Get Mystery Box with random crypto!

ጥቁር ነጥብ (እዮብ በላይ) ጭጋግ ሞላው የዳመነው በልቤ ነው ይዘንባል ከአይኔ ጥቁር አባ | ግጥም ፍቅር ቅኔ

ጥቁር ነጥብ
(እዮብ በላይ)

ጭጋግ ሞላው የዳመነው በልቤ ነው
ይዘንባል ከአይኔ ጥቁር አባይ የሚፈሰው
እንባየ ነው ወንዝ ሆኖ በሲቃው ያራሰው

አለም ሲዞር ውሎ መፍሰሱ በጭለማ ያላበቃ
ልክ ፀሀይ ስትጠልቅ በቀን ተደብቃ
ፅልመትን ለማጥፋት ትወጣለች ጨረቃ

ፌሽታ አጥቼ በሀዘን ተሞላ ልቤ
ጥዋትና ማታ ጥቁር ነጥብ ሆኖ ሀሳቤ

ደብዝዞ በልዞ በህይወቴ ያረፈው ነጥብ
የማይለቅ የታተመ የዘላለም ጥቁር ነጥብ
የማይጠፋ የማይለወጥ የፈጣሪ
ማህተብ

ጥቁር ነጥብ፤

ጥቁር ሰማይ ጥቁር ቀን
እራሱን ያው ያንኑ የሚደግም በቀቀን

ጥቁር ነጥብ ጭለማ ያከበረ
በራሱ ቃል ቃሉን የሻረ

አለም ጥቁር ለበሰች
ህግ ስለተላለፈች

እንባየ መውረዱ አልቆመ
አባይም መፍሰሱ አልቆመ
ጥቁር ነጥብ በአለም ላይ አለ እንደታተመ

ዝናብ ያዘለ ደመና
ጭጋግ የሞላው የብርሀን ፋና

ዘንቦ አይዘንብ ብርሀን አይታይ
ጠቁሯል የልቤ ሰማይ

ጠፋሁ ጠፋሁ የለሁም የለሁም
ታጥሬያለሁ በሬሳ ይጎርፋል የሰው ደም

ጥቁር አባይ የናይል ባለንጀራ
አለምን አራሱ በደም እንዲጠራ

እንዲጠራ የጠቆረው ምሽት
ትንሽ ቢቀላ ሀሴት ቢሸምት

በፍርድ ቀን ማንም አይተርፍም
በህያውም ሆነ በሙታንም
ስርየት መክደኛ አያተርፍም

አለ አለ የፍርድ ወንበር
የሸንጎው መሪ ይፈርዳል ሳይለይ ዘር

ልንገርህ ልብ በል ስማ ይችን ቃል
ክበር ካለህ በጠጠርም ይከበራል
እረኛም እንሰሳውን ትቶ ሰውን ይመራል
ጎልያድን ጥሎ ዳዊት ተከብሯል

ብላቴናዎቹ እንዲቦርቁ እንዲሆኑ አንድ ልብ
ያሰሙ መውጫዋን ያችን የንጋት ኮከብ

ዳዊት በበገና እዝራ በመሰንቆ
ጥቁር ብርሀን ይውጣ አለምን ለቆ

ዛሬም እንደ ትናንቱ ዳግም እንደገና
ሀጥያተኛ ነኝና ጌታችን ሆይ ና

ኤሎ ሄ ኤሎ ሄ ኤሌ ሄ ኤሎ ሄ