Get Mystery Box with random crypto!

ታላቁ ሰሓባ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ ረ.ዐ. ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም ሆነ አስተዋጽኦ አልነበረ | HAppy Mûslim

ታላቁ ሰሓባ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ ረ.ዐ. ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም ሆነ አስተዋጽኦ አልነበረውም፡፡ የአላህ ፈቃድ ሆነና እስልምናን ተቀበለ፡፡ ከሰለመ በኋላ በምርኮነት በሩም ንጉስ እጅ ወደቀ፡፡ ንጉሱም ሊገድለው አሰበ፡፡
‹ሃይማኖትህን የምትተው ከሆነ ይህን ያህል ሀብት እሰጥሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ ሃይማኖቴን እንድተው ብለህ ሙሉ ሀብትህን ብትሰጠኝ የምተው አይደለሁም፡፡› አለው፡፡
ቀጥሎም ‹ሃይማኖትህን ከተውክ ከሥልጣኔ አካፍልሃለሁ፡፡› በማለት ሊያግባባው ሞከረ፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ የዚህ ዓለም ስልጣን ለኔ ምንም አይደለም፡፡› አለው፡፡
‹እንግዲያውስ እገድልሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹የሻህን መስራት ትችላለህ፡፡› አለው፡፡
ንጉሱ ጋሻጃግሬዎቹን ‹በቀስት ወጋጉትና አሰቃዩት፡፡ አትግደሉት፡፡› በማለት አዘዛቸው፡፡
ከፍተኛ ስቃይ እስኪሰማው ድረስ እጆቹን በቀስት ወጋጉት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› በማለትም ጠየቁት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በቀስቱ እግሩን ወጋጉት› አላቸው፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
ንጉሱ በመቀጠልም ‹ሁለት ባልደረቦቹን አምጡና በበርሜል ዘይት በማፍላት እዚያ ውስጥ ክተቷቸው፡፡› አለ፡፡ ከሱ ጋር የነበሩትን ሁለት ሙስሊሞች አመጡና ዐይኑ እያየ በፈላ ዘይት ውስጥ ከተቷቸው፡፡ አሁንም ጠየቁት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡ አለበለዚያ …› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በሉ ውሰዱና ዘይቱ ውስጥ ክተቱት፡፡› አላቸው፡፡
ሊከቱት ወደ በርሜሉ ሲያስጠጉት ታላቁ ሑዘይፋ ረ.ዐ. አለቀሰ፡፡
ሰዎቹ ይህንኑ ለንጉሱ ነገሩት፡፡ ንጉሱም ‹መልሱት ወዲህ› አላቸው፡፡ መልሰው አመጡት፡፡
ንጉሱም ‹ማልቀስህ ተነግሮኛል፡፡› አለው፡፡ ሑዘይፋም ‹አዎን› አለው ለንጉሱ፡፡
‹እንግዲያውስ ሃይማኖትህን ተው፡፡› አለው፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አለ፡፡
‹እንግዲያውስ ለምን አለቀስክ?› አለው፡፡
‹በአላህ መንገድ የምሰጠው ነፍስ አንዲት ብቻ መሆኗ ነው ያስለቀሰኝ፡፡ በሰውነቴ ላይ ባለው ፀጉር ልክ ነፍስ ቢኖረኝና በአላህ መንገድ አንድ በአንድ ብሰጥ እመኝ ነበር፡፡› አለው፡፡

@heppymuslim29