Get Mystery Box with random crypto!

ጨካኙ አባት ሴት ልጁ እንዲህ ትላለች .... ' 6 አመታትን ያህል አባቴ ባልገባኝ ምክንያ | HAppy Mûslim

ጨካኙ አባት

ሴት ልጁ እንዲህ ትላለች ....
" 6 አመታትን ያህል አባቴ ባልገባኝ ምክንያት ለትዳር ጥያቄ የሚያቀርቡልኝን ወንዶች ሁሉ እንቢ አለ ። በዚህም ጉዳይ ምንም አይነት ውይይት አይቀበልም ።
እኔን ፍለጋ በሩን የሚያንኳኩ ሰዎችን ሁሉ አባቴ በእንግዳ ማረፊያው ክፍል ለግማሽ ሰዓት አንዳንዴም ከዛ ያነሰ ያህል ያወራቸዋል ፣ ከዚያም የመጣው ወጣት በፍጥነት ይወጣል

እናቴ አባቴን ለመጠየቅ ቸኮለች" ምንድን ነው የሆነው "
እንዲህ ሲል መለሰላት፡- ጥሎሹን አልወደድኩትም የእሱ አቻ በቤታችን ውስጥ የለችም !

የመንፈስ ጭንቀት ወደ እኔ ዘልቆ መግባት ጀመረ ። አባቴ በኔ ድርሻ እና በኔ ደስታ መጋረጃ በመሆኑ በሱ መቆጣት ጀመርኩ። ራሴን እጠይቅ ነበር "እንዴት ሊሆን ይችላል? ለገንዘብ ብሎ ለአንዲት ሴት ልጁ የማይቻለውን ጥሎሽ ይመኛል !

አሁን ተዓምር ተፈጠረ ።
አባቴ ከአመልካቾች ከአንዱ ተስማማ ።
ባለቤቴ ስለከፈለልኝ ጥሎሽ አባቴ ሳይነግረኝ ትዳራችን ተፈፀመ...

የሚገርመው ነገር ባለቤቴ በአማካይ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያለ እንጂ ቀድመውት ከጠየቁት ሰዎች አንፃር ከብዙዎቹ ድሃ ነበር
እሱም ከአባቴ ጋ ስለተስማሙበት ጥሎሽ (መህር)አልነገረኝም

በትዳራችን አስር አመታት አለፉ ። ከባለቤቴ ምንም ክፉን ነገር አላየሁም። ያየሁት ርህራሄን, ደግነትን እና ስስትን ብቻ ነው

ዕድሜዬ እየጨመረ ቢሆንም በባለቤቴ እንክብካቤ ምክንያት ምንም የመከፋትም የመረበሽ ስሜት አይሰማኝም ነበር ።
አባቴ ጥሎን ወደማይቀረው ጉዞ እስኪሄድ ድረስ..

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባለቤቴ ወደኔ መጣ ወደ ደረቱ አቀፈኝና “ትንሿ አትዘኚ " አለኝ ።
" ትንሿ " በምትለው ቃል በጣም ተገረምኩ ።
በስስት አየኝና ... ‹‹አዎ ትንሼ ነሽ ።
.....
ለጋብቻ አንቺን ስጠይቅ አባትሽ ምን ማድረግ እንደምችል ጠየቀኝ። ትንሽ አሰብኩና ፡- አጎቴ ብዙ ምሰጠው የለኝም ። ግን ምዬ የምነግርህ ነገር ቢኖር አንተን በሞት ብታጣህ እንኳ የቲምነት እንዳይሰማት አደርጋለሁ። ልክ የአብራኬ ክፋይ እንደሆነች ሴት ልጅ እንከባከባታለሁ " አልኩት ።

አባትሽም ፈገግ አሉና ፡- "ሚስትህ ልጄ ናት"አሉኝ

@heppymuslim29