Get Mystery Box with random crypto!

እችልበታለሁ! . (#ፈይሠል_አሚን) . በርግጥ ጉራ አይደለም. . . ግን. . .ያላየሁት የለም! | ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

እችልበታለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በርግጥ ጉራ አይደለም. . .
ግን. . .ያላየሁት የለም!
ከሕይወት ተምሬያለሁ. . .
ለክቶ መወሰን፣
እችልበታለሁ!
ስሕተትና ጊዜ ከከተቱኝ እሣት፤
ሳልከስል መነሣት፣
በጎዶሎ ስሜት ላይ. . .
በትክክል መሳሳት!
እችልበታለሁ!
.
አንቺም ብትሔጂ. . .
እርግጠኛ ነኝ፣ልቤን እንደማደነድን፣
ሔደሽ ሳትጨርሺ፣ቆስዬ እንደምድን፣
አዎ! እርግጠኛ ነኝ!
በመብረቅ ፍጥነት፣
በብርሃን ፍጥነት፣እንደማገግም፣
ቢኾንም. . .
ቢኾንም. . .
ላጣሽ አልፈልግም!
.
@huluezih
@huluezih