Get Mystery Box with random crypto!

የማለዳ ማስታወሻ #148 . አህያ ፀባይ አላት! አህያ ጉልበት አላት! አህያ ታዛዥ ናት! አህያ | ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የማለዳ ማስታወሻ #148
.
አህያ ፀባይ አላት!
አህያ ጉልበት አላት!
አህያ ታዛዥ ናት!
አህያ ቻይ ናት!
.
ነገር ግን. . . ሁሉ ነገር ያላት አህያ የራሴ የምትለው ነገር የላትም። የምትሸከመው ሸክም የራሷ አይደለም። ፀባይዋ ከዱላ አያስጥላትም። ታዛዥነቷ ፍትሕ አያስገኝላትም። እሷ ያላት ሁሉ የአህያውን ባለቤት ብቻ ነው የሚጠቅመው።
.
አህያ ከባለቤቷ የምታገኘው ብቸኛው ነገር ከለላ ነው።የአህያው ባለቤት አህያውን ጅብ እንዳይበላት ይጠብቃታል። ይኼን የሚያደርገው አህያዋ ስለሚገ'ባት ሳይኾን የሚያገኘውን ጥቅም እንዳያጣ ብቻ ነው። አንድ ቀን አህያዋ ጉልበቷ ሲሟጠጥ፣እርጅና ሲጫናት ግን ባለቤቷ ራሱ አውጥቶ ለጅብ ይሠጣታል።
.
አህያ ብታኮርፍ፣አህያ ሐሳብ ብትሠጥ፣ አህያ ቀንና ሌት ብትሠራ፣ ከተሸካሚነት ነጥሎ የሚያያት የለም። መነሻ መድረሻዋ በአለቃዋ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ነው። አህያ የራሷ አለቃ ራሷ መኾን አትችልም። ዕድሜ ዘመኗን የተሸከመችው ሸክም፣ በቃል የማይገለፅ ታታሪነቷ እና ታዛዥነቷ ማምሻ ላይ ከጅብ አያስጥላትም።
.
ብዙዎቻችን እንደዚህች አህያ ነን። የሰው ሸክም ስንሸከም፣ ጅብ ፈርተን ስንጠራ አቤት፣ስንላክ ወዴት እያልን የራሳችን የኾነ አንዳች ነገር ሳይኖረን መጨረሻችን የጅብ ማዕድ ላይ ነው። ለእኛ የማይተርፍ ሸክም ለምን እንሸከማለን? የማያሳድገን አፈር ላይ ለምን እንቀበራለን? ራሳችንን የምናጣበት ሥፍራ ላይ ለምን እንከርማለን? በዚህም በዚያም ከጅብ ካልተረፍን ጉልበት ሳለን ከጅቡ ብንገናኝ አይሻለንም? ጉልበታችን ሲደክም በሌላ አህያ ለምንተካበት ሥፍራ ለብዙ የሚተርፍ ኃይላችንን እናባክናለን? የራሴ የምትለው ምንም ከሌለህ አንተ ማነህ? ማንም!
.
እርግጥ ነው. . .ብዙዎቻችን እንደዚያች አህያ ነን። ነገር ግን አህዮች አይደለንም። ብልጦችን ከነ ነውራቸው አንሸከምም።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih