Get Mystery Box with random crypto!

ለሕይወትህ ትርጉም የማይሰጥ ጉዳይ ላይ ጊዜ አታጥፋ 'ጊዜ ሕይወት ማለት ነው፤ ሕይወት ጊዜ ከሆ | Hoora cast/talent Factory

ለሕይወትህ ትርጉም የማይሰጥ ጉዳይ ላይ ጊዜ አታጥፋ

"ጊዜ ሕይወት ማለት ነው፤ ሕይወት ጊዜ ከሆነ ዋናው ነገር ጊዜህን እንዴት እየተጠቀምክበት ነው? እኔ በሕይወቴ አልቀልድም የምትል ሰው ነህ? ጊዜህን የምታከብር ከሆነ እቤትህ ቁጭ ብለህ ጊዜዬን ምን ላይ እያጠፋሁ ነው ብለህ በፅሞና ችግርህን ነቅሰህ ትፅፈዋለህ፤ ለፃፍከው ችግር ደግሞ ማሰብ የአእምሮ መሳሪያህን በመጠቀም መፍትሔውን ትፈልግለታለህ፤ ስለ ሕይወትህ ስትፅፍ ለሕይወትህ ትርጉም የማይሰጥ ጉዳይ ላይ ጊዜህን አታጠፋም፤ ያወቅከውን ችግር በተቃራኒው ወደ መልካም በመቀይር ደጋግመህ ስትፅፈው መሆን ያለብህን ሰው በመሆን ጊዜህን በአግባቡ ትጠቀማለህ"

ዳዊት
ውብ ቀን ተመኘን