Get Mystery Box with random crypto!

የ17 አመቱ የግንደበረት ነዋሪ 7ኛው የHVE ነፃ የልብ ቀዶ ተጠቃሚ ሆነ:: በከፍተኞ የልብ ድካም | Healing Valves Ethiopia

የ17 አመቱ የግንደበረት ነዋሪ 7ኛው የHVE ነፃ የልብ ቀዶ ተጠቃሚ ሆነ:: በከፍተኞ የልብ ድካም ውስጥ የነበረው ታዳጊ ከሞት አፋፍ ላይ የነበረ ሲሆን በሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት በሆነው HVE እና የነፃ በጎ አገልጋይ የሀገራችን ልጆች በሁለት የልብ በሮች ላይ የተሳካ ቀዶ ጥገና ተከናወነለት:: በዛሬው እለት (እሁድ) የቤተሰባቸውን ጊዜና ደስታ የሰውት እነዚህ የበጎ ፈቃደኞ አገልጋዮች በተሳተፋበት 5 ሰአት በፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና ላይ እጅግ አስጨናቂና አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለሰባተኛ ጊዜ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል:: ክብርና ምስጋና ለአገር በቀል የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን:: በአሜሪካ የHVE እህት ድርጅት ለምታደርጉት ያልተቋረጠ እርዳታ በታካሚ ቤተሰቦች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳቹህ::

Today healing valves Ethiopia (HVE) performed the 7th life saving open-heart surgery for a 17 years old boy from Gindeberet. In post RHD severe mitral valve stenosis and severe tricuspid regurgitation with recurrent heart failure, the young boy successfully underwent mitral valve replacement plus tricuspid valve repair. A volunteer local team member of HVE put aside family and personal joy and spent the precious Sunday on saving a life for free. We salute the local volunteer team and respect to your commendable performances. We are always grateful to our sister company in US to make this true by supporting financially.