Get Mystery Box with random crypto!

ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ ማን ሊታደም ከድግሱ? ዘውድ ያወረው ድንብር ፣ ማህላውን የረሳ ሳር ያለመልማል | ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹

ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ?
ዘውድ ያወረው ድንብር ፣ ማህላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ።

ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬም፣ ሞቼም ልክሳት!

የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባ ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት

ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሀገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠርያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
......

https://t.me/HgerenewsEthiopia

https://vm.tiktok.com/ZMNdcTwmb/?k=1