Get Mystery Box with random crypto!

ልክ ነበር! . (#ፈይሠል_አሚን) . ያለፈው ሁሉ. . . ቢያቃጥልም ያፅናናል፣ ቢያሳፍርም ያፀናል | ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

ልክ ነበር!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ያለፈው ሁሉ. . .
ቢያቃጥልም ያፅናናል፣
ቢያሳፍርም ያፀናል፣
ቢያታገልም ያቆማል፤
በዚህ ሁሉ መሐል. . .
ያማል!
ግን. . .አልፏልና አላፍርበትም፤
በትናንቱ በሬ አላርስበትም!
ምክንያቱም. . .
እንዲህ ነው ሕይወት፣የጊዜ ሥርዓቱ፣
ያደረግነው ሁሉ. . .
ልክ ነበር በሰዓቱ!
.
@huluezih
@huluezih