Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ማስታወቂያ እንደሚታወቀው ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የጤና | Health info & vacancy news (HIVN)

አዲስ ማስታወቂያ
እንደሚታወቀው ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ለባለፉት ወራት ምዝገባ አድርገው እና ተገቢውን አሟልተው ከተገኙ 7582 ተመዝጋቢዎች መካከል ለ200 ባለ ዕድለኞች ሰኔ 10  በኤሊያ ሆቴል የመጀመሪያ ዙር ዕጣ በተሳካ ሁኔታ አውጥቷል ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰኔ 10 የመጀመሪያ ዙር እጣ ከወጣ በኃላ የመመዝገብ ዕድሉ ያመለጣቸው  የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች ዕድሉ ዳግም እንዲሰጣቸው በግልም ሆነ በቡድን በከፍተኛ ሁኔታ እየጠየቁ ይገኛሉ ። በመሆኑም ዕድሉ ያመለጣቸውን ሰራተኞች ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ለመጨረሻ ጊዜ ዕድሉን የሚጠቀሙበት መንገድ  ተዘጋጅቷል።ስለዚህ በተለያዩ ምክንያቶች ምንም ዓይነት ምዝገባ ያላደረጋችሁ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች እስከ  10/11/15 ዓም ድረስ ብቻ አስፈላጊውን ሁሉ በማሟላት መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን ።
- ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ከላይ ከተቀመጠው የመጨረሻ የምዝገባ ቀን በፊት የተመዝጋቢዎች ቁጥር ከሞላ ምዝገባው ከተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በፊት ሊቆም ይችላል።
ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች
ከምትሰሩበት ተቋም ሰራተኛ መሆናችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ (3 ኮፒ)
51 ሺህ እና 4 ሺህ የተከፈለበት የዳሽን ባንክ ስሊፕ(ኦሪጅናል) (3 ኮፒ)
የኗሪነት መታወቂያ/ፓስፖርት/የመስሪያ ቤት መታወቂያ
ምዝገባው የሚካሄደው በውክልና ከሆነ ህጋዊ ውክልና እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ
3*4 ፎቶ ብዛት 2
ለበለጠ መረጃ
+251934185874
+251942576792
የመመዝገቢያ አድራሻ
22 ከጎላጎል ወደ ድንበሯ በሚወስደው መንገድ ከትራፊክ ፅ/ቤት ጀርባ ቡኒ አዲስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ