Get Mystery Box with random crypto!

ምድራችን ላይ የሚሰልጥኑ ሁለት መንግስታት ወይም አገዛዞች አሉ። አንደኛው የጨለማው ወይም የሰይጣ | Healing School Official

ምድራችን ላይ የሚሰልጥኑ ሁለት መንግስታት ወይም አገዛዞች አሉ።
አንደኛው የጨለማው ወይም የሰይጣን አለም ነው። ይህም መንግስት ዘፈንን ኢንተርኔትን ፊልሞችን እና ዘርዝረን የማንጨርሳቸውን ነገሮች በመጠቀም ሁለት ነገሮችን እያደረገ ነው።
አንደኛው በእጁ ያሉት ነፍሳት የትም እንዳይሄዱ አጥብቋ እየያዛቸው በማወቅም ባለማወቅም የእርሱ ተከታይ እያደረጋቸው ነው።
ሁለተኛው ይህ የጨለማ መንግስት የተለያዩ ነገሮችን በመጠቀም እያደረገ ያለው አዳዲስ ነፍሳትን ማሳትና ለእራሱ መንግስት ማዋል ነው።
ሁለተኛው መንግስት የእግዚአብሔር መንግስት ወይም የብረሃን መንግስት ነው። በዚህ መንግስት ስር ያሉ ሰራተኞች ሁለት ነገር እያደረጉ አሉ ከዚህም በኋላ ሊያደርጉ ይገባቸዋል።
አንደኛ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማለትም መዝሙር ስብከት ኢንተርኔት ... በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያሉት እንዲጠነክሩ እንዲፀኑ እና እንዲያድጉ ማድረግ አለብን።
ሁለተኛ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ከጨለማው አለም ነፍሳትን በመናጠቅ ለእግዚአብሔር የብረሃን መንግስት ማዋል አለብን።
ማቴዎስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁷ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤
³⁸ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።

God's General Eth
@Witness_Neba contact