Get Mystery Box with random crypto!

ቁርአንን በሙዚቃ አድርጎ የመጨፈር ድፍረት ከየት መጣ ልባችን ደርቆ በትቢት ተወጥሮ ቁርአንና | Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ

ቁርአንን በሙዚቃ አድርጎ የመጨፈር ድፍረት ከየት መጣ

ልባችን ደርቆ በትቢት ተወጥሮ
ቁርአንና ሀዲስን ወደዚያ ወርውሮ
በትንሹ ጭንቅላት ኩራት ተጨምሮ
አቤት አወዳደቅ በተንኮል ተወጥሮ።

ከዚህ  በፊት እህት ወንድሞቻችን ከሙዚቃ የማይተናነስ ነሺዳና መንዙማ በሚሉበት ግዜ ተዉ አላህን ፍሩ ማለት ሲገባ ማሸ አላህ በርቱቱቱቱቱ!!! ሲባል ነበር !!

እሀዉ ዛሬ በተከበረው በአላህ ቃል በሆነው ቁርአን ሲከፈን፣ ሲጨንቀን፣ስንደሰት ለሁሉም ነገር መፍትሔ ሆኖ የሚያገለግለንን የህይወት መመሪያ የሆነው የጌታችንን ቃል
#በራፕፕፕፕ ተደርጎ መጣላችሁ።

ዉሻ በቀደደው ጅብ ይመላለሳል!!
የኛው ሙስሊሞች ናቸው የተባሉት
#በሰለዋት እየጨፈሩ አይተናል ሴቱ ወንዱ አንድላይ ሆኖ ለዛውም መስጂድ ዉስጥ ጥጋበችን እስከዚህ ደርሶአል።

አላህን ፍሪ በየት ለዛች እህትሽ
አስታዉሺ በየት ጀሃናም አለልሽ
ምንም አይጠቅምሽ በትቢት መወጠርሽ።

አላህን ፍራ በለው ያንን ወንድምህን
በቁርአንና በሀዲስ የሚቀልደዉን
ቁርአንን በሙዚቃ አድርጎ የሚጫዋተውን።

ስለዚህ ወደጆቼ፦
==========
ቁርአን የአይን ማረፊያችን እንጂ የማንም ዱርዬ ቲክቶክ Fb YouTube ማሞቂያ የጨዋታ መስሪያ አይደለም የቻላችሁት ጥራት አድርጉ።

ወላሂ ቢላሂ
||
አላህ አየያዙ  የከፋ ነው ባላሰብነው ሰአት ይዘናል!!
ሀቅን መደበቅ እናቁም  ለእውነት እንኑር እስልምና ህይወታችን ነው በህይታችን ማንም እንዲጫወት መፍቀድ የለብንም  አላህን ፈርታን በአላህና በነብዩ ስም የሚቀልዱ ሰዎችን ከመታገል ወደኃላ ማለት የለብንም ።

እስልምና ዉብ ነው የዉቦች ዉበት
እስልምና ፍቅር ነው የሰላም ሰገነት
በቁርአን በሀዲስ ከመጡ  እሱን ለማንቋሸሽ
በትቢት በጥጋብ የአላህን ቃል ለማንቋሸሽ
በአላህ ይሁንብህ አትፍራ ወደኃላ አትሽሽ
ማንም አይቻልም እስልምናን ማንቋሸሽ


እህት ወንድሞቼ የአላህ ዲን መጫወቻ አይደለም ማንም እየተነሳ የሚጫወትበት በያላችሁበት መታገል አለባችሁ በዚህ በወጣትነታችን ለእስልምና የሚጠቅም ቢያንስ አንድ መልካም ተግባር መፈፀም አለብን ።

አደራ አደራ
========
||
እስልምናን ጠቅማን እንጂ አድክማን ወደ አኼራ መሄድ የለብንም  በአላህ ፊት ተጠያቂ መሆናች አይቀሬ ነው ።
እኛ ዝም በማለታችን ነው በሙስሊሞች ሰይቀር በቁርአን መጫወት የጀመሩት አስቡት ምን ያህል ልባችን እንደደረቀ።

ወላሂ የአላህ ትግስት ይገርማል
እንደኛ ተንኮል ትቢት ቢሆንማ እሳት ይዘንባል ብዬ አስባለሁ ትግስቱ የአላህ ይገርማል።

አላህ ትክክለኛውን መንገድ ይምራን
ተንኮለኞችን ተገቢውን ቅጠት ይስጣቸው
አላህ አንድነታችንን ጠንካራ ያድርግልን መለያየት የጥፋልን መልካም ስራ ሰርተው ጀነት ከሚገቡት ያድርገን አሚን አሚን።

ተፃፈ በወንድማችሁ
Muktarr Hussen Butijra
|||
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen