Get Mystery Box with random crypto!

:::::::በጋብቻ ለሊት:::::::: በጋብቻ ለሊት የሚፈፀሙ ተግባሮች 1፡- ባገባህበት ወቅ | Hanan Alhadra💚

:::::::በጋብቻ ለሊት::::::::

በጋብቻ ለሊት የሚፈፀሙ ተግባሮች

1፡- ባገባህበት ወቅት የምታደርገው ድንቅ ዱዓ..
“አላሁመ ኢኒ_አስአሉከ ኸይረሃ ወኸይረ ማ ጀበልተሃ ዓለይሂ ወአኡዙ ቢከ ሚን ሸሪሃ ወሸሪ ማ ጀበልተሃ አልይሂ

አላህ ሆይ! እኔ የዝችን ሴት መልካም ጎን እና እንድታዘነብል ያመላከትካትን በጎ ነገር እጠይቀሃለሁ፤ ከተንኮሏና ካዘነበለችበት መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ)፡፡”

2፡- የሰርግህን ቀን ዉሎ ካሳለፍክ በኋላ ምሽት ላይ ሚስትህ ጋር አንድ ላይ ስትሆኑ ብቸኝነት ይሰማታል፣ ፍርሀት ይወራታል፣ሀፍረት ይሰማታልና አጫውታት፣ ዘና አድርጋት!

3፡- ረከዓተይን አሰግዳት፡፡ ይህ ሶላት ባል የቤቱ አባወራና አስተዳዳሪ እንዲሁም ጠባቂ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ሁለታችሁም በዛ ለሊት ፍርሃት እንዳይሰማችሁና ለወደፊት የትዳር ህይወታችሁ መሳካት ጥሩ አስተዋፅኡ አለው፡፡

4፡- ወተት አጠጣት (ይህ ለርሷ መረጋጋትን ያደርግላታል)፡፡ صلى الله عليه وسلم አንድ ባል ሚስቱ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ወተት እንዲያጠጣት መክረዋል፡፡

5፡- ራሷን(ግንባሯን) ይዘህ የሚከተለውን ዱዓ አድርግ

ቢስሚላህ አላሁመ ጀንኒብነ ሸየጧነ ወጀንኒብነ ሸይጧኒ ማ ረዘቅተና

በአላህ ስም! አላህ ሆይ! ሰይጣንን አርቅልን፤ያበረከትክልንን ነገርም ከሸይጧን አርቅልን)”

#እርሷም ግንባርህን ይዛ ይህን ዱዓ ታሰማለች፡፡ ይህ ዱዓ ለወደፊት የትዳር ህይወታህ መቃናት፣ የምትወልዷቸው ልጆች ከሸይጧን እንዲጠበቁና መልካም ልጆች እንዲሆኑ ይረዳል፡፡ትዳሩ ያማረና የሰከነ እንዲሆንም ያግዛል፡፡

ይህ የተወዳጁ # صلى الله عليه وسلم ሱና ነው፡፡ ባረከሏሁ ፊኩም

ይህ መልዕክት እርሶ ጋ አይቀመጥ ለሌሎች ሼር በማድረግ የአጅር ተካፍይ ይሁኑ

t.me/hanan_islamic_paje