Get Mystery Box with random crypto!

ለእህቶቼ ይድረስልኝ ፋጢማ ረዲአላሁ አንሃ አንድ ቀን ቁጭ ብላ እያለቀሰች  ሳለ ምን ሆነሽ ነ | Hanan Alhadra💚

ለእህቶቼ ይድረስልኝ

ፋጢማ ረዲአላሁ አንሃ አንድ ቀን ቁጭ ብላ እያለቀሰች  ሳለ ምን ሆነሽ ነው ለምን ታለቅሽያለሽ ? ብላ አንደኛዋ ጠየቀቻት !
እሷን ግን ያስለቀሳት የአዱኒያ ጉዳይ አልነበረም !!
መልሷ እንዲህ የሚል ነበር…… እያስለቀሰኝ ያለው  የሞትኩኝ እለት ጀናዛዬ ታጥቦ ተገንዞ ሲሰገድብኝ
ወንድ ፊት ነው ያኔ የምሆነው እና ወንዶች ሲሰግዱብኝ ከከፈኑ ውስጥ የሰውነቴ ቅርፅ ስለሚታይ ሊኖር የሚችለው ነገር አሁኑኑ ሳስበው ዘግንኖኝ ነው  አፍሬ ነው አለች ።

ሱበሃነላህ የምታለቅሰው ለዚህ ነበር

እህቴ ዛሬ የእግርሽ ጥፍር ለምን ወጣ ? የፀጉርሽ ጫፍ ለምን ታየ ? ከሰውነትሽ ሽታ ወንድ ጋር ለምን ሄዳ ብሎ ወሏሂ አሏህ ይጠይቅሻል።
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል  የትኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ ከወንዶች አጠገብ አታልፍም  ወንዶች የእሷ ሽታ አይሸታቸውም  እሷ ዝሙተኛ ናት ዝሙተኛ ናት  ዝሙተኛ ናት ብለዋል

እያንዳንዱ ድርጊት ከረህማን ጋር ፣ ከአላህ ጋር ፣ ከማሊከል  ሙልክ ጋር የሚያጋጭ መሆኑን እያወቀች አንዴም ቁጭ ብላ አታለቅስም !  ለማልቀስም አታስብም ! እንደውም ስትመከር ሁሉ የምትሰጠው ምላሽ ሌላ ነው ። አላህ አላከረረም ፤ አላህ አላጠበቀም፤ እንደ ድሮ እንኑር ወይ ? የሚል የሚያሳዝን መልስ ትሰጣለች።

የምትገላለጭው እህቴ ሆይ ፦
ያለችሽ ሰዓት አሁኑኑ ነውና ወደ ጌታሽ ተመለሺ ።  ነገ ከነገ ወዲያ ሀገር ስገባ ፣ ባል ሳገባ ፣ የመሳሰሉትን  ምክንያቶችን  አታቅርቢ ። መለከል መውት በየትኛው ሰዓት ሩዕሽን እንደሚወስዳት ምን አሳወቀሽ ያ ኡክቲ 

አላህን እንፍራ አላህ የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን
@hanan_Islamic_paje