Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ታዉቋል !! ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት | HaTrick sport 🇪🇹

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ታዉቋል !!

ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀዉ የሴካፋ ሴቶች እግርኳስ ዉድድር ላይ ተሳታፊ ለሆኑት ሉሲዎቹ አሰልጣኝ ፍሬዉ ሀይለገብርኤል በዋና አሰልጣኝነት ተሹሟል።

አሰልጣኝ ፍሬዉ ከ20 አመት በታች የሴቶቹን ብሔራዊ ቡድን ይዞ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በአለም ከ20 አመት በታች የሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ላይ እስከ መጨረሻው ምዕራፍ ድረስ መጓዝ ችሎ እንደነበር አይዘነጋም። ለአሰልጣኙም ሉሲዎቹን በዉድድሩ ላይ ዉጤታማ እንዲያደርግ ሀላፊነትም ተጥሎበታል።

ከግንቦት 14 እስከ 28 ድረስ ለአስራአራት ቀናት ያክል በሚደረገዉ ውድድር ላይም ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በዚህም መሰረት ሉሲዎቹ በምድብ ሁለት ከታንዛኒያ ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን ጋር መደልደላቸዉ ይታወሳል።

@HaTricksport