Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ ጦር ከትግራይ እየወጣ ነው | Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

የኤርትራ ጦር ከትግራይ እየወጣ ነው | Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ


ከ2 ዓመታት በፊት የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተሰማርቶ የነበረው የኤርትራ ጦር እየወጣ ነው ተባለ።

ጦሩ ዛሬ ሽሬ፣ አድዋ እና አክሱምን ከመሳሰሉ የክልሉ አካባቢዎች በጭነትና በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እየተጫነ መንቀሳቀሱን የአራት ኪሎ የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

ሆኖም ጦሩ መሉ ለሙሉ ኢትዮጵያን ለቆ ስለመውጣቱ የታወቀ ነገር የለም።

በህወሓት እና በመንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት አፈጻጸም የሚገመግምና ኦባሳንጆን፣ ኡሁሩ ኬንያታን እና ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ያካተተ የአፍሪካ ኅብረት ልዑክ እና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እንዲሁም የፌዴራል መንግሥቱ ቁንጮ ባለስልጣናት ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 20/2015 ዓ/ም መቀሌ ከተማ መግባታቸው ይታወሳል።

ወደ ከተማው የገቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት የፌደራል መንግሥት ተቋማትን መጠበቅ መጀመራቸው መገለጹም ይታወሳል።

የኤርትራ ጦር ትግራይን ለቆ መውጣት የጀመረው ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም ከዐይን እማኞች የምስክርነት ቃል በስተቀረ በሁለቱ ሃገራት መንግስታት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።


#aratkilomedia ን በተለያዩ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉ
............

ዩቲዩብ :
https://youtube.com/@AratKiloMedia
https://youtube.com/@aratkilonews

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/profile.php?...

ቴሌግራም: https://t.me/Horn_African_News

ትዊተር: https://twitter.com/Aratkilomedia?t=0...