Get Mystery Box with random crypto!

ኤርትራን በተመለከተ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~ በተመሳሳይ ግብፅ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

ኤርትራን በተመለከተ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በተመሳሳይ ግብፅ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ መድባ ወደ ኢትዮጵያ መሣሪያ እያስገባች በጋምቤላ ለኦነግ ሸኔና ለሕወሓት ጭምር በአየርና መሬት ላይ ስታስታጥቅ፣ እነዚህ አካላት ምንም አይተነፍሱም ነበር፤ ይህ የሚያሳየው መንግሥትን የሚያዳክም ሲሆን ዝምታ፣ መንግሥትን የሚያግዝ ሲሆን ደግሞ ጩኸት ማብዛት የሚወዱ መኖራቸውን ነው››

‹‹በመሆኑም ኤርትራ እኛን አስቸገረን ካላልን ምን አሳሰባቸው? ኤርትራ ባስቸገረን ጊዜ እኛ ራሳችን በቃን እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ካሳሰባችሁ ሱዳን ትውጣ ብላችሁ መግለጫ አውጡ፡፡ ከዚያ ኤርትራ ትውጣ ብትሉ እኛ መረዳት እችላለን››

‹‹በሌላ በኩል በእኛ አስታኮ የኤርትራ መንግሥትን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም፤ ቢያንስ ከተፈጠረው የሰላም ስምምነት አንፃር እኛ እንዳንፈርስ አግዘውናል፡፡ የጋራ ጠላት የነበረን ቢሆንም ትጥቁን የፈታ የሕወሓት ታጣቂ ግን ኢትዮጵያዊ ነው››

‹‹ስለዚህ አቅማችን ባለበት እስኪጠናከር ሕወሓት መጀመሪያ ትጥቁን መፍታት ይጀምርና እንደማንወጋ ስናረጋግጥ፣ ከጀርባችን ያለው አካል ማንም ይሁን ማን ይውጣልን ማለት እንችላለን›› ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ በሲሳይ ሳህሉ


ለአራት ኪሎ ሚዲያ ዜና እና ትንታኔዎች ሰብስክራይብ ያድርጉ

የማህበረሰብ ትስስር ገጾቻችንን ይከተሉ!

ፌስቡክ : https://www.facebook.com/profile.php?id=100088485937460&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም : https://t.me/Horn_African_News

ትዊተር : https://twitter.com/Aratkilomedia?t=0_firYVZjR-U-k4JFC-S6w&s=09