Get Mystery Box with random crypto!

1 ጥያቄ ልጠይቃችሁ አሁን ሁላችሁም ባላችሁበት እስቲ ያሳለፉችሁት ህይወታችሁን አስታውሱት ስንት | 𝕫𝕖𝕟𝕗𝕒𝕝𝕒𝕪𝕖😍😍

1 ጥያቄ ልጠይቃችሁ
አሁን ሁላችሁም ባላችሁበት እስቲ ያሳለፉችሁት ህይወታችሁን አስታውሱት ስንት ወንጀል እና መአት ትዝ ይላችሀል? ይህ እናንተ ያስታወሳችሁት ነው እናንተ ረስታችሁት አላህ የፃፈውስ?
ለምን ተውበት አታደርግም?
ለምን ተውበትህ ላይ አትፀናም?
ለምን ትመለሳለህ?
ለምን ሰላም እንደምታገኝ እያወክ ጥሩ ስራን አትሰራም?
ለምንስ ከወንጀል አትቆጠብም?
ለምን የቀብር ቤትህን አታስብም?
ብቻህን ጨለማ ውስጥ እንደምትኖር ለምን ትዝ አይልህም?

መስፈርቱን አሟልተህ ወደ ጌታህ ተመለስ

1 ከምትሰራው ወንጀል ሙሉ በሙሉ ራቅ
2 ላትመለስ ለራስህ ቃል ግባ
3 ከምርህ ተፀፀት
ከነዚህ 1ዱን ካላሟላህ አልቶበትክም ወላሂ ከልብህ ስማ ሞት መች እንደሚመጣብህ አታውቅም ራስህን አዘጋጅተህ ጠብቀው ይሄን ፅሁፍ እያነበብክ ስንት ሰው ሞተ? ስንት ሰው ከስራው ጋር ተገናኘ? ስንቱስ ሰው ወይኔ አላህን እና መልዕክተኛውን በታዘዝኩ እያለ ከንቱ ፀፀት ተፀፀተ? አንተ ደግሞ ይህን ፅሁፍ ሳትጨርስ ልትሞት ትችላለህ ተራህ ደርሶ ይሆናል።

@Hasaek