጵንኤል ብሎ ስም አውጥቶ የከበረ ድንጋይ በአስቀመጡበት ምድር ላይ ሌትና ቀን የተለያዩ የራስ ጌጦች፤ ስማቸው ጌራ የሚባሉ ልዩ ልዩ ክቡር በርኔጣዎች፤ የእጅ ቀለበቶች፤ ከእንቁዩጳና ከአልማዝ ድንጋይ ሺህ ጊዜ መቶ ሺህ የሚሆኑ የወርቅና የብር መክሊቶች ተዘጋጁ። ንኤል ማለት የአምላክ ፍንጣሪ፤ ግዩን ማለት ፈሳሽ ማለት ነው።


✦አጼ ሰንደቅ አልማ አንድ መቶ ሺህ ሰረገሎች በአሥር ሺህ ሰረገሎች በአሥር ሺህ አንድ መቶ አምሳ ፈረሰኞች በሰባት ሺህ ልዩ ልዩ ፈጣን ግመሎች በወርቅ እና በብር ጌጥ በተሸለሙ እግረኛ ሰራዊት ሁሉ ታጅቦ ወደ ግዮን ዳርቻ ወረደ።


✦በዚያም አንድ በመንፈስ የሚመራ ታላቅ ነቢይ እና ካህን ነበረ እርሱም ቅባአ መንግስቱን አዘጋጅቶ ጠበቀው ነብዩ ከቀባው በኋላ እንዲህ አለው " ሺህ ዓመት ንገሥ አንተን የሚመስል የሚስተካከል ንጉሥ ፈጽሞ አይመጣም። ስምህም ለዘላለም በዘርህ ዘንድ # አጼ እንጂ እጼ ወይንም እሴ አትባልም። የመንግሥትህም ስም ያየሁት #ሰንደቅ_አልማ ሲባልና በተለያዩ # ቀለሞች_በዓለም ላይ ሲውለበለብ አይቻለሁ። " ብሎ ታላቁ ካህን እና ነቢይ ራኤል ትንቢት ተናገረ። የኢትዩጵያ ሰንደቅ አላማ ከዚህ የመጣ ነው።

ኢትኤል ነኝ
ጣና ዳር
┈┈┈••✦~~~

ምንጭ :- ፩)የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ መፃህፍ በመሪ ራስ አማን በላይ