Get Mystery Box with random crypto!

ዋልያዎቹ ፈርኦኖቹን የሚገጥሙበት ስታዲየም ታዉቋል !! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ | HaTrick sport 🇪🇹

ዋልያዎቹ ፈርኦኖቹን የሚገጥሙበት ስታዲየም ታዉቋል !!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሜዳዉ ማድረግ የሚገባዉን ጨዋታ የካፍን መመዘኛ የሚያሟላ ስታዲየም ባለመኖሩ ምክንያት ካፍ በገለልተኛ ስታዲየም የኢትዮጵያ ጨወታዋን እድታደርግ ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከፈርኦኖቹ ጋር የሚያደርጉትን የመድብ ሁለተኛ ጨዋታ በማላዊ ለማድረግ ከዉሳኔ ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል። ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸዉንም እዚያዉ በማላዊ ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

@HaTricksport