Get Mystery Box with random crypto!

የትዳር ምርጫ … •===============• ☞በሂወትህ በበርካታ ምርጫዎች ውስጥ ታልፋለህ። ብዙ | Hanan Alhadra💚

የትዳር ምርጫ …
•===============•
☞በሂወትህ በበርካታ ምርጫዎች ውስጥ ታልፋለህ። ብዙዎቹ ምርጫዎችህ ስህተት ቢኖርባቸውም በቀላሉ ልትቀለብሳቸውና ያለከባድ ጉዳት ልታስተካክላቸው ትችላለህ። ትዳር ላይ የምትወስነው ምርጫ ሲቀር። እሱ ግን በቀላሉ ማጠፍ አይቻልም። በቀላሉ ማስተካከልም ከባድ ነው።
አንዴ ከሳትክ በምርጫህ መቀጠሉም ቀጣይነት ያለው ስቃይ ይሆንብሃል። ምርጫህን ቀልብሰህ ሌላ አማራጭ መከተሉም የራሱ የሆነ ከባድ ጠባሳ አለው። እከሌ «ፈት_ነው መባሉ ራሱ የሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም። ለሴት ከሆነ ደግሞ ጉዳቱ ከዚህም ይብሳል።

☞ስለዚህ አጀማመርህ ላይ አስተዋይ ሁን። ትዳር መንፈሳዊ፣ አእምሯዊ እና አካላዊ ስምምነትን የሚሻ ትልቅ ውል መሆኑን ተረዳ። ምን አይነት የትዳር አጋር ልምረጥ ? ማንን ላግባ? በሚለው አጀንዳ ላይ ስትወስን ከስሜት ተፅእኖ ውጭ ሆነህ ፣ ተረጋግተህ፣ መክረህ፣ አማክረህ እና ሰዎች ለሚሰጡህ አስተያየቶች ዋጋ ሰጥተህም ጭምር መሆን አለበት።

ቤተሰብ...ለጓደኛ...ለወዳጅ...ሼር ማድረግ እንዳትረሱ
https://t.me/hanan_islamic_paje