Get Mystery Box with random crypto!

አሰድ እሳት ( Leo) ፫ ፲ ውበት ... በእምብርክክ የሚያስኬድ ቁንጅና ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላ | Horoscope አሰትሮሎጅ

አሰድ እሳት ( Leo) ፫

፲ ውበት ... በእምብርክክ የሚያስኬድ ቁንጅና ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? እሷ ያንን እንዳደረገች የታሪክ ድርሳኗ ላይ ተከትቧል ... በዛ ላይ ሁሉም ሊዮዎች ላይ እንዳለው አይነት ብልሃት እሷም ጋር ነበር ። ሊዮ ቆንጆ አደሉም ለሚለው ጥያቄ መልስ የምትሰጥልን ብዙዎ በውበቷ ማለው ሊያመልኳት የዳዳቸው ... ምስራዊት ቆንጆ ኪሊዮፓትራ ። ሊዮ ናት ( በነገራችን ላይ አወደነገስቱም መኳንት ያፈቅሯታል ይላል መኳንት ደሞ ቁንጅና ነብሳቸው ባሻዬ ስለዚህ ሊዮ እንስቶች ቆንጆ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው )
፲፩ ንግስና ፣ ውበት ፣ ጥበብ ... አንዳንዶች የደቡብ አረቢያን ሴት ናት ይላሉ ። አንዳንዶች ጥቁር መሆኗን ዓለም እንዳያምን የተፋለሱ ታሪኮች በመከተብ ለጥቁር ያላቸውን ጥላቻ ራስ ወዳድነታቸውን አሳይተዋል ። እሷ ግን መሃልዬ መሃልዬ ዘሰለሞን በተሰኘው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል " ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ " ብላለች ። አክሱማዊት ንግስት ፣ የውበት እምቤት ፣ የጥበብ ባለቤት ፣ ንግስት ሳባ ( ማክዳ) ። ስለ አለም ስልጣኔ ሲነሳ የሷ ተፅዕኖ አለ ። የስነህንፃ ጥበብ ሀሁ ሲነሳም አለች ። ነጮቹ ከጫካ ሳይወጡ ሀፍረተ ስጋቸውን በቅጠል መሸነፍ ሳያቆሞ እኛ ፊደል ቀርፀን የመገበያያ ገንዘብ አትመን ሌላ ታሪክ ውስጥ የነበረነው በዚች ንግስት ጥበብ ነበር .... አዎ ሊዮ ናት ።
፲፪ ንግስና ቅድስና ... ስለነሱ ከበቂ በላይ በታላቁ መፅሀፍ ማንበብ ትችላላችሁ ። የኔ ድኩማን ቃላትም ስለነሱ ለመፃፍ አይበቁም ብቻ ግን ቅዱስ ዳዊት እና ጠቢቡ ሰለሞን ሊዮ መሆናቸውን ላስታውሳችሁ ብዬ ነው ።

ከእናቱ ማህፀን የተመረጠ የሚለው የአውደነገስት ሀረግ ዝም ብሎ አደለም ። ሊዮ የጥንካሬ ፣ ያለመሸነፍ ፣ የአይበገሬነት ... ምናምን ምሳሌ እንጂ እንደምትሉት ጉራ ብቻ አደለም ። ገና ትን እስኪላችሁ እቀጥላለሁ ... ለዛሬ ባለልደቶች መልካም ልደት እንደሁሌው እወዳችኋለሁ
https://t.me/horoscopebloodT