Get Mystery Box with random crypto!

የባለ ታሪኳ ዘመድ እንዲህ ትላለች ...     ' የአክስቴ ልጅ ናት ፣ ሰላሳዎቹን ገብታለች ።  | Hanan Alhadra💚

የባለ ታሪኳ ዘመድ እንዲህ ትላለች ...
    " የአክስቴ ልጅ ናት ፣ ሰላሳዎቹን ገብታለች ።  እንደየትኛዋም ሴት ሁሉ የትዳሯ መዘግየት አሳስቧታል ። ታድያ እናቶች በሰፈራቸው ለዚህ አይነቱ ክስተት ዱዓ መቀማመጥ ልምድ አላቸው ። ለሷም ዱዓ ይዘውላታል ። 

" ያ ረብ ኢማን ያለውን ፣ ዐመለን ሷሊሑን ...!" እያሉ ከተያያዙት ሰንበትበት ብለዋል ።

   የባርያውን ልመና ሚቀበለው (አልሙጂቡ) ፣ ድምፁን  ሰሚው (አስ-ሰሚዑ) ምላሽ ሰጣቸው ። ገራሚው ነገር ታድያ በስንት ዱዓ የመጣው ባል እዛው ከጎረቤት ይኖር የነበረ ሰው መሆኑ ነው ። በስራ ሌላ ሀገር  ነው ሚኖረው ። እሱም ምትሆነውን በመፈለግ ውስጥ ነበር ።  ከብዙ መንከራተት ኋላ ውሳኔውን  እዚህችው ሴት ላይ አሳረፈ ።

      የኒካሁ ዕለት የሁለቱም ጎረቤት የነበረች ተጫዋጭ ሴት ወደሱ ጠጋ ብላ  ...

" ምነው እዚሁ አጠገባችን ሆነህ ነው ብዙ ዳቦ ያስጨረስከን?  ! " አለችው ።

እናም ...
   አጠገባችሁን ተመልከቱ ፣ ከጎናችሁ ጀምሩ ፣ ዙርያችሁን በደንብ ቃኙ

የተባረከውን ይስጠን ፣
      የሰጣችሁን አላህ ያቆይላችሁ ! 

https://t.me/hanan_islamic_paje