Get Mystery Box with random crypto!

ፈርሂን ወርቁን ማን ሰረቀው ክፍል ①③!(መጨረሻ) (ነኢማ ኸድር) 'ፈርሁ | 👳‍♀[𝐒𝐮𝐡𝐚𝐢𝐛][𝐀𝐥𝐰𝐞𝐝𝐮𝐝]-𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋👳‍♂

ፈርሂን
ወርቁን ማን ሰረቀው
ክፍል ①③!(መጨረሻ)
(ነኢማ ኸድር)

"ፈርሁ ባለፈው የካዝናውን ቁልፍ ጥለውት እኔና ሀጂ ከጀርባ ስናስቆርጠው ጥግ ላይ አገኘነው እንዴት እንደገባ ግን እንጃ ብሮችም ተገኝተዋል አሁን ትዝ አለኝ የካዝናው መሳቢያ ለካ ትንሽ ክፍተት አለው ሁሌ ለ ሀጂ እነግራቸዋለው እልና እረሳዋለው ይኀው ዞሮዞሮ ጣጣው ወደኔ መጣ እየገረመኝ "እና ሀጂ ሲያዩት ምን አሉ"አልኩት ምን እንዳሉ ለመስማት ጓጉቼ
"ባክሽ ፈርሁ ሀጂ ወላሂ እስካሁን ታሟል ደም ግፊቱ ተነስቶበት እዛው ወደቀብን ፈርሁ ወላሂ የሌለ ነው የተፀፀተው"ብሎኝ ዝም አለ ሰለ ሀጂ ስሰማ እንባዬ ፈሰሰ ሀጂ ከ አባቴም በላይ ነበሩ ለኔ ብዙ ሆነዋል ሰአቱ ሳናስበው ሄደ የኔም የ አማርም ስልክ በጥሪ ተጨናነቀ እንደማይቀር ቃል ገብቶልኝ ተለያየን እነ ሀሰናት ቤት ስደርስ ሀሱ የሌለ አምሮባት የሚያምር የሙሽራ ሶፋ ላይ ተቀምጣለች ቶሎ ተስተካክዬ ወደሳሎኑ ወጣው ሀሰናት አኩርፋለች ስታየኝ ደነገጥኩ ኩርፊያዋን ለማጥፋት ብዬ "እእ ቲማቲሜ ፏ ብያለው ሙሽራዋ እኔ ነኛ ምመስለው ሀሀሀ"ስላት እየሳቀች "ሂ አዝጌ ቆይ ከሰርጌ ብኃላ ላግኝሽ"ብላ ሳቀች ቤቱ የሌለ ቀውጢ ሆኗል ሴቶች ተሰብስበው በድቤ ይቀውጡታል አንደኛዋ ሚዜ "ያዙ"አለች
ነጭ ትወዳለች ደሞሞ ለብሳዋለች
ለሀቁ አሆነ ትቦንሰዋለች አለች አንዷ ቀጠል አርጋ
አሩሳ አሩሳ ይቀወጥ አሩሳ
ሀስኒዬ አገባች በሀላል ጠበሳ.................
እያሉ የዙሁር(የ6 ሰዐት ስግደት)ጥሪ ከመስጅዱ እስኪወጣ ድረስ አስነኩት የስድስት ሰአቱ ስግደት በህብረት ሰግደን እራሳችንን አስተካክለን ጨርሰን ሙሽራውን እየጠበቅን ነው በ አማካኝ 8 ሰአት መድረስ እንዳለባቸው ተነግሮዋቸዋል እንደ ድንገት ስልኬ ጠራ እጄ ላይ ስለነበር ወዲያው አየሁት መርዋን ነበር "ሀሉ"አልኩት እየተሞላቀኩኝ "የኔ ሞልቃቃ አሁን ሽማግሌዎቹ ጨርሰው ወተው ደውለውልኝ ነው የዛሬ ወር ተወስኗል እኔና አንቺ ስለተስማማን ምንም ቀጠሮ ሳይሰጥ ነው የተጠናቀቀው አልሀምዱሊላህ" አለኝ በጣም ደስ ብሎታል ድምፁ ያስታውቃል "የት ነህ"አልኩት ድምፄን ቆጣ አርጌ "ውዴ ለካ አልነገርኩሸም ጓደኛዬ ዛሬ ያገባል እና ሚዜው ነኝ በቃ ከተጠለፍኩብሽም..."ብሎ ሳቀ እኔም እየሳኩኝ ላስደነግጠው "አሚን በደንብ ሞሽረው"አልኩት ስልኩን ዘጋው እንደደነገጠ ያስታውቃል ትንሽ ቆይቶ ደወለና አማር ሁሉንም እንደነገረው ነግሮኝ ትንሽ አውርተን ስልኩን ዘጋን እንደተባለው ልክ 7፡50 ሲል የመኪና ክላክስ ተሰማ ሰው ሁሉ ገረመው አንዳንዱም "ለመጀመሪያ ጊዜ ሰአትን ያከበረ ሙሽራ" እያለ ይገረማል እኔ ግን አልገረመኝም ምክንያቱም ሀጂ ሰአት አክባሪነታቸውን ስለማውቅ የሳቸው አስተዋጽኦ አለበት ስለዛ አልተገረምኩም እቤቱ በር እንደደረሱ አሚን አጅበውት ወረዱ ሴትና ወንድ ስላልተደባለቀ ሙሽራውን ማየት አልቻልንም የምሳ ፕሮግራም አልቆ ወረቀት የሚፈርሙበት ሰአት ደረሰ አማር ፈርሞ ሴቷን ሊያስፈርም መርዋን ወደ ጊቢው ገባ በመስኮት ስላየሁት ፍጥን ብዬ ወጣው እና የቤቱ መግቢያ ጋር ቆምኩኝ መርዋን ሲያየኝ ሳቅ አለ አንድም ቀን መርዋንን ሳቀው ፊቱላዬ እንዲ ሚያምር ፈገግታ አይቼበት አላቅም በእጁ ጠራኝና "አምሮብሻል በይ ሂጂና አስፈርመሽ ይዘሽ ነይ ደሞ እራስሽ ፈርሚበት አሉሽ"ብሎ ከት ብሎ ሳቀ ሊያናደኝ መሆኑ ስለገባኝ "እንኳንም አስታወስከኝ"ብዬው ወደውስጥ ገብቼ አስፈረምኳት ገና ወረቀቱን ሳስገባው እልልታውን እንደ ጉድ አስነኩት ፊርማው እንዳለቀ ከሴቱም ከወንዱም ጋር መንዙማው ቀለጠ እያለ እያለ ሙሽራው ሙሽራትን ይዞ ሄደ በዚ መልኩ የአማርና የ ሀሰናት ሰርግ አለፈ ሰርጋቸው በመጣ በ 15 ቀን ለኔው ጉድ ደሞ መንንጎዳጎድ ተጀመረ ቬሎ መረጣ ሚዜ አዳራሽ...ግን ሁሉንም መርዋን ስላስተካከለው በ ሳምንት ውስጥ ጨረስን ለሰርጋችን 1 ሳምንት ብቻ ቀረው ሁሉም በጉጉት እየጠበቀ ነው እንደ ድንገት ሰኞ ጠዋት ሀጂ ደውለው ሱቅ እንድመጣ ነግረውኝ ወደ ከሰአት ሄድኩኝ ሀጂ ገና ሲያዩኝ ከአይናቸው እንባ መንቦልቦል ጀመረ አቅፌያቸው ተላቀስን ይቅርታም ተጠያይቀን እነሱ ጋር ውዬ ልወጣ ስል "ፈርሁ"አሉኝ
"ወዬ ሀጂ ምን ልታዘዝ"አልኳቸው የያኔው ትውስታ ትዝ ብሎኝ ፈገግ አሉና "የሰርጋቹ 1ሳምንት ወደ አንድ ምርጥ ቦታ ብታሳልፉስ አዋሳ 1 ሳምንት ትሄዳላቹ ቦታ ተይዟል ሁሉ ነገር ጨርሻለው"ብለውኝ ሳቅ አሉ እኔም በደስታ ተጠመጠምኩባቸው የሀጂን ሰርፕራይዝ ለሁሉም ተናገርኩኝ መርዋን ሲሰማ ደውሎ አመሰገናቸው እንዲ እንዲ እያለ እሁዱ ደረሰ እነ አማር ከተጋቡም ወር ሞላው ወይ ጊዜ ሲገርም እሁድ ሁሉም በጠዋት ተነስቶ ይንዳጎዳል የኔ ሚዜዎች ኢነብ ሀሰናት ሀውለትና ሀኒም
የመርዋን ደሞ አንዋር አማር አክረም እና ሱኡድ ነበሩ እሁዱ ሰአቱ አልሄድ አለኝ ሁላችንም በህብረት ቤቱን አፀዳድተን ልንሞሸር ገባን "ሙሽራ መሆን እንዲ ያስጠላል"እስክል ድረስ እነ ኢነብ አደረቁኝ ሁላችንም ተዘጋጅተናል አሁን ሚጠበቀው ሙሽራው ነው ልክ 9 ሰአት ሲል እቤት ደረሱ እልልታው ከ መንዙማውጋ ሰፈሩን በ አንድ እግሩ አቆመው....
እኔና መርዋን የአብሮነት ኑሮዋችንን ሀ ብለን ጀመርን 1 ሳምንቱንም ሀጂ ያዘጋጁልን ቦታ ሄደን የማይረሳ ትዝታ አሳልፈን መጣን አማርና ሀሰናት የሌለ ፍቅራቸውን እያደሩት ነው በተጋባን በ 6 ወሩ የወርቋ ባለቤት ልታገባ እንደሆነ ተነገረን ሁላችንም ደስ አለን የወርቋ ባለቤት ማለት ኢነብ ናት ከዛ ከመልከ መልካሙ ልጅ ጋር!!!!!!

አል ም
ተፈፀመ
1k Like ያንሰዋል

ስለ ታሪኩ ለአስተያየት @muba_ya

በቅርቡ በ አዲስ ታሪክ እንመለሳለን

አስጀምሮ ላስጨረሰን ለአለማቱ ጌታ ምስጋና እናቀርባለን አልሀምዱሊላህ


@eslamik_tube
@eslamik_tube